መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #146
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 146 |
Psalm 146 |
1 ሃሌ ሉያ። ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ። |
1 Praise ye the Lord. Praise the Lord, O my soul. |
2 በሕይወቴ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ። |
2 While I live will I praise the Lord: I will sing praises unto my God while I have any being. |
3 ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆች አትታመኑ። |
3 Put not your trust in princes, nor in the son of man, in whom there is no help. |
4 ነፍሱ ትወጣለች ወደ መሬቱም ይመለሳል ያን ጊዜ ምክሩ ሁሉ ይጠፋል። |
4 His breath goeth forth, he returneth to his earth; in that very day his thoughts perish. |
5 የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምስጉን ነው |
5 Happy is he that hath the God of Jacob for his help, whose hope is in the Lord his God: |
6 እርሱም ሰማይንና ምድርን ባሕርንም፥ በእነርሱ ያለውንም ሁሉ የፈጠረ እውነትን ለዘላለም የሚጠብቅ |
6 Which made heaven, and earth, the sea, and all that therein is: which keepeth truth for ever: |
7 ለተበደሉት የሚፈርድ፥ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ ነው። እግዚአብሔር የታሰሩትን ይፈታል |
7 Which executeth judgment for the oppressed: which giveth food to the hungry. The Lord looseth the prisoners: |
8 እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሣል እግዚአብሔር ዕውሮችን ጥበበኞች ያደርጋቸዋል እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል |
8 The Lord openeth the eyes of the blind: the Lord raiseth them that are bowed down: the Lord loveth the righteous: |
9 እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል ድሀ አደጎችንና ባልቴቶችን ይቀበላል የኃጢአተኞችንም መንገድ ያጠፋል። |
9 The Lord preserveth the strangers; he relieveth the fatherless and widow: but the way of the wicked he turneth upside down. |
10 እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሣል ጽዮን ሆይ፥ አምላክሽ ለልጅ ልጅ ነው። ሃሌ ሉያ። |
10 The Lord shall reign for ever, even thy God, O Zion, unto all generations. Praise ye the Lord. |