መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #45
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 45

Ps 45

1 ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ፥ እኔ ሥራዬን ለንጉሥ እነግራለሁ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።

1 My heart is inditing a good matter: I speak of the things which I have made touching the king: my tongue is the pen of a ready writer.

2 ውበትህ ከሰው ልጆች ይልቅ ያምራል ሞገስ በከንፈሮችህ ፈሰሰ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባረከህ።

2 Thou art fairer than the children of men: grace is poured into thy lips: therefore God hath blessed thee for ever.

3 ኃያል ሆይ፥ በቍንጅናህና በውበትህ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ።

3 Gird thy sword upon thy thigh, O most mighty, with thy glory and thy majesty.

4 ስለ ቅንነትና ስለ የዋህነት ስለ ጽድቅም አቅና ተከናወን ንገሥም ቀኝህም በክብር ይመራሃል።

4 And in thy majesty ride prosperously because of truth and meekness and righteousness; and thy right hand shall teach thee terrible things.

5 ኃያል ሆይ፥ ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፥ እነርሱም በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ይገባሉ፥ አሕዛብም በበታችህ ይወድቃሉ።

5 Thine arrows are sharp in the heart of the king’s enemies; whereby the people fall under thee.

6 አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘላለም ነው የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።

6 Thy throne, O God, is for ever and ever: the sceptre of thy kingdom is a right sceptre.

7 ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ።

7 Thou lovest righteousness, and hatest wickedness: therefore God, thy God, hath anointed thee with the oil of gladness above thy fellows.

8 በልብሶችህ ሁሉ ከርቤና ሽቱ ዝባድም አሉ ከዝሆን ጥርሶች አዳራሽ ደስ ያሰኙሃል።

8 All thy garments smell of myrrh, and aloes, and cassia, out of the ivory palaces, whereby they have made thee glad.

9 የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።

9 Kings’ daughters were among thy honourable women: upon thy right hand did stand the queen in gold of Ophir.

10 ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ

10 Hearken, O daughter, and consider, and incline thine ear; forget also thine own people, and thy father’s house;

11 ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና።

11 So shall the king greatly desire thy beauty: for he is thy Lord; and worship thou him.

12 የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል። የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትህ ይማለላሉ።

12 And the daughter of Tyre shall be there with a gift; even the rich among the people shall intreat thy favour.

13 ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው ልብስዋ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው።

13 The king’s daughter is all glorious within: her clothing is of wrought gold.

14 በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፥ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ

14 She shall be brought unto the king in raiment of needlework: the virgins her companions that follow her shall be brought unto thee.

15 በደስታና በሐሴት ይወስዱአቸዋል፥ ወደ ንጉሥ እልፍኝም ያስገቡአቸዋል።

15 With gladness and rejoicing shall they be brought: they shall enter into the king’s palace.

16 በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ፥ በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ።

16 Instead of thy fathers shall be thy children, whom thou mayest make princes in all the earth.

17 ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ ስለዚህ ለዓለምና ለዘላለም አሕዛብ ይገዙልሃል።

17 I will make thy name to be remembered in all generations: therefore shall the people praise thee for ever and ever.