ኦሪት ዘዳግም Orit ZeDaGim
Deuteronomy / Devarim #17
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘዳግም 17 |
Deuteronomy 17 |
1 በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነውና ነውር ወይም ክፉ ነገር ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ። |
1 Thou shalt not sacrifice unto the Lord thy God any bullock, or sheep, wherein is blemish, or any evilfavouredness: for that is an abomination unto the Lord thy God. |
2 አምላክህ እግዚአብሔር ከሰጠህ ከአገርህ ደጆች በማንኛይቱም ውስጥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን ቃል ኪዳኑን በማፍረስ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ክፋት የሠራ ቢገኝ፥ |
2 If there be found among you, within any of thy gates which the Lord thy God giveth thee, man or woman, that hath wrought wickedness in the sight of the Lord thy God, in transgressing his covenant, |
3 ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ፥ እኔ ላላዘዝኋቸው ለፀሐይና ለጨረቃ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የሰገደ ቢገኝ፥ |
3 And hath gone and served other gods, and worshipped them, either the sun, or moon, or any of the host of heaven, which I have not commanded; |
4 ቢያወሩልህም ብትሰማም፥ ያንን ፈጽመህ መርምር እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ እርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥ |
4 And it be told thee, and thou hast heard of it, and enquired diligently, and, behold, it be true, and the thing certain, that such abomination is wrought in Israel: |
5 ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ። |
5 Then shalt thou bring forth that man or that woman, which have committed that wicked thing, unto thy gates, even that man or that woman, and shalt stone them with stones, till they die. |
6 በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች አፍ ሞት የሚገባው ይገደል በአንድ ምስክር አፍ አይገደል። |
6 At the mouth of two witnesses, or three witnesses, shall he that is worthy of death be put to death; but at the mouth of one witness he shall not be put to death. |
7 እርሱን ለመግደል በመጀመሪያ የምስክሮች እጅ በኋላም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ትሁንበት እንዲሁም ክፋቱን ከመካከልህ አስወግድ። |
7 The hands of the witnesses shall be first upon him to put him to death, and afterward the hands of all the people. So thou shalt put the evil away from among you. |
8 በደምና በደም፥ በፍርድና በፍርድ፥ በመቍሰልና በመቍሰል መካከል በአገርህ ደጅ ውስጥ ሰዎች ስለሚከራከሩበት ክርክር የሚሳንህ የፍርድ ነገር ቢነሣ፥ አንተ ተነሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ትወጣለህ |
8 If there arise a matter too hard for thee in judgment, between blood and blood, between plea and plea, and between stroke and stroke, being matters of controversy within thy gates: then shalt thou arise, and get thee up into the place which the Lord thy God shall choose; |
9 ወደ ሌዋውያን ካህናት በዚያም ዘመን ወደ ተሾመው ፈራጅ መጥተህ ትጠይቃለህ እነርሱም የፍርዱን ነገር ይነግሩሃል። |
9 And thou shalt come unto the priests the Levites, and unto the judge that shall be in those days, and enquire; and they shall shew thee the sentence of judgment: |
10 እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ የነገሩህን የፍርድ ነገር ታደርጋለህ እንዳስተማሩህም ታደርግ ዘንድ ጠብቅ። |
10 And thou shalt do according to the sentence, which they of that place which the Lord shall choose shall shew thee; and thou shalt observe to do according to all that they inform thee: |
11 እንዳስተማሩህም ሕግ፥ እንደ ነገሩህም ፍርድ አድርግ ከነገሩህ ፍርድ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል። |
11 According to the sentence of the law which they shall teach thee, and according to the judgment which they shall tell thee, thou shalt do: thou shalt not decline from the sentence which they shall shew thee, to the right hand, nor to the left. |
12 ማናቸውም ሰው ቢኰራ፥ በዚያም አምላክህን እግዚአብሔርን ለማገልገል የሚቆመውን ካህኑን ወይም ፈራጁን ለመስማት ባይወድድ፥ ያ ሰው ይሙት፥ ከእስራኤልም ዘንድ ክፋትን አስወግድ |
12 And the man that will do presumptuously, and will not hearken unto the priest that standeth to minister there before the Lord thy God, or unto the judge, even that man shall die: and thou shalt put away the evil from Israel. |
13 ሕዝቡም ሁሉ ሰምቶ ይፈራል፥ ከዚያም ወዲያ አይኰራም። |
13 And all the people shall hear, and fear, and do no more presumptuously. |
14 አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በተቀመጥህባትም ጊዜ። በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ በላዬ ንጉሥ አነግሣለሁ ስትል፥ |
14 When thou art come unto the land which the Lord thy God giveth thee, and shalt possess it, and shalt dwell therein, and shalt say, I will set a king over me, like as all the nations that are about me; |
15 አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን በላይህ ታነግሣለህ ከወንድሞችህ መካከል የሆነውን በአንተ ላይ ንጉሥ ታነግሣለህ ወንድምህ ያልሆነውን ከሌላ ወገን ሰው በላይህ ንጉሥ ታደርግ ዘንድ አይገባህም። |
15 Thou shalt in any wise set him king over thee, whom the Lord thy God shall choose: one from among thy brethren shalt thou set king over thee: thou mayest not set a stranger over thee, which is not thy brother. |
16 ነገር ግን ለእርሱ ፈረሶችን አያበዛም እግዚአብሔር፦ በዚያ መንገድ ደግማችሁ አትመለሱም ብሎአችኋልና ፈረሶችን ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብፅ አይመልስም። |
16 But he shall not multiply horses to himself, nor cause the people to return to Egypt, to the end that he should multiply horses: forasmuch as the Lord hath said unto you, Ye shall henceforth return no more that way. |
17 ልቡም እንዳይስት ሚስቶችን ለእርሱ አያበዛም ወርቅና ብርም ለእርሱ እጅግ አያበዛም። |
17 Neither shall he multiply wives to himself, that his heart turn not away: neither shall he greatly multiply to himself silver and gold. |
18 በመንግሥቱም ዙፋን በተቀመጠ ጊዜ ከሌዋውያን ካህናት ወስዶ ይህን ሕግ ለራሱ በመጽሐፍ ይጻፍ። |
18 And it shall be, when he sitteth upon the throne of his kingdom, that he shall write him a copy of this law in a book out of that which is before the priests the Levites: |
19-21 አምላኩን እግዚአብሔርን መፍራት ይማር ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ ይህችንም ሥርዓት ጠብቆ ያደርግ ዘንድ፥ ልቡ በወንድሞቹ ላይ እንዳይኰራ ከትእዛዙም ቀኝና ግራ እንዳይል፥ እርሱም ልጆቹም በእስራኤል ልጆች መካከል ረጅም ዘመን ይነግሡ ዘንድ መጽሐፉ ከእርሱ ጋር ይኑር፥ ዕድሜውንም ሁሉ ያንብበው። |
19 And it shall be with him, and he shall read therein all the days of his life: that he may learn to fear the Lord his God, to keep all the words of this law and these statutes, to do them: |