መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #126
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 126

Psalm 126

1 እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስተኞች ሆንን።

1 When the Lord turned again the captivity of Zion, we were like them that dream.

2 በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን፥ አንደበታችንም ሐሴትን ሞላ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ። እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው ተባለ።

2 Then was our mouth filled with laughter, and our tongue with singing: then said they among the heathen, The Lord hath done great things for them.

3 እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገልን፥ ደስም አለን።

3 The Lord hath done great things for us; whereof we are glad.

4 አቤቱ፥ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ።

4 Turn again our captivity, O Lord, as the streams in the south.

5 በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይለቅማሉ።

5 They that sow in tears shall reap in joy.

6 በሄዱ ጊዜ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ።

6 He that goeth forth and weepeth, bearing precious seed, shall doubtless come again with rejoicing, bringing his sheaves with him.