መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #47
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 47

Psalm 47

1 አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።

1 O clap your hands, all ye people; shout unto God with the voice of triumph.

2 እግዚአብሔር ልዑል ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና።

2 For the Lord most high is terrible; he is a great King over all the earth.

3 አሕዛብን ከእኛ በታች፥ ወገኖችንም ከእግራችን በታች አስገዛልን።

3 He shall subdue the people under us, and the nations under our feet.

4 ለርስቱ እኛን መረጠን፥ የወደደውን የያዕቆብን ውበት።

4 He shall choose our inheritance for us, the excellency of Jacob whom he loved. Selah.

5 አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።

5 God is gone up with a shout, the Lord with the sound of a trumpet.

6 ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ።

6 Sing praises to God, sing praises: sing praises unto our King, sing praises.

7 እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና በማስተዋል ዘምሩ።

7 For God is the King of all the earth: sing ye praises with understanding.

8 እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ እግዚአብሔር በቅድስናው ዙፋን ይቀመጣል።

8 God reigneth over the heathen: God sitteth upon the throne of his holiness.

9 የምድር ኃይለኞች ለእግዚአብሔር ናቸውና የአሕዛብ አለቆች ወደ አብርሃም አምላክ ተሰበሰቡ እርሱንም ከፍ ከፍ አደረጉት።

9 The princes of the people are gathered together, even the people of the God of Abraham: for the shields of the earth belong unto God: he is greatly exalted.