ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #18
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘሌዋውያን 18

Leviticus 18

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

1 And the Lord spake unto Moses, saying,

2 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

2 Speak unto the children of Israel, and say unto them, I am the Lord your God.

3 እንደ ተቀመጣችሁባት እንደ ግብፅ ምድር ሥራ አትሥሩ እኔም ወደ እርስዋ እንደማገባችሁ እንደ ከነዓን ምድር ሥራ አትሥሩ በሥርዓታቸውም አትሂዱ።

3 After the doings of the land of Egypt, wherein ye dwelt, shall ye not do: and after the doings of the land of Canaan, whither I bring you, shall ye not do: neither shall ye walk in their ordinances.

4 ፍርዴን አድርጉ፥ በእርስዋም ትሄዱ ዘንድ ሥርዓቴን ጠብቁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

4 Ye shall do my judgments, and keep mine ordinances, to walk therein: I am the Lord your God.

5 የሚሠራቸው ሰው በእነርሱ በሕይወት ይኖራልና ሥርዓቴንና ፍርዴን ጠብቁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

5 Ye shall therefore keep my statutes, and my judgments: which if a man do, he shall live in them: I am the Lord.

6 ከእናንተም ማንም ሰው ኃፍረተ ሥጋውን ይገልጥ ዘንድ ወደ ዘመዱ ሁሉ አይቅረብ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

6 None of you shall approach to any that is near of kin to him, to uncover their nakedness: I am the Lord.

7 የአባትህን ኃፍረተ ሥጋና የእናትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ እናትህ ናት ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።

7 The nakedness of thy father, or the nakedness of thy mother, shalt thou not uncover: she is thy mother; thou shalt not uncover her nakedness.

8 የአባትህን ሚስት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ የአባትህን ኃፍረተ ሥጋ ነው።

8 The nakedness of thy father’s wife shalt thou not uncover: it is thy father’s nakedness.

9 የእኅትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ፥ በቤት ወይም በውጭ የተወለደች ብትሆን፥ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።

9 The nakedness of thy sister, the daughter of thy father, or daughter of thy mother, whether she be born at home, or born abroad, even their nakedness thou shalt not uncover.

10 የወንድ ልጅህን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ወይም የሴት ልጅህን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ የአንተ ኃፍረተ ሥጋ ነውና።

10 The nakedness of thy son’s daughter, or of thy daughter’s daughter, even their nakedness thou shalt not uncover: for theirs is thine own nakedness.

11 ከአባትህ የተወለደችውን የአባትህን ሚስት ልጅ ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ እህትህ ናት ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።

11 The nakedness of thy father’s wife’s daughter, begotten of thy father, she is thy sister, thou shalt not uncover her nakedness.

12 የአባትህን እኅት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ የአባትህ ዘመድ ናት።

12 Thou shalt not uncover the nakedness of thy father’s sister: she is thy father’s near kinswoman.

13 የእናትህን እኅት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ የእናትህ ዘመድ ናት።

13 Thou shalt not uncover the nakedness of thy mother’s sister: for she is thy mother’s near kinswoman.

14 የአባትህን ወንድም ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፥ ወደ ሚስቱም አትቅረብ የአጎትህ ሚስት ናት።

14 Thou shalt not uncover the nakedness of thy father’s brother, thou shalt not approach to his wife: she is thine aunt.

15 የምራትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ የልጅህ ሚስት ናት ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።

15 Thou shalt not uncover the nakedness of thy daughter in law: she is thy son’s wife; thou shalt not uncover her nakedness.

16 የወንድምህን ሚስት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ የወንድምህ ኃፍረተ ሥጋ ነው።

16 Thou shalt not uncover the nakedness of thy brother’s wife: it is thy brother’s nakedness.

17 የሴትንና የሴት ልጅዋን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ የወንድ ልጅዋን ሴት ልጅ ወይም የሴት ልጅዋን ሴት ልጅ ኃፍረተ ሥጋዋን ትግለጥ ዘንድ አታግባ ዘመዶች ናቸው ዝሙት ነው።

17 Thou shalt not uncover the nakedness of a woman and her daughter, neither shalt thou take her son’s daughter, or her daughter’s daughter, to uncover her nakedness; for they are her near kinswomen: it is wickedness.

18 ሚስትህ በሕይወት ሳለች እኅትዋ ጣውንትዋ እንዳትሆን፥ ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ ከእርስዋ ጋር እኅትዋን አታግባ።

18 Neither shalt thou take a wife to her sister, to vex her, to uncover her nakedness, beside the other in her life time.

19 እርስዋም በመርገምዋ ርኵሰት ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ ወደ ሴት አትቅረብ።

19 Also thou shalt not approach unto a woman to uncover her nakedness, as long as she is put apart for her uncleanness.

20 እንዳትረክስባትም ከባልንጀራህ ሚስት ጋር አትተኛ።

20 Moreover thou shalt not lie carnally with thy neighbour’s wife, to defile thyself with her.

21 ከዘርህም ለሞሎክ በእሳት አሳልፈህ አትስጥ፥ የአምላክህንም ስም አታርክስ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

21 And thou shalt not let any of thy seed pass through the fire to Molech, neither shalt thou profane the name of thy God: I am the Lord.

22 ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ ጸያፍ ነገር ነውና።

22 Thou shalt not lie with mankind, as with womankind: it is abomination.

23 እንዳትረክስባትም ከእንሰሳ ጋር አትተኛ ሴት ከእርሱ ጋር ትተኛ ዘንድ በእንስሳ ፊት አትቁም የተጠላ ነገር ነውና።

23 Neither shalt thou lie with any beast to defile thyself therewith: neither shall any woman stand before a beast to lie down thereto: it is confusion.

24 በእነዚህ ሁሉ ከፊታችሁ የማሳድዳቸው አሕዛብ ረክሰዋልና በእነዚህ ነገሮች ሁሉ አትርከሱ።

24 Defile not ye yourselves in any of these things: for in all these the nations are defiled which I cast out before you:

25 ምድሪቱም ረከሰች ስለዚህ ኃጢአትዋን በእርስዋ ላይ እመልሳለሁ፥ ምድሪቱም የሚኖሩባትን ሰዎች ትተፋለች።

25 And the land is defiled: therefore I do visit the iniquity thereof upon it, and the land itself vomiteth out her inhabitants.

26 ሥርዓቴንና ፍርዴን ጠብቁ እናንተም የአገሩ ልጆች በእናንተም መካከል የሚኖሩት እንግዶች ከዚህ ርኵሰት ምንም አትሥሩ

26 Ye shall therefore keep my statutes and my judgments, and shall not commit any of these abominations; neither any of your own nation, nor any stranger that sojourneth among you:

27 ከእናንተ በፊት የነበሩ የአገሩ ልጆች ይህን ርኵሰት ሁሉ ሠርተዋልና፥ ምድሪቱም ረክሳለችና

27 (For all these abominations have the men of the land done, which were before you, and the land is defiled;)

28 ባረከሳችኋት ጊዜ ምድሪቱ ከእናንተ በፊት የነበረውን ሕዝብ እንደ ተፋች እናንተን እንዳትተፋችሁ።

28 That the land spue not you out also, when ye defile it, as it spued out the nations that were before you.

29 ከዚህ ርኵሰት ሁሉ ማናቸውን የሚያደርግ ያ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋልና።

29 For whosoever shall commit any of these abominations, even the souls that commit them shall be cut off from among their people.

30 ስለዚህ ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎች የሠሩትን ጸያፍ የሆነውን ወግ ሁሉ እንዳትሠሩ፥ በእርሱም እንዳትረክሱ ሥርዓቴን ጠብቁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

30 Therefore shall ye keep mine ordinance, that ye commit not any one of these abominable customs, which were committed before you, and that ye defile not yourselves therein: I am the Lord your God.