መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #32
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 32 |
Ps 32 |
1 መተላለፉ የቀረችለት ኃጢአቱም የተከደነችለት ምስጉን ነው። |
1 Blessed is he whose transgression is forgiven, whose sin is covered. |
2 እግዚአብሔር በደልን የማይቈጥርበት በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው ምስጉን ነው። |
2 Blessed is the man unto whom the Lord imputeth not iniquity, and in whose spirit there is no guile. |
3 ሁልጊዜ ከመጮኼ የተነሣ ዝም ባልሁ ጊዜ አጥንቶቼ ተበላሹ |
3 When I kept silence, my bones waxed old through my roaring all the day long. |
4 በቀንና በሌሊት እጅህ ከብዳብኛለችና፥ እርጥበቴም ለበጋ ትኵሳት ተለወጠ። |
4 For day and night thy hand was heavy upon me: my moisture is turned into the drought of summer. Selah. |
5 ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፥ በደሌንም አልሸፈንሁም ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውህልኝ። |
5 I acknowledged my sin unto thee, and mine iniquity have I not hid. I said, I will confess my transgressions unto the Lord; and thou forgavest the iniquity of my sin. Selah. |
6 ስለዚህ ቅዱስ ሁሉ በምቹ ጊዜ ወደ አንተ ይለምናል ብዙ የጥፋት ውኃም ወደ እርሱ አይቀርብም። |
6 For this shall every one that is godly pray unto thee in a time when thou mayest be found: surely in the floods of great waters they shall not come nigh unto him. |
7 አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነህ፥ ከጣርም ትጠብቀኛለህ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ። |
7 Thou art my hiding place; thou shalt preserve me from trouble; thou shalt compass me about with songs of deliverance. Selah. |
8 አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ። |
8 I will instruct thee and teach thee in the way which thou shalt go: I will guide thee with mine eye. |
9 ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጕሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ። |
9 Be ye not as the horse, or as the mule, which have no understanding: whose mouth must be held in with bit and bridle, lest they come near unto thee. |
10 በኃጢአተኛ ብዙ መቅሠፍት አለበት በእግዚአብሔር የሚታመነውን ግን ምሕረት ይከብበዋል። |
10 Many sorrows shall be to the wicked: but he that trusteth in the Lord, mercy shall compass him about. |
11 ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ |
11 Be glad in the Lord, and rejoice, ye righteous: and shout for joy, all ye that are upright in heart. |