መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #42
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 42 |
Ps 42 |
1 ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። |
1 As the hart panteth after the water brooks, so panteth my soul after thee, O God. |
2 ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ? |
2 My soul thirsteth for God, for the living God: when shall I come and appear before God? |
3 ዘወትር። አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ። |
3 My tears have been my meat day and night, while they continually say unto me, Where is thy God? |
4 ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና በዓል የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ። |
4 When I remember these things, I pour out my soul in me: for I had gone with the multitude, I went with them to the house of God, with the voice of joy and praise, with a multitude that kept holyday. |
5 ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ። |
5 Why art thou cast down, O my soul? and why art thou disquieted in me? hope thou in God: for I shall yet praise him for the help of his countenance. |
6 አምላኬ ሆይ፥ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወከች ስለዚህ በዮርዳኖስ ምድር በአርሞንኤምም በታናሹ ተራራ አስብሃለሁ። |
6 O my God, my soul is cast down within me: therefore will I remember thee from the land of Jordan, and of the Hermonites, from the hill Mizar. |
7 በፍዋፍዋቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራታለች ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ። |
7 Deep calleth unto deep at the noise of thy waterspouts: all thy waves and thy billows are gone over me. |
8 እግዚአብሔር በቀን ቸርነቱን ያዝዛል፥ በሌሊትም ዝማሬው በእኔ ዘንድ ይሆናል የእኔ ስእለት ለሕይወቴ አምላክ ነው። |
8 Yet the Lord will command his lovingkindness in the daytime, and in the night his song shall be with me, and my prayer unto the God of my life. |
9 እግዚአብሔርን፦ አንተ መጠጊያዬ ነህ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ? እለዋለሁ። |
9 I will say unto God my rock, Why hast thou forgotten me? why go I mourning because of the oppression of the enemy? |
10 ጠላቶቼ ሁልጊዜ። አምላክህ ወዴት ነው? ባሉኝ ጊዜ አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ። |
10 As with a sword in my bones, mine enemies reproach me; while they say daily unto me, Where is thy God? |
11 ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ። |
11 Why art thou cast down, O my soul? and why art thou disquieted within me? hope thou in God: for I shall yet praise him, who is the health of my countenance, and my God. |