ኦሪት ዘዳግም Orit ZeDaGim
Deuteronomy / Devarim #16
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘዳግም 16 |
Deuteronomy 16 |
1 በአቢብ ወር አምላክህ እግዚአብሔር በሌሊት ከግብፅ ስላወጣህ የአቢብን ወር ጠብቅ፥ የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ፋሲካ አድርግበት። |
1 Observe the month of Abib, and keep the passover unto the Lord thy God: for in the month of Abib the Lord thy God brought thee forth out of Egypt by night. |
2 አምላክህ እግዚአብሔር በዚያ ስሙ ይጠራበት ዘንድ በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ከበግና ከላም መንጋ ፋሲካ ሠዋ። |
2 Thou shalt therefore sacrifice the passover unto the Lord thy God, of the flock and the herd, in the place which the Lord shall choose to place his name there. |
3 የቦካውን እንጀራ ከእርሱ ጋር አትብላ ከግብፅ አገር በችኰላ ስለ ወጣህ ከግብፅ አገር የወጣህበትን ቀን በዕድሜህ ሁሉ ታስብ ዘንድ የመከራን እንጀራ፥ ቂጣ እንጀራ፥ ሰባት ቀን ከእርሱ ጋር ብላ። |
3 Thou shalt eat no leavened bread with it; seven days shalt thou eat unleavened bread therewith, even the bread of affliction; for thou camest forth out of the land of Egypt in haste: that thou mayest remember the day when thou camest forth out of the land of Egypt all the days of thy life. |
4 ሰባት ቀንም በአገርህ ሁሉ እርሾ አይታይም በመጀመሪያው ቀን ማታ ከሠዋኸው ሥጋ እስከ ነገ ድረስ ምንም አይደር። |
4 And there shall be no leavened bread seen with thee in all thy coast seven days; neither shall there any thing of the flesh, which thou sacrificedst the first day at even, remain all night until the morning. |
5 አምላክህ እግዚአብሔር ከሰጠህ ከአገርህ ደጆች በማንኛይቱም ፋሲካን ትሠዋ ዘንድ አይገባህም። |
5 Thou mayest not sacrifice the passover within any of thy gates, which the Lord thy God giveth thee: |
6 ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ስሙ ይጠራበት ዘንድ በመረጠው በዚያ ስፍራ ከግብፅ በወጣህበት ወራት፥ ፀሐይ ሲገባ፥ ማታ ፋሲካን ሠዋ። |
6 But at the place which the Lord thy God shall choose to place his name in, there thou shalt sacrifice the passover at even, at the going down of the sun, at the season that thou camest forth out of Egypt. |
7 አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ታበስለዋለህ፥ ትበላውማለህ በነጋውም ተነሥተህ ወደ ድንኳንህ ትሄዳለህ። |
7 And thou shalt roast and eat it in the place which the Lord thy God shall choose: and thou shalt turn in the morning, and go unto thy tents. |
8 ስድስት ቀን ቂጣ እንጀራ ብላ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ጉባኤ ይሁን ሥራን ሁሉ አታድርግበት። |
8 Six days thou shalt eat unleavened bread: and on the seventh day shall be a solemn assembly to the Lord thy God: thou shalt do no work therein. |
9 ሰባት ሳምንትም ትቈጥራለህ መከሩን ማጨድ ከምትጀምርበት ቀን ጀምሮ ሰባት ሳምንት መቍጠር ትጀምራለህ። |
9 Seven weeks shalt thou number unto thee: begin to number the seven weeks from such time as thou beginnest to put the sickle to the corn. |
10 አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ መጠን በፈቃድህ የምታቀርበውን አምጥተህ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሰባቱ ሱባዔ በዓል ታደርጋለህ። |
10 And thou shalt keep the feast of weeks unto the Lord thy God with a tribute of a freewill offering of thine hand, which thou shalt give unto the Lord thy God, according as the Lord thy God hath blessed thee: |
11 አንተ፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ፥ በአገርህም ደጅ ውስጥ ያለው ሌዋዊ፥ በመካከልህም ያሉት መጻተኛና ድሀ አደግ መበለትም አምላክህ እግዚአብሔር በዚያ ስሙ ይጠራበት ዘንድ በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ። |
11 And thou shalt rejoice before the Lord thy God, thou, and thy son, and thy daughter, and thy manservant, and thy maidservant, and the Levite that is within thy gates, and the stranger, and the fatherless, and the widow, that are among you, in the place which the Lord thy God hath chosen to place his name there. |
12 አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ አስብ ይህንንም ሥርዓት ጠብቅ፥ አድርገውም። |
12 And thou shalt remember that thou wast a bondman in Egypt: and thou shalt observe and do these statutes. |
13 ከአውድማህና ከመጥመቂያህ ፍሬህን በሰበሰብህ ጊዜ የዳስ በዓል ሰባትን ቀን ትጠብቃለህ። |
13 Thou shalt observe the feast of tabernacles seven days, after that thou hast gathered in thy corn and thy wine: |
14 አንተም፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ፥ በአገርህም ደጅ ውስጥ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፥ ድሀ አደግና መበለትም በበዓል ደስ ይበላችሁ። |
14 And thou shalt rejoice in thy feast, thou, and thy son, and thy daughter, and thy manservant, and thy maidservant, and the Levite, the stranger, and the fatherless, and the widow, that are within thy gates. |
15 አምላክህ እግዚአብሔር በፍሬህ ሁሉ በእጅህም ሥራ ሁሉ ይባርክሃልና እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰባት ቀን በዓል ታደርጋለህ አንተም ፈጽሞ ደስ ይልሃል። |
15 Seven days shalt thou keep a solemn feast unto the Lord thy God in the place which the Lord shall choose: because the Lord thy God shall bless thee in all thine increase, and in all the works of thine hands, therefore thou shalt surely rejoice. |
16 በዓመት ሦስት ጊዜ፥ በቂጣ በዓል፥ በሰባቱ ሱባዔም በዓል፥ በዳስም በዓል ወንዶችህ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እርሱ በመረጠው ስፍራ ይታዩ በእግዚአብሔርም ፊት ባዶ እጃቸውን አይታዩ። |
16 Three times in a year shall all thy males appear before the Lord thy God in the place which he shall choose; in the feast of unleavened bread, and in the feast of weeks, and in the feast of tabernacles: and they shall not appear before the Lord empty: |
17 አምላክህ እግዚአብሔር በረከት እንደ ሰጠህ መጠን እያንዳንዱ ሰው እንደ ችሎታው ይስጥ። |
17 Every man shall give as he is able, according to the blessing of the Lord thy God which he hath given thee. |
18 አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በአገርህ ደጅ ሁሉ በየነገዶችህ ፈራጆችንና አለቆችን ሹም ለሕዝቡም ቅን ፍርድ ይፍረዱ። |
18 Judges and officers shalt thou make thee in all thy gates, which the Lord thy God giveth thee, throughout thy tribes: and they shall judge the people with just judgment. |
19 ፍርድን አታጣምም ፊት አይተህም አታድላ ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና ጉቦ አትቀበል። |
19 Thou shalt not wrest judgment; thou shalt not respect persons, neither take a gift: for a gift doth blind the eyes of the wise, and pervert the words of the righteous. |
20 በሕይወት ትኖር ዘንድ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም የሚሰጥህን ምድር ትወርስ ዘንድ እውነተኛውን ፍርድ ተከተል። |
20 That which is altogether just shalt thou follow, that thou mayest live, and inherit the land which the Lord thy God giveth thee. |
21 ለአንተ በምትሠራው በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ አጠገብ ከማናቸውም ዛፍ የማምለኪያ ዐፀድ አድርገህ አትትከል። |
21 Thou shalt not plant thee a grove of any trees near unto the altar of the Lord thy God, which thou shalt make thee. |
22 አምላክህ እግዚአብሔርም የሚጠላውን ሐውልት ለአንተ አታቁም። |
22 Neither shalt thou set thee up any image; which the Lord thy God hateth. |