ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #30
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 30

Genesis 30

1 ራሔልም ለያዕቆብ ልጆችን እንዳልወለደች ባየች ጊዜ በእኅትዋ ቀናችባት ያቆብንም። ልጅ ስጠኝ ይህስ ካልሆነ እሞታለሁ አለችው።

1 And when Rachel saw that she bare Jacob no children, Rachel envied her sister; and said unto Jacob, Give me children, or else I die.

2 ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ። በውኑ እኔ የሆድን ፍሬ በነሣሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን? አላት።

2 And Jacob’s anger was kindled against Rachel: and he said, Am I in God’s stead, who hath withheld from thee the fruit of the womb?

3 እርስዋም ባሪያዬ ባላ እነሆ አለች ድረስባት በእኔም ጭን ላይ ትውለድ፥ የእርስዋም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁኑልኝ አለች።

3 And she said, Behold my maid Bilhah, go in unto her; and she shall bear upon my knees, that I may also have children by her.

4 ባሪያዋን ባላንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ለእርሱ ሰጠችው ያዕቆብም ደረሰባት።

4 And she gave him Bilhah her handmaid to wife: and Jacob went in unto her.

5 ባላም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደችለት።

5 And Bilhah conceived, and bare Jacob a son.

6 ራሔልም። እግዚአብሔር ፈረደልኝ፥ ቃሌንም ደግሞ ሰማ፥ ወንድ ልጅንም ሰጠኝ አለች ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው።

6 And Rachel said, God hath judged me, and hath also heard my voice, and hath given me a son: therefore called she his name Dan.

7 የራሔልም ባሪያ ባላ ደግማ ፀነሰች፥ ለያዕቆብም ሁለተኛ ወንድ ልጅን ወለደች።

7 And Bilhah Rachel’s maid conceived again, and bare Jacob a second son.

8 ራሔልም። ብርቱ ትግልን ከእኅቴ ጋር ታገልሁ፥ አሸነፍሁም አለች ስሙንም ንፍታሌም ብላ ጠራችው።

8 And Rachel said, With great wrestlings have I wrestled with my sister, and I have prevailed: and she called his name Naphtali.

9 ልያም መውለድን እንዳቆመች ባየች ጊዜ ባሪያዋን ዘለፋን ወሰደች፥ ሚስት ትሆነውም ዘንድ ለያዕቆብ ሰጠችው።

9 When Leah saw that she had left bearing, she took Zilpah her maid, and gave her Jacob to wife.

10 የልያ ባሪያ ዘለፋም ወንድ ልጅን ለያዕቆብ ወለደች።

10 And Zilpah Leah’s maid bare Jacob a son.

11 ልያም። ጉድ አለች ስሙንም ጋድ ብላ ጠራችው።

11 And Leah said, A troop cometh: and she called his name Gad.

12 የልያ ባሪያ ዘለፋም ዳግመኛ ለያዕቆብ ወንድ ልጅን ወለደች።

12 And Zilpah Leah’s maid bare Jacob a second son.

13 ልያም። ደስታ ሆነልኝ ሴቶች ያመሰግኑኛልና አለች ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው።

13 And Leah said, Happy am I, for the daughters will call me blessed: and she called his name Asher.

14 ሮቤል ስንዴ በሚታጨድበት ወራት ወጣ፥ በእርሻም እንኮይ አገኘ፥ ለእናቱ ለልያም አመጣላት። ራሔልም ልያን፦ የልጅሽን እንኮይ ስጪኝ አለቻት።

14 And Reuben went in the days of wheat harvest, and found mandrakes in the field, and brought them unto his mother Leah. Then Rachel said to Leah, Give me, I pray thee, of thy son’s mandrakes.

15 እርስዋም፦ ባሌን መውሰድሽ በውኑ ጥቂት ነገር ነውን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን? አለቻት። ራሔልም። እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይተኛ አለች።

15 And she said unto her, Is it a small matter that thou hast taken my husband? and wouldest thou take away my son’s mandrakes also? And Rachel said, Therefore he shall lie with thee to night for thy son’s mandrakes.

16 ያዕቆብም ሲመሽ ከዱር ገባ፥ ልያም ልትቀበለው ወጣች እንዲህም አለችው። ወደ እኔ ትገባለህ በልጄ እንኮይ በእርግጥ ተከራይቼሃለሁና። በዚያችም ሌሊት ከእርስዋ ጋር ተኛ።

16 And Jacob came out of the field in the evening, and Leah went out to meet him, and said, Thou must come in unto me; for surely I have hired thee with my son’s mandrakes. And he lay with her that night.

17 እግዚአብሔርም የልያን ጸሎት ሰማ፥ ፀነሰችም፥ አምስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች።

17 And God hearkened unto Leah, and she conceived, and bare Jacob the fifth son.

18 ልያም። ባሪያዬን ለባሌ ስለ ሰጠሁ እግዚአብሔር ዋጋዬን ሰጠኝ አለች ስሙንም ይሳኮር ብላ ጠራችው።

18 And Leah said, God hath given me my hire, because I have given my maiden to my husband: and she called his name Issachar.

19 ልያም ደግማ ፀነሰች፥ ስድስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች።

19 And Leah conceived again, and bare Jacob the sixth son.

20 ልያም። እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው።

20 And Leah said, God hath endued me with a good dowry; now will my husband dwell with me, because I have born him six sons: and she called his name Zebulun.

21 ከዚያም በኋላ ሴት ልጅን ወለደች፥ ስምዋንም ዲና አለቻት።

21 And afterwards she bare a daughter, and called her name Dinah.

22 እግዚአብሔርም ራሔልን አሰበ፥ እግዚአብሔርም ተለመናት፥ ማኅፀንዋንም ከፈተላት

22 And God remembered Rachel, and God hearkened to her, and opened her womb.

23 ፀነሰችም፥ ወንድ ልጅንም ወለደችና። እግዚአብሔር ስድቤን አስወገደ አለች

23 And she conceived, and bare a son; and said, God hath taken away my reproach:

24 ስሙንም። እግዚአብሔር ሁለተኛ ወንድ ልጅን ይጨምርልኝ ስትል ዮሴፍ ብላ ጠራችው።

24 And she called his name Joseph; and said, The Lord shall add to me another son.

25 ራሔልም ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ ወደ ስፍራዬ ወደ አገሬም እመለስ ዘንድ አሰናብተኝ።

25 And it came to pass, when Rachel had born Joseph, that Jacob said unto Laban, Send me away, that I may go unto mine own place, and to my country.

26 ስለ እነርሱ የተገዛሁላቸውን ሚስቶቼንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ የተገዛሁልህን መገዛት ታውቃለህና።

26 Give me my wives and my children, for whom I have served thee, and let me go: for thou knowest my service which I have done thee.

27 ላባም። በዓይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚሁ ተቀመጥ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና አለው።

27 And Laban said unto him, I pray thee, if I have found favour in thine eyes, tarry: for I have learned by experience that the Lord hath blessed me for thy sake.

28 ደመወዝህን ንገረኝ፥ እርሱንም እሰጥሃለሁ አለ።

28 And he said, Appoint me thy wages, and I will give it.

29 እርሱም አለው፦ እንዴት እንዳገለገልሁህ፥ ከብትህንም እንዴት እንደ ጠበቅሁልህ አንተ ታውቃለህ።

29 And he said unto him, Thou knowest how I have served thee, and how thy cattle was with me.

30 ከእኔ መምጣት በፊት የነበረህ ጥቂት ነበርና፥ ዛሬም እጅግ በዛ ወደ አንተ በመምጣቴም እግዚአብሔር ባረክህ አሁንም እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው?

30 For it was little which thou hadst before I came, and it is now increased unto a multitude; and the Lord hath blessed thee since my coming: and now when shall I provide for mine own house also?

31 እርሱም፦ የምሰጥህ ምንድር ነው? አለ። ያዕቆብም አለው። ምንም አትስጠኝ ይህንም ነገር ብታደርግልኝ እንደ ገና በጎችህን አበላለሁ እጠብቃለሁም።

31 And he said, What shall I give thee? And Jacob said, Thou shalt not give me any thing: if thou wilt do this thing for me, I will again feed and keep thy flock:

32 ዛሬ በመንጎችህ በኩል አልፋለሁ፥ በዚያም ከበጎችህ መካከል ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለበቱን ጥቁሩንም በግ ሁሉ፥ ከፍየሎቹም ነቍጣና ዝንጕርጕር ያለበቱን እለያለሁ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ።

32 I will pass through all thy flock to day, removing from thence all the speckled and spotted cattle, and all the brown cattle among the sheep, and the spotted and speckled among the goats: and of such shall be my hire.

33 ስለዚህም በፊትህ ያለውን ደመወዜን ለመመልከት በመጣህ ጊዜ ወደ ፊት ጻድቅነቴ ይመሰክርልኛል ከፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ የሌለበት ከበግ ጠቦቶችም ጥቁር ያልሆኑ ሁሉ፥ እርሱ በእኔ ዘንድ ቢገኝ እንደ ተሰረቀ ይቆጠርብኝ።

33 So shall my righteousness answer for me in time to come, when it shall come for my hire before thy face: every one that is not speckled and spotted among the goats, and brown among the sheep, that shall be counted stolen with me.

34 ላባም። እነሆ እንደ ቃልህ ይሁን አለ።

34 And Laban said, Behold, I would it might be according to thy word.

35 በዚያም ቀን ከተባቶቹ ፍየሎች ሽመልመሌ መሳይና ነቍጣ ያለባቸውን፥ ከእንስቶቹም ፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸውን፥ ነጭ ያለበትን ማንኛውንም ሁሉ፥ ከበጎቹም መካከል ጥቁሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለልጆቹ ሰጣቸው።

35 And he removed that day the he goats that were ringstraked and spotted, and all the she goats that were speckled and spotted, and every one that had some white in it, and all the brown among the sheep, and gave them into the hand of his sons.

36 በእርሱና በያዕቆብ መካከልም የሦስት ቀን መንገድ ያህል አራቃቸው ያዕቆብም የቀሩትን የላባን በጎች ይጠብቅ ነበር።

36 And he set three days’ journey betwixt himself and Jacob: and Jacob fed the rest of Laban’s flocks.

37 ያዕቆብም ልብን ለውዝ ኤርሞን ከሚባሉ እንጨቶች እርጥብ በትርን ወስዶ በበትሮቹ ውስጥ ያለው ነጭ እንዲታይ ነጭ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው።

37 And Jacob took him rods of green poplar, and of the hazel and chesnut tree; and pilled white strakes in them, and made the white appear which was in the rods.

38 የላጣቸውንም በትሮች በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ በበጎቹ ፊት አኖራቸው በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ ይጎመጁ ነበር።

38 And he set the rods which he had pilled before the flocks in the gutters in the watering troughs when the flocks came to drink, that they should conceive when they came to drink.

39 በጎቹም በትሮቹን አይተው ከመጎምጀታቸው የተነሣ ፀነሱ በጎቹም ሽመልመሌ መሳይና ዝንጕርጕር ነቍጣም ያለበቱን ወለዱ።

39 And the flocks conceived before the rods, and brought forth cattle ringstraked, speckled, and spotted.

40 ያዕቆብም ጠቦቶቹን ለየ፥ ሽመልመሌ መሳይና ጥቁር ያለባቸውን በጎቹንም ሁሉ በላባ በጎች ፊት ለፊት አኖረ መንጎቹንም ለብቻቸው አቆማቸው፥ ወደ ላባም በጎች አልጨመራቸውም።

40 And Jacob did separate the lambs, and set the faces of the flocks toward the ringstraked, and all the brown in the flock of Laban; and he put his own flocks by themselves, and put them not unto Laban’s cattle.

41 እንዲህም ሆነ የበረቱት በጎች በጎመጁ ጊዜ፥ በጎቹ በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ ከበጎቹ ፊት አደረገ

41 And it came to pass, whensoever the stronger cattle did conceive, that Jacob laid the rods before the eyes of the cattle in the gutters, that they might conceive among the rods.

42 በደከሙ በጎችም ፊት በትሩን አያደርገውም ነበር የደከሙትም ለላባ፥ የበረቱትም ለያዕቆብ ሆኑ።

42 But when the cattle were feeble, he put them not in: so the feebler were Laban’s, and the stronger Jacob’s.

43 ያ ሰውም እጅግ ባለ ጠጋ ሆነ ብዙም ከብት ሴቶችም ወንዶችም ባሪያዎች ግመሎችም አህዮችም ሆኑለት።

43 And the man increased exceedingly, and had much cattle, and maidservants, and menservants, and camels, and asses.