መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #145
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 145 |
Psalm 145 |
1 አምላኬ ንጉሤ ሆይ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፥ ስምህንም ለዘላለም ዓለምም እባርካለሁ። |
1 I will extol thee, my God, O king; and I will bless thy name for ever and ever. |
2 በየቀኑ ሁሉ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም ለዘላለም ዓለምም አመሰግናለሁ። |
2 Every day will I bless thee; and I will praise thy name for ever and ever. |
3 እግዚአብሔር ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው ለታላቅነቱም ፍጻሜ የለውም። |
3 Great is the Lord, and greatly to be praised; and his greatness is unsearchable. |
4 ትውልደ ትውልድ ሥራህን ያመሰግናሉ፥ ኃይልህንም ያወራሉ። |
4 One generation shall praise thy works to another, and shall declare thy mighty acts. |
5 የቅድስናህን ግርማ ክብር ይናገራሉ፥ ተኣምራትህንም ይነጋገራሉ። |
5 I will speak of the glorious honour of thy majesty, and of thy wondrous works. |
6 የግርማህንም ኃይል ይናገራሉ፥ ታላቅነትህንም ይነጋገራሉ፥ ብርታትህንም ይነጋገራሉ። |
6 And men shall speak of the might of thy terrible acts: and I will declare thy greatness. |
7 የቸርነትህን ብዛት መታሰብ ያወጣሉ፥ በጽድቅህም ሐሤትን ያደርጋሉ። |
7 They shall abundantly utter the memory of thy great goodness, and shall sing of thy righteousness. |
8 እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥ ከቍጣ የራቀ፥ ምሕረቱም ብዙ ነው |
8 The Lord is gracious, and full of compassion; slow to anger, and of great mercy. |
9 እግዚአብሔር ለሚታገሡት ቸር ነው። ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ነው። |
9 The Lord is good to all: and his tender mercies are over all his works. |
10 አቤቱ፥ ሥራህ ሁሉ ያመሰግኑሃል፥ ቅዱሳንህም ይባርኩሃል። |
10 All thy works shall praise thee, O Lord; and thy saints shall bless thee. |
11 የመንግሥትህን ክብር ይናገራሉ፥ ኃይልህንም ይነጋገራሉ፥ |
11 They shall speak of the glory of thy kingdom, and talk of thy power; |
12 ለሰው ልጆች ኃይልህን የመንግሥትህንም ግርማ ክብር ያስታውቁ ዘንድ |
12 To make known to the sons of men his mighty acts, and the glorious majesty of his kingdom. |
13 መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፥ ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው። |
13 Thy kingdom is an everlasting kingdom, and thy dominion endureth throughout all generations. |
14 እግዚአብሔር በቃሎቹ የታመነ ነው፥ በሥራውም ሁሉ ጻድቅ ነው እግዚአብሔር የተፍገመገሙትን ሁሉ ይደግፋቸዋል፥ የወደቁትንም ያነሣቸዋል። |
14 The Lord upholdeth all that fall, and raiseth up all those that be bowed down. |
15 የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ። |
15 The eyes of all wait upon thee; and thou givest them their meat in due season. |
16 አንተ እጅህን ትከፍታለህ፥ ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ። |
16 Thou openest thine hand, and satisfiest the desire of every living thing. |
17 እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው በሥራውም ሁሉ ቸር ነው። |
17 The Lord is righteous in all his ways, and holy in all his works. |
18 እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው። |
18 The Lord is nigh unto all them that call upon him, to all that call upon him in truth. |
19 ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያደርጋል፥ ልመናቸውንም ይሰማል ያድናቸዋልም። |
19 He will fulfil the desire of them that fear him: he also will hear their cry, and will save them. |
20 እግዚአብሔር የሚወድዱትን ሁሉ ይጠብቃል ኃጢአተኞችንም ሁሉ ያጠፋል። |
20 The Lord preserveth all them that love him: but all the wicked will he destroy. |
21 አፌ የእግዚአብሔርን ምስጋና ይናገራል ሥጋም ሁሉ ለዘላለም ዓለም የተቀደሰውን ስሙን ይባርክ። |
21 My mouth shall speak the praise of the Lord: and let all flesh bless his holy name for ever and ever. |