መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #113
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 113

Psalm 113

1 ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት፥ የእግዚአብሔርንም ስም አመስግኑ።

1 Praise ye the Lord. Praise, O ye servants of the Lord, praise the name of the Lord.

2 ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ የእግዚአብሔር ስም ቡሩክ ይሁን።

2 Blessed be the name of the Lord from this time forth and for evermore.

3 ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን።

3 From the rising of the sun unto the going down of the same the Lord’s name is to be praised.

4 እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍተኛ ነው፥ ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።

4 The Lord is high above all nations, and his glory above the heavens.

5 እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ማን ነው? በላይ የሚኖር

5 Who is like unto the Lord our God, who dwelleth on high,

6 በሰማይና በምድር የተዋረዱትን የሚያይ

6 Who humbleth himself to behold the things that are in heaven, and in the earth!

7-8 ከአለቆች ጋር ከሕዝቡም አለቆች ጋር ያኖረው ዘንድ ችግረኛን ከመሬት የሚያነሣ፥ ምስኪኑንም ከፋንድያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ

7 He raiseth up the poor out of the dust, and lifteth the needy out of the dunghill;
8 That he may set him with princes, even with the princes of his people.

9 መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት። ሃሌ ሉያ።

9 He maketh the barren woman to keep house, and to be a joyful mother of children. Praise ye the Lord.