ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #29
In Amharic and English
ኦሪት ዘፍጥረት 29 |
Genesis 29 |
1 ያዕቆብም ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሰዎች አገር ሄደ። |
1 Then Jacob went on his journey, and came into the land of the people of the east. |
2 በሜዳውም እነሆ ጕድጓድን አየ፥ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በላዩ ተመስገው ነበር ከዚያ ጕድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና በጕድጓዱም አፍ የነበረው ድንጋይ ትልቅ ነበረ። |
2 And he looked, and behold a well in the field, and, lo, there were three flocks of sheep lying by it; for out of that well they watered the flocks: and a great stone was upon the well’s mouth. |
3 መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተከማቹ ጊዜ ድንጋዩን ከጕድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር ድንጋዩንም ወደ ስፍራው መልሰው በጕድጓዱ አፍ እንደ ገና ይገጥሙት ነበር። |
3 And thither were all the flocks gathered: and they rolled the stone from the well’s mouth, and watered the sheep, and put the stone again upon the well’s mouth in his place. |
4 ያዕቆብም። ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንት የወዴት ናችሁ? አላቸው። እርሱም፦ እኛ የካራን ነን አሉት። |
4 And Jacob said unto them, My brethren, whence be ye? And they said, Of Haran are we. |
5 የናኮርን ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን? አላቸው። እርሱም፦ እናውቀዋለን አሉት። |
5 And he said unto them, Know ye Laban the son of Nahor? And they said, We know him. |
6 እርሱ። ደኅና ነውን? አላቸው። እርሱም፦ አዎን ደኅና ነው አሁንም ልጁ ራሔል ከበጎች ጋር መጣች አሉት። |
6 And he said unto them, Is he well? And they said, He is well: and, behold, Rachel his daughter cometh with the sheep. |
7 እርሱም፦ ቀኑ ገና ቀትር ነው፥ ከብቶቹ የሚከማቹበት ሰዓቱም ገና አልደረሰም አሁንም በጎቹን አጠጡና ሄዳችሁ አሰማሩአቸው አላቸው። |
7 And he said, Lo, it is yet high day, neither is it time that the cattle should be gathered together: water ye the sheep, and go and feed them. |
8 እነርሱም አሉ፦ መንጎች ሁሉ እስኪከማቹና ድንጋዩን ከጕድጓዱ አፍ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን። |
8 And they said, We cannot, until all the flocks be gathered together, and till they roll the stone from the well’s mouth; then we water the sheep. |
9 እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ የላባ ልጅ ራሔል ከአባትዋ በጎች ጋር ደረሰች እርስዋ የአባትዋን በጎች ትጠብቅ ነበርና። |
9 And while he yet spake with them, Rachel came with her father’s sheep: for she kept them. |
10 ያዕቆብም የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የእጎቱን የላባን በጎች ባየ ጊዜ፥ ቀረበ ከጕድጓዱም አፍ ድንጋዩን ገለበጠ፥ የአጎቱን የላባን በጎችንም አጠጣ። |
10 And it came to pass, when Jacob saw Rachel the daughter of Laban his mother’s brother, and the sheep of Laban his mother’s brother, that Jacob went near, and rolled the stone from the well’s mouth, and watered the flock of Laban his mother’s brother. |
11 ያዕቆብም ራሔልን ሳማት፥ ቃሉንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ። |
11 And Jacob kissed Rachel, and lifted up his voice, and wept. |
12 ያዕቆብም የአባትዋ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ለራሔል አስታወቃት እርስዋም ሮጣ ሄዳ ለአባትዋ ይህን ነገር ነገረችው። |
12 And Jacob told Rachel that he was her father’s brother, and that he was Rebekah’s son: and she ran and told her father. |
13 ላባም የእኅቱን ልጅ የያዕቆብን ወሬ በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ሮጠ፥ አቅፎም ሳመው፥ ወደ ቤቱም አገባው። ነገሩንም ሁሉ ለላባ ነገረው። |
13 And it came to pass, when Laban heard the tidings of Jacob his sister’s son, that he ran to meet him, and embraced him, and kissed him, and brought him to his house. And he told Laban all these things. |
14 ላባም። በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ። |
14 And Laban said to him, Surely thou art my bone and my flesh. And he abode with him the space of a month. |
15 ላባም ያዕቆብን፦ ወንድሜ ስለሆንህ በከንቱ ታገለግለኛለህን? ምንዳህ ምንድር ነው? ንገረኝ አለው። |
15 And Laban said unto Jacob, Because thou art my brother, shouldest thou therefore serve me for nought? tell me, what shall thy wages be? |
16 ለላባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት የታላቂቱ ስም ልያ የታናሺቱ ስም ራሔል ነበረ። |
16 And Laban had two daughters: the name of the elder was Leah, and the name of the younger was Rachel. |
17 ልያም ዓይነ ልም ነበረች ራሔል ግን መልከ መልካም ነበረች ፊትዋም ውብ ነበረ። |
17 Leah was tender eyed; but Rachel was beautiful and well favoured. |
18 ያዕቆብም ራሔልን ወደደእንዲህም አለ፦ ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገዛልሃለሁ። |
18 And Jacob loved Rachel; and said, I will serve thee seven years for Rachel thy younger daughter. |
19 ላባም። ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለአንተ ብሰጣት ይሻላል ከእኔ ጋር ተቀመጥ አለ። |
19 And Laban said, It is better that I give her to thee, than that I should give her to another man: abide with me. |
20 ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት። |
20 And Jacob served seven years for Rachel; and they seemed unto him but a few days, for the love he had to her. |
21 ያዕቆብም ላባን፦ ወደ እርስዋ እገባ ዘንድ ሚስቴን ስጠኝ፥ ቀኔ ተፈጽሞአልና አለው። |
21 And Jacob said unto Laban, Give me my wife, for my days are fulfilled, that I may go in unto her. |
22 ላባም የዚያን ስፍራ ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፥ ሰርግም አደረገ። |
22 And Laban gathered together all the men of the place, and made a feast. |
23 በመሸም ጊዜ ልጁን ልያን ወስዶ ለያዕቆብ አገባለት ያዕቆብም ወደ እርስዋ ገባ። |
23 And it came to pass in the evening, that he took Leah his daughter, and brought her to him; and he went in unto her. |
24 ላባም ለልጁ ለልያ ባሪያይቱን ዘለፋን ባርያ ትሆናት ዘንድ ሰጣት። |
24 And Laban gave unto his daughter Leah Zilpah his maid for an handmaid. |
25 በነጋም ጊዜ እነሆ ልያ ሆና ተገኘች ላባንም። ምነው እንደዚህ አደረግህብኝ? ያገለገልሁህ ስለ ራሔል አልነበረምን? ለምን አታለልኸኝ? አለው። |
25 And it came to pass, that in the morning, behold, it was Leah: and he said to Laban, What is this thou hast done unto me? did not I serve with thee for Rachel? wherefore then hast thou beguiled me? |
26 ላባም እንዲህ አለ፦ በአገራችን ታላቂቱ ሳለች፥ ታናሺቱን እንሰጥ ዘንድ ወግ አይደለም |
26 And Laban said, It must not be so done in our country, to give the younger before the firstborn. |
27 ይህችንም ሳምንት ፈጽም ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ። |
27 Fulfil her week, and we will give thee this also for the service which thou shalt serve with me yet seven other years. |
28 ያዕቆብም እንዲህ አደረገ፥ ይህችንም ሳምንት ፈጸመ ልጁን ራሔልንም ለእርሱ ሚስት ትሆን ዘንድ ሰጠው። |
28 And Jacob did so, and fulfilled her week: and he gave him Rachel his daughter to wife also. |
29 ላባም ለልጁ ለራሔል ባርያይቱን ባላን ባርያ ትሆናት ዘንድ ሰጣት። |
29 And Laban gave to Rachel his daughter Bilhah his handmaid to be her maid. |
30 ያዕቆብም ወደ ራሔል ደግሞ ገባ። ራሔልንም ከልያ ይልቅ ወደዳት ሌላ ሰባት ዓመትም ተገዛለት። |
30 And he went in also unto Rachel, and he loved also Rachel more than Leah, and served with him yet seven other years. |
31 እግዚአብሔርም ልያ የተጠላች መሆንዋን ባየ ጊዜ ማኅፀንዋን ከፈተላት ራሔል ግን መካን ነበረች። |
31 And when the Lord saw that Leah was hated, he opened her womb: but Rachel was barren. |
32 ልያም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው እግዚአብሔር መከራዬን አይቶአልና፥ እንግዲህም ወዲህ ባሌ ይወድደኛል ብላለችና። |
32 And Leah conceived, and bare a son, and she called his name Reuben: for she said, Surely the Lord hath looked upon my affliction; now therefore my husband will love me. |
33 ደግሞም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ሰማ ይህን ደገመኝ አለች ስሙንም ስምዖን ብላ ጠራችው። |
33 And she conceived again, and bare a son; and said, Because the Lord hath heard that I was hated, he hath therefore given me this son also: and she called his name Simeon. |
34 ደግሞም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች አሁንም ባሌ ወደ እኔ ይጠጋል፥ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች ስለዚህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራችው። |
34 And she conceived again, and bare a son; and said, Now this time will my husband be joined unto me, because I have born him three sons: therefore was his name called Levi. |
35 ደግሞም ፀነስች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለች ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች። |
35 And she conceived again, and bare a son: and she said, Now will I praise the Lord: therefore she called his name Judah; and left bearing. |