ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #11
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘሌዋውያን 11

Leviticus 11

1 እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው።

1 And the Lord spake unto Moses and to Aaron, saying unto them,

2 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በሉአቸው። ከምድር እንስሶች ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው።

2 Speak unto the children of Israel, saying, These are the beasts which ye shall eat among all the beasts that are on the earth.

3 የተሰነጠቀ ሰኮና ያለውንና የሚያመሰኳውን እንስሳ ሁሉ ብሉ።

3 Whatsoever parteth the hoof, and is clovenfooted, and cheweth the cud, among the beasts, that shall ye eat.

4 ነገር ግን ከሚያመሰኩት፥ ሰኮናቸው ስንጥቅ ከሆነው ከእነዚህ አትበሉም ግመል ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።

4 Nevertheless these shall ye not eat of them that chew the cud, or of them that divide the hoof: as the camel, because he cheweth the cud, but divideth not the hoof; he is unclean unto you.

5 ሽኮኮ ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።

5 And the coney, because he cheweth the cud, but divideth not the hoof; he is unclean unto you.

6 ጥንቸልም ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።

6 And the hare, because he cheweth the cud, but divideth not the hoof; he is unclean unto you.

7 እርያም ሰኮናው ተሰንጥቋል፥ ነገር ግን ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።

7 And the swine, though he divide the hoof, and be clovenfooted, yet he cheweth not the cud; he is unclean to you.

8 የእነዚህን ሥጋ አትበሉም፥ በድናቸውንም አትነኩም በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።

8 Of their flesh shall ye not eat, and their carcase shall ye not touch; they are unclean to you.

9 በውኃ ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ እነዚህን ትበላላችሁ በውኆች በባሕሮችም በወንዞችም ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ትበላላችሁ።

9 These shall ye eat of all that are in the waters: whatsoever hath fins and scales in the waters, in the seas, and in the rivers, them shall ye eat.

10 በውኆቹ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ፥ በውኆች ውስጥ የሕይወት ነፍስ ካላቸው ሁሉ፥ በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።

10 And all that have not fins and scales in the seas, and in the rivers, of all that move in the waters, and of any living thing which is in the waters, they shall be an abomination unto you:

11 በእናንተም ዘንድ የተጸየፉ ይሆናሉ ሥጋቸውንም አትበሉም፥ በድናቸውንም ትጸየፋላችሁ።

11 They shall be even an abomination unto you; ye shall not eat of their flesh, but ye shall have their carcases in abomination.

12 ክንፍና ቅርፊትም የሌላቸው በውኃ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።

12 Whatsoever hath no fins nor scales in the waters, that shall be an abomination unto you.

13 ከወፎችም ወገን የምትጸየፉአቸው እነዚህ ናቸው አይበሉም የተጸየፉ ናቸው

13 And these are they which ye shall have in abomination among the fowls; they shall not be eaten, they are an abomination: the eagle, and the ossifrage, and the ospray,

14 ንስር፥ ገዲ፥ ዓሣ አውጭ፥ ጭላት፥ ጭልፊት በየወገኑ፥

14 And the vulture, and the kite after his kind;

15 ቁራ ሁሉ በየወገኑ፥

15 Every raven after his kind;

16 ሰጎን፥ ጠላቋ፥ ዝዪ፥ በቋል በየወገኑ፥

16 And the owl, and the night hawk, and the cuckow, and the hawk after his kind,

17-18 ጕጕት፥ እርኩም፥ ጋጋኖ፥ የውኀ ዶሮ፥

17 And the little owl, and the cormorant, and the great owl,
18 And the swan, and the pelican, and the gier eagle,

19 ይብራ፥ ጥምብ አንሣ አሞራ፥ ሽመላ፥ ሳቢሳ በየወገኑ፥ ጅንጁላቴ ወፍ፥ የሌሊት ወፍ።

19 And the stork, the heron after her kind, and the lapwing, and the bat.

20 የሚበርርም፥ በአራት እግሮችም የሚሔድ ተንቀሳቃሽ ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፈ ነው።

20 All fowls that creep, going upon all four, shall be an abomination unto you.

21 ነገር ግን ከሚበርሩት፥ አራትም እግሮች ካሉአቸው፥ ከእግሮቻቸውም በላይ በምድር ላይ የሚዘልሉባቸው ጭኖች ካሉአቸው ተንቀሳቃሾች እነዚህን ትበላላችሁ።

21 Yet these may ye eat of every flying creeping thing that goeth upon all four, which have legs above their feet, to leap withal upon the earth;

22 ከእነርሱም እነዚህን ትበላላችሁ አራቱን ዓይነት አንበጣዎች በየወገናቸው።

22 Even these of them ye may eat; the locust after his kind, and the bald locust after his kind, and the beetle after his kind, and the grasshopper after his kind.

23 ነገር ግን የሚበርር፥ አራትም እግሮች ያሉት ተንቀሳቃሽ ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፈ ነው።

23 But all other flying creeping things, which have four feet, shall be an abomination unto you.

24 በእነዚህም ርኩስ ትሆናላችሁ የእነርሱንም በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።

24 And for these ye shall be unclean: whosoever toucheth the carcase of them shall be unclean until the even.

25 ከእነርሱም በድን የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።

25 And whosoever beareth ought of the carcase of them shall wash his clothes, and be unclean until the even.

26 ሰኮናም ያለው፥ ነገር ግን ሰኮናው ያልተሰነጠቀ፥ የማያመሰኳም እንሰሳ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው እርሱን የሚነካ ሁሉ ርኩስ ነው።

26 The carcases of every beast which divideth the hoof, and is not clovenfooted, nor cheweth the cud, are unclean unto you: every one that toucheth them shall be unclean.

27 በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ ሁሉ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው የእርሱን በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።

27 And whatsoever goeth upon his paws, among all manner of beasts that go on all four, those are unclean unto you: whoso toucheth their carcase shall be unclean until the even.

28 በድናቸውንም የሚያነሣ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው። እነርሱም በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።

28 And he that beareth the carcase of them shall wash his clothes, and be unclean until the even: they are unclean unto you.

29 በምድር ላይም ከሚንቀሳቀስ ተንቀሳቅሳሽ እነዚህ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው ሙጭልጭላ፥ አይጥ፥ እንሽላሊት በየወገኑ፥

29 These also shall be unclean unto you among the creeping things that creep upon the earth; the weasel, and the mouse, and the tortoise after his kind,

30 ኤሊ፥ አዞ፥ ገበሎ፥ አርጃኖ፥ እስስት።

30 And the ferret, and the chameleon, and the lizard, and the snail, and the mole.

31 ከሚንቀሳቀሱት ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች የሚሆኑ እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም የሞተውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።

31 These are unclean to you among all that creep: whosoever doth touch them, when they be dead, shall be unclean until the even.

32 ከእነርሱም የሞተውን የሚነካ በምንም ላይ ቢወድቅ እርሱ ርኩስ ነው የእንጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቁርበት ወይም ከረጢት ቢሆን የሚሠራበት ዕቃ ሁሉ እርሱ በውኃ ውስጥ ይደረግ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።

32 And upon whatsoever any of them, when they are dead, doth fall, it shall be unclean; whether it be any vessel of wood, or raiment, or skin, or sack, whatsoever vessel it be, wherein any work is done, it must be put into water, and it shall be unclean until the even; so it shall be cleansed.

33 ከእነርሱም አንዳች በውስጡ የወደቀበትን የሸክላውን ዕቃ ሁሉ ስበሩት፥ በውስጡም ያለው ሁሉ ርኩስ ነው።

33 And every earthen vessel, whereinto any of them falleth, whatsoever is in it shall be unclean; and ye shall break it.

34 በእርሱ ውስጥ ያለው፥ ውኃም የሚፈስስበት የሚበላ መብል ሁሉ ርኩስ ነው በዚህም ዕቃ ሁሉ ያለው የሚጠጣ መጠጥ ሁሉ ርኩስ ነው።

34 Of all meat which may be eaten, that on which such water cometh shall be unclean: and all drink that may be drunk in every such vessel shall be unclean.

35 ከእነዚህም በድን የሚወድቅበት ሁሉ ርኩስ ነው እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰባበራል ርኩሶች ናቸው በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ይሆናሉ።

35 And every thing whereupon any part of their carcase falleth shall be unclean; whether it be oven, or ranges for pots, they shall be broken down: for they are unclean, and shall be unclean unto you.

36 ነገር ግን ምንጩ፥ ጕድጓዱም፥ የውኃውም ኵሬ ንጹሐን ናቸው በድናቸውን ግን የሚነካ ርኩስ ነው።

36 Nevertheless a fountain or pit, wherein there is plenty of water, shall be clean: but that which toucheth their carcase shall be unclean.

37 ከበድናቸውም በሚዘራ ዘር ላይ አንዳች ቢወድቅ እርሱ ንጹሕ ነው።

37 And if any part of their carcase fall upon any sowing seed which is to be sown, it shall be clean.

38 ነገር ግን በዘሩ ላይ ውኃ ቢፈስስበት፥ ከዚህ በኋላ ከበድናቸው አንዳች ቢወድቅበት፥ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።

38 But if any water be put upon the seed, and any part of their carcase fall thereon, it shall be unclean unto you.

39 ለመብል ከሚሆኑላችሁ እንስሶች የሞተ ቢኖር፥ በድኑን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ርኩስ ነው።

39 And if any beast, of which ye may eat, die; he that toucheth the carcase thereof shall be unclean until the even.

40 ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል በድኑንም የሚያነሣ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።

40 And he that eateth of the carcase of it shall wash his clothes, and be unclean until the even: he also that beareth the carcase of it shall wash his clothes, and be unclean until the even.

41 በምድርም ላይ የሚንቀሳቀስ ተንቀሳቃሽ ሁሉ የተጸየፈ ነው፥ አትብሉትም።

41 And every creeping thing that creepeth upon the earth shall be an abomination; it shall not be eaten.

42 በሆዱ የሚሳብ፥ በአራትም እግሮች የሚሳብ፥ ብዙ እግሮችም ያሉት፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ የተጸየፉ ናቸውና አትብሉአቸው።

42 Whatsoever goeth upon the belly, and whatsoever goeth upon all four, or whatsoever hath more feet among all creeping things that creep upon the earth, them ye shall not eat; for they are an abomination.

43 በሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ ሰውነታችሁን አታስጸይፉ በእነርሱም እንዳትረክሱ ሰውነታችሁን አታርክሱባቸው።

43 Ye shall not make yourselves abominable with any creeping thing that creepeth, neither shall ye make yourselves unclean with them, that ye should be defiled thereby.

44 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና በምድርም ላይ በሚሳብ ተንቀሳቃሽ ሁሉ ሰውነታችሁን አታርክሱ።

44 For I am the Lord your God: ye shall therefore sanctify yourselves, and ye shall be holy; for I am holy: neither shall ye defile yourselves with any manner of creeping thing that creepeth upon the earth.

45 እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር ነኝ እንግዲህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።

45 For I am the Lord that bringeth you up out of the land of Egypt, to be your God: ye shall therefore be holy, for I am holy.

46 የእንስሳና የወፍ፥ በውኃም ውስጥ የሚንቀሳቀስ የፍጥረት ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀስ የፍጥረት ሁሉ ሕግ ይህ ነው።

46 This is the law of the beasts, and of the fowl, and of every living creature that moveth in the waters, and of every creature that creepeth upon the earth:

47 በርኩስና በንጹሕ መካከል፥ የሕይወት ነፍስ ካላቸውም በምትበሉትና በማትበሉት መካከል እንድትለዩ ነው።

47 To make a difference between the unclean and the clean, and between the beast that may be eaten and the beast that may not be eaten.