መጽሐፈ ምሳሌ | MeTsiHaFe MiSaLae
Proverbs of Solomon | Mishlei Shlomo #1
In Amharic and English
መጽሐፈ ምሳሌ 1 |
Proverbs 1 |
1 የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች |
1 The proverbs of Solomon the son of David, king of Israel; |
2 ጥበብንና ተግሣጽን ለማወቅ፥ የእውቀትንም ቃል ለማስተዋል፥ |
2 To know wisdom and instruction; to perceive the words of understanding; |
3 የጥበብን ትምህርት ጽድቅንና ፍርድን ቅንነትንም ለመቀበል፥ |
3 To receive the instruction of wisdom, justice, and judgment, and equity; |
4 ብልሃትን ለአላዋቂዎች ይሰጥ ዘንድ ለጐበዛዝትም እውቀትንና ጥንቃቄን፥ |
4 To give subtilty to the simple, to the young man knowledge and discretion. |
5 ጠቢብ እነዚህን ከመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል። |
5 A wise man will hear, and will increase learning; and a man of understanding shall attain unto wise counsels: |
6 ምሳሌንና ትርጓሜን የጠቢባንና ቃልና የተሸሸገውን ነገር ለማስተዋል። |
6 To understand a proverb, and the interpretation; the words of the wise, and their dark sayings. |
7 የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። |
7 The fear of the Lord is the beginning of knowledge: but fools despise wisdom and instruction. |
8 ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናንትህንም ሕግ አትተው |
8 My son, hear the instruction of thy father, and forsake not the law of thy mother: |
9 ለራስህ የሞገስ ዘውድ ለአንገትህም ድሪ ይሆንልሃልና። |
9 For they shall be an ornament of grace unto thy head, and chains about thy neck. |
10 ልጄ ሆይ፥ ኃጢአተኞች ቢያባብሉህ እሺ አትበል። |
10 My son, if sinners entice thee, consent thou not. |
11 ደምን ለማፍሰስ ለእኛ ጋር ና እናድባ፥ ለንጹሕም ያለ ምክንያት ወጥመድን እንሸምቅበት ቢሉ |
11 If they say, Come with us, let us lay wait for blood, let us lurk privily for the innocent without cause: |
12 በሕይወታቸው ሳሉ እንደ ሲኦል ሆነን እንዋጣቸው፥ በሙሉም ወደ ጕድጓድ እንደሚወድቁ ይሁኑ |
12 Let us swallow them up alive as the grave; and whole, as those that go down into the pit: |
13 መልካሙን ሀብት ሁሉ እናገኛለን፥ ከምርኮውም ቤታችንን እንሞላለን |
13 We shall find all precious substance, we shall fill our houses with spoil: |
14 ዕጣህን ከእኛ ጋር ጣል ለሁላችንም አንድ ከረጢት ይሁን ቢሉ |
14 Cast in thy lot among us; let us all have one purse: |
15 ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥ ከጎዳናቸውም እግርህን ፈቀቅ አድርግ |
15 My son, walk not thou in the way with them; refrain thy foot from their path: |
16 እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፥ ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና። |
16 For their feet run to evil, and make haste to shed blood. |
17 መርበብ በወፎች ዓይን ፊት በከንቱ ትተከላለችና። |
17 Surely in vain the net is spread in the sight of any bird. |
18 እነርሱም በደማቸው ላይ ያደባሉ፥ በነፍሳቸውም ላይ ይሸምቃሉ። |
18 And they lay wait for their own blood; they lurk privily for their own lives. |
19 እንዲሁ ይህ መንገድ ትርፍን ለማግኘት የሚሳሳ ሁሉ ነው። የባለቤቱን ነፍስ ይነጥቃል። |
19 So are the ways of every one that is greedy of gain; which taketh away the life of the owners thereof. |
20 ጥበብ በጎዳና ትጮኻለች በአደባባይ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች |
20 Wisdom crieth without; she uttereth her voice in the streets: |
21 በአደባባይ ትጣራለች በከተማይቱ መግቢያ በር ቃልን ትናገራለች። |
21 She crieth in the chief place of concourse, in the openings of the gates: in the city she uttereth her words, saying, |
22 እናንተ አላዋቂዎች፥ እስከ መቼ አላዋቂነት ትወድዳላችሁ? ፌዘኞችም ፌዝን ይፈቅዳሉ? ሰነፎችም እውቀትን ይጠላሉ? |
22 How long, ye simple ones, will ye love simplicity? and the scorners delight in their scorning, and fools hate knowledge? |
23 ወደ ዘለፋዬ ተመለሱ እነሆ፥ መንፈሴን አፈስስላችኋለሁ ቃሌን አስተምራችኋለሁ። |
23 Turn you at my reproof: behold, I will pour out my spirit unto you, I will make known my words unto you. |
24 በጠራሁ ጊዜ እምቢ ስላላችሁ፥ እጄን በዘረጋሁ ጊዜ ማንም ስላላስተዋለ፥ |
24 Because I have called, and ye refused; I have stretched out my hand, and no man regarded; |
25 ምክሬን ሁሉ ግን ቸል ስላላችሁ፥ ዘለፋዬንም ስላልፈቀዳችሁ |
25 But ye have set at nought all my counsel, and would none of my reproof: |
26 እኔም ስለዚህ በጥፋታችሁ እስቃለሁ ጥፋታችሁም በመጣ ጊዜ አላግጥባችኋለሁ። |
26 I also will laugh at your calamity; I will mock when your fear cometh; |
27 ድንጋጤ እንደ ጐርፍ በደረሰባችሁ ጊዜ፥ ጥፋታችሁም እንደ ዐውሎ ነፋስ በመጣ ጊዜ፥ ጭንቅና መከራ በወረደባችሁ ጊዜ። |
27 When your fear cometh as desolation, and your destruction cometh as a whirlwind; when distress and anguish cometh upon you. |
28 የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም። |
28 Then shall they call upon me, but I will not answer; they shall seek me early, but they shall not find me: |
29 እውቀትን ጠልተዋልና፥ እግዚአብሔርንም መፍራት አልመረጡምና |
29 For that they hated knowledge, and did not choose the fear of the Lord: |
30 ምክሬን አልፈቀዱምና፥ ዘለፋዬንም ሁሉ ንቀዋልና |
30 They would none of my counsel: they despised all my reproof. |
31 ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ ከራሳቸው ምክር ይጠግባሉ። |
31 Therefore shall they eat of the fruit of their own way, and be filled with their own devices. |
32 አላዋቂዎችን ከጥበብ መራቅ ይገድላቸዋልና፥ ሰነፎችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋልና። |
32 For the turning away of the simple shall slay them, and the prosperity of fools shall destroy them. |
33 የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። |
33 But whoso hearkeneth unto me shall dwell safely, and shall be quiet from fear of evil. |