ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #16
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 16

Genesis 16

1 የአብራም ሚስት ሦራ ግን ለአብራም ልጅ አልወለደችለትም ነበር ስምዋ አጋር የተባለ ግብፃዊት ባሪያም ነበረቻት።

1 Now Sarai Abram’s wife bare him no children: and she had an handmaid, an Egyptian, whose name was Hagar.

2 ሦራም አብራምን፦ እነሆ፥ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ ምናልባት ከእርስዋ በልጅ እታነጽ እንደ ሆነ ወደ እርስዋ ግባ አለችው።

2 And Sarai said unto Abram, Behold now, the Lord hath restrained me from bearing: I pray thee, go in unto my maid; it may be that I may obtain children by her. And Abram hearkened to the voice of Sarai.

3 አብራምም የሦራን ቃል ሰማ። አብራምም በከነዓን ምድር አሥር ዓመት ከተቀመጠ በኋላ፥ የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባሪያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።

3 And Sarai Abram’s wife took Hagar her maid the Egyptian, after Abram had dwelt ten years in the land of Canaan, and gave her to her husband Abram to be his wife.

4 እርሱም ወደ አጋር ገባ፥ አረገዘችም እንዳረገዘችም ባየች ጊዜ እመቤትዋን በዓይንዋ አቃለለች።

4 And he went in unto Hagar, and she conceived: and when she saw that she had conceived, her mistress was despised in her eyes.

5 ሦራም አብራምን፦ መገፋቴ በአንተ ላይ ይሁን እኔ ባሪያዬን በብብትህ ሰጠሁህ እንዳረገዘችም ባየች ጊዜ እኔን በዓይንዋ አቃለለችኝ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ አለችው።

5 And Sarai said unto Abram, My wrong be upon thee: I have given my maid into thy bosom; and when she saw that she had conceived, I was despised in her eyes: the Lord judge between me and thee.

6 አብራምም ሦራን፦ እነሆ ባሪያሽ በእጅሽ ናት እንደ ወደድሽ አድርጊባት አላት። ሦራም ባሠቀየቻት ጊዜ አጋር ከፊትዋ ኮበለለች።

6 But Abram said unto Sarai, Behold, thy maid is in thy hand; do to her as it pleaseth thee. And when Sarai dealt hardly with her, she fled from her face.

7 የእግዚአብሔር መልአክም በውኃ ምንጭ አጠገብ በበረሀ አገኛት ምንጩም ወደ ሱር በምትወስደው መንገድ አጠገብ ነው።

7 And the angel of the Lord found her by a fountain of water in the wilderness, by the fountain in the way to Shur.

8 እርሱም፦ የሦራ ባሪያ አጋር ሆይ፥ ከወዴት መጣሽ? ወዴትስ ትሄጃለሽ? አላት። እርስዋም፦ እኔ ከእመቤቴ ከሦራ የኮበለልሁ ነኝ አለች።

8 And he said, Hagar, Sarai’s maid, whence camest thou? and whither wilt thou go? And she said, I flee from the face of my mistress Sarai.

9 የእግዚአብሔር መልአክም፦ ወደ እመቤትሽ ተመለሺ፥ ከእጅዋም በታች ሆነሽ ተገዥ አላት።

9 And the angel of the Lord said unto her, Return to thy mistress, and submit thyself under her hands.

10 የእግዚአብሔር መልአክም፦ ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፥ ከብዛቱም የተነሣ አይቆጠርም አላት።

10 And the angel of the Lord said unto her, I will multiply thy seed exceedingly, that it shall not be numbered for multitude.

11 የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።

11 And the angel of the Lord said unto her, Behold, thou art with child, and shalt bear a son, and shalt call his name Ishmael; because the Lord hath heard thy affliction.

12 እርሱም የበዳ አህያን የሚመስል ሰው ይሆናል እጁ በሁሉ ላይ ይሆናል፥ የሁሉም እጅ ደግሞ በእርሱ ላይ ይሆናል እርሱም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት ይኖራል።

12 And he will be a wild man; his hand will be against every man, and every man’s hand against him; and he shall dwell in the presence of all his brethren.

13 እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና።

13 And she called the name of the Lord that spake unto her, Thou God seest me: for she said, Have I also here looked after him that seeth me?

14 ስለዚህም የዚያ ጕድጓድ ስም ብኤርለሃይሮኢ ተብሎ ተጠራ እርሱም በቃዴስና በባሬድ መካከል ነው።

14 Wherefore the well was called Beer–lahai–roi; behold, it is between Kadesh and Bered.

15 አጋርም ለአብራም ወንድ ልጅን ወለደችለት አብራምም አጋር የወለደችለትን የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው።

15 And Hagar bare Abram a son: and Abram called his son’s name, which Hagar bare, Ishmael.

16 አጋር እስማኤልን ለአብራም በወለደችለት ጊዜ አብራም የሰማንያ ስድስት ዓመት ሰው ነበረ።

16 And Abram was fourscore and six years old, when Hagar bare Ishmael to Abram.