ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #15
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 15

Genesis 15

1 ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።

1 After these things the word of the Lord came unto Abram in a vision, saying, Fear not, Abram: I am thy shield, and thy exceeding great reward.

2 አብራምም፦ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምንን ትሰጠኛለህ? እኔም ያለ ልጅ እሄዳለሁ የቤቴም መጋቢ የደማስቆ ሰው ይህ ኤሊዔዘር ነው አለ።

2 And Abram said, Lord God, what wilt thou give me, seeing I go childless, and the steward of my house is this Eliezer of Damascus?

3 አብራምም፦ ለእኔ ዘር አልሰጠኸኝም እነሆም፥ በቤቴ የተወለደ ሰው ይወርሰኛል አለ።

3 And Abram said, Behold, to me thou hast given no seed: and, lo, one born in my house is mine heir.

4 እነሆም፥ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፦ ይህ አይወርስህም ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል።

4 And, behold, the word of the Lord came unto him, saying, This shall not be thine heir; but he that shall come forth out of thine own bowels shall be thine heir.

5 ወደ ሜዳም አወጣውና፦ ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠር አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው።

5 And he brought him forth abroad, and said, Look now toward heaven, and tell the stars, if thou be able to number them: and he said unto him, So shall thy seed be.

6 አብራምም በእግዚአብሔር አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።

6 And he believed in the Lord; and he counted it to him for righteousness.

7 ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ አለው።

7 And he said unto him, I am the Lord that brought thee out of Ur of the Chaldees, to give thee this land to inherit it.

8 አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንድወርሳት በምን አውቃለሁ? አለ።

8 And he said, Lord God, whereby shall I know that I shall inherit it?

9 እርሱም፦ የሦስት ዓመት ጊደር፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም ያዝልኝ አለው።

9 And he said unto him, Take me an heifer of three years old, and a she goat of three years old, and a ram of three years old, and a turtledove, and a young pigeon.

10 እነዚህንም ሁሉ ወሰደለት፥ በየሁለትም ከፈላቸው፥ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው ወፎችን ግን አልከፈለም።

10 And he took unto him all these, and divided them in the midst, and laid each piece one against another: but the birds divided he not.

11 አሞራዎችም በሥጋው ላይ ወረዱ፥ አብራምም አበረራቸው።

11 And when the fowls came down upon the carcases, Abram drove them away.

12 ፀሐይም በገባች ጊዜ በአብራም ከባድ እንቅልፍ መጣበት እነሆም፥ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማ ወደቀበት

12 And when the sun was going down, a deep sleep fell upon Abram; and, lo, an horror of great darkness fell upon him.

13 አብራምንም አለው፦ ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ እወቅ ባሪያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።

13 And he said unto Abram, Know of a surety that thy seed shall be a stranger in a land that is not theirs, and shall serve them; and they shall afflict them four hundred years;

14 ደግሞም በባርነት በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ ከዚያም በኋላ በብዙ ከብት ይወጣሉ።

14 And also that nation, whom they shall serve, will I judge: and afterward shall they come out with great substance.

15 አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ በመልካም ሽምግልና ትቀበራለህ።

15 And thou shalt go to thy fathers in peace; thou shalt be buried in a good old age.

16 በአራተኛው ትውልድ ግን ወደዚህ ይመለሳሉ የአሞራውያን ኃጢአት ገና አልተፈጸመምና።

16 But in the fourth generation they shall come hither again: for the iniquity of the Amorites is not yet full.

17 ፀሐይም በገባች ጊዜ ታላቅ ጨለማ ሆነ የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ።

17 And it came to pass, that, when the sun went down, and it was dark, behold a smoking furnace, and a burning lamp that passed between those pieces.

18 በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ። ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ

18 In the same day the Lord made a covenant with Abram, saying, Unto thy seed have I given this land, from the river of Egypt unto the great river, the river Euphrates:

19 ቄናውያንን ቄኔዛውያንንም

19 The Kenites, and the Kenizzites, and the Kadmonites,

20 ቀድሞናውያንንም ኬጢያውያንንም

20 And the Hittites, and the Perizzites, and the Rephaims,

21 ፌርዛውያንንም ራፋይምንም አሞራውያንንም ከነዓናውያንንም ጌርጌሳውያንንም ኢያቡሳውያንንም።

21 And the Amorites, and the Canaanites, and the Girgashites, and the Jebusites.