ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #11
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 11

Genesis 11

1 ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች።

1 And the whole earth was of one language, and of one speech.

2 ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ በዚያም ተቀመጡ።

2 And it came to pass, as they journeyed from the east, that they found a plain in the land of Shinar; and they dwelt there.

3 እርስ በርሳቸውም፦ ኑ፥ ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም እንተኵሰው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው የምድርም ዝፋት እንደ ጭቃ ሆነችላቸው።

3 And they said one to another, Go to, let us make brick, and burn them throughly. And they had brick for stone, and slime had they for morter.

4 እንዲህም፦ ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው አሉ።

4 And they said, Go to, let us build us a city and a tower, whose top may reach unto heaven; and let us make us a name, lest we be scattered abroad upon the face of the whole earth.

5 እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።

5 And the Lord came down to see the city and the tower, which the children of men builded.

6 እግዚአብሔርም አለ፦ እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፥ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው ይህንም ለማድረግ ጀመሩ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም።

6 And the Lord said, Behold, the people is one, and they have all one language; and this they begin to do: and now nothing will be restrained from them, which they have imagined to do.

7 ኑ፥ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።

7 Go to, let us go down, and there confound their language, that they may not understand one another’s speech.

8 እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው ከተማይቱንም መሥራት ተዉ።

8 So the Lord scattered them abroad from thence upon the face of all the earth: and they left off to build the city.

9 ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።

9 Therefore is the name of it called Babel; because the Lord did there confound the language of all the earth: and from thence did the Lord scatter them abroad upon the face of all the earth.

10 የሴም ትውልድ ይህ ነው። ሴም የመቶ ዓመት ሰው ነበረ፥ አርፋክስድንም ከጥፋት ውኃ በኋላ በሁለተኛው ዓመት ወለደ።

10 These are the generations of Shem: Shem was an hundred years old, and begat Arphaxad two years after the flood:

11 ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኋላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

11 And Shem lived after he begat Arphaxad five hundred years, and begat sons and daughters.

12 አርፋክስድም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ቃይንምንም ወለደ

12 And Arphaxad lived five and thirty years, and begat Salah:

13 አርፋክስድም ቃይንምን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ቃይንምም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ሳላንም ወለደ ቃይንምም ሳላን ከወለደ በኋላ ሶስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

13 And Arphaxad lived after he begat Salah four hundred and three years, and begat sons and daughters.

14 ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ዔቦርንም ወለደ

14 And Salah lived thirty years, and begat Eber:

15 ሳላም ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሦስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

15 And Salah lived after he begat Eber four hundred and three years, and begat sons and daughters.

16 ዔቦርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፥ ፋሌቅንም ወለደ

16 And Eber lived four and thirty years, and begat Peleg:

17 ዔቦርም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

17 And Eber lived after he begat Peleg four hundred and thirty years, and begat sons and daughters.

18 ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ራግውንም ወለደ

18 And Peleg lived thirty years, and begat Reu:

19 ራግውንም ከወለደ በኋላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

19 And Peleg lived after he begat Reu two hundred and nine years, and begat sons and daughters.

20 ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሴሮሕንም ወለደ

20 And Reu lived two and thirty years, and begat Serug:

21 ራግውም ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

21 And Reu lived after he begat Serug two hundred and seven years, and begat sons and daughters.

22 ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ናኮርንም ወለደ

22 And Serug lived thirty years, and begat Nahor:

23 ናኮርንም ከወለደ በኋላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

23 And Serug lived after he begat Nahor two hundred years, and begat sons and daughters.

24 ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ታራንም ወለደ

24 And Nahor lived nine and twenty years, and begat Terah:

25 ታራንም ከወለደ በኋላ ናኮር መቶ ሃያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።

25 And Nahor lived after he begat Terah an hundred and nineteen years, and begat sons and daughters.

26 ታራም መቶ ዓመት ኖረ፥ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ።

26 And Terah lived seventy years, and begat Abram, Nahor, and Haran.

27 የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ ሐራንም ሎጥን ወለደ።

27 Now these are the generations of Terah: Terah begat Abram, Nahor, and Haran; and Haran begat Lot.

28 ሐራንም በተወለደበት አገር በከለዳውያን ዑር በአባቱ በታራ ፊት ሞተ።

28 And Haran died before his father Terah in the land of his nativity, in Ur of the Chaldees.

29 አብራምና ናኮርም ሚስቶችን አገቡ የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው የናኮር ሚስት የሐራን ልጅ ሚልካ ናት ሐራንም የሚልካና የዮስካ አባት ነው።

29 And Abram and Nahor took them wives: the name of Abram’s wife was Sarai; and the name of Nahor’s wife, Milcah, the daughter of Haran, the father of Milcah, and the father of Iscah.

30 ሦራም መካን ነበረች ልጅ አልነበራትም።

30 But Sarai was barren; she had no child.

31 ታራም ልጁን አብራምንና የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥን የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ወሰደ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ።

31 And Terah took Abram his son, and Lot the son of Haran his son’s son, and Sarai his daughter in law, his son Abram’s wife; and they went forth with them from Ur of the Chaldees, to go into the land of Canaan; and they came unto Haran, and dwelt there.

32 የታራም ዕድሜ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ሆነ ታራም በካራን ሞተ።

32 And the days of Terah were two hundred and five years: and Terah died in Haran.