መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #37
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 37 |
Ps 37 |
1 በክፉዎች ላይ አትቅና፥ ዓመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና |
1 Fret not thyself because of evildoers, neither be thou envious against the workers of iniquity. |
2 እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፥ እንደ ለመለመ ቅጠልም ይረግፋሉና። |
2 For they shall soon be cut down like the grass, and wither as the green herb. |
3 በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ። |
3 Trust in the Lord, and do good; so shalt thou dwell in the land, and verily thou shalt be fed. |
4 በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል። |
4 Delight thyself also in the Lord; and he shall give thee the desires of thine heart. |
5 መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል። |
5 Commit thy way unto the Lord; trust also in him; and he shall bring it to pass. |
6 ጽድቅህን እንደ ብርሃን፦ ፍርድህንም እንደ ቀትር ያመጣል። |
6 And he shall bring forth thy righteousness as the light, and thy judgment as the noonday. |
7 ለእግዚአብሔር ተገዛ ተስፋም አድርገው። መንገድም በቀናችለትና ጥመትን በሚያደርግ ሰው አትቅና። |
7 Rest in the Lord, and wait patiently for him: fret not thyself because of him who prospereth in his way, because of the man who bringeth wicked devices to pass. |
8 ከቁጣ ራቅ መዓትንም ተው እንዳትበድል አትቅና። |
8 Cease from anger, and forsake wrath: fret not thyself in any wise to do evil. |
9 ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ። |
9 For evildoers shall be cut off: but those that wait upon the Lord, they shall inherit the earth. |
10 ገና ጥቂት፥ ኃጢአተኛም አይኖርም ትፈልገዋለህ ቦታውንም አታገኝም። |
10 For yet a little while, and the wicked shall not be: yea, thou shalt diligently consider his place, and it shall not be. |
11 ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፥ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል። |
11 But the meek shall inherit the earth; and shall delight themselves in the abundance of peace. |
12 ኃጢአተኛ ጻድቁን ይመለካከተዋል፥ ጥርሱንም በእርሱ ላይ ያንገጫግጫል። |
12 The wicked plotteth against the just, and gnasheth upon him with his teeth. |
13 እግዚአብሔር ይሥቅበታል፥ ቀኑ እንደሚደርስ አይቶአልና። |
13 The Lord shall laugh at him: for he seeth that his day is coming. |
14 ኃጢአተኞች ሰይፋቸውን መዘዙ፥ ቀስታቸውንም ገተሩ ድሀውንና ችግረኛውን ይጥሉ ዘንድ ልበ ቅኖችንም ይወጉ ዘንድ |
14 The wicked have drawn out the sword, and have bent their bow, to cast down the poor and needy, and to slay such as be of upright conversation. |
15 ሰይፋቸው ወደ ልባቸው ይግባ፥ ቀስታቸውም ይሰበር። |
15 Their sword shall enter into their own heart, and their bows shall be broken. |
16 ለጻድቅ ያለው ጥቂት ከብዙ ከኃጢአተኞች ሀብት ይበልጣል። |
16 A little that a righteous man hath is better than the riches of many wicked. |
17 የኃጥአን ክንድ ትሰበራለችና እግዚአብሔር ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል። |
17 For the arms of the wicked shall be broken: but the Lord upholdeth the righteous. |
18 የንጹሓንን መንገድ እግዚአብሔር ያውቃል፥ ርስታቸውም ለዘላለም ነው |
18 The Lord knoweth the days of the upright: and their inheritance shall be for ever. |
19 በክፉ ዘመንም አያፍሩም በራብ ዘመንም ይጠግባሉ። |
19 They shall not be ashamed in the evil time: and in the days of famine they shall be satisfied. |
20 ኅጥአን ግን ይጠፋሉ፥ የእግዚአብሔር ጠላቶች በከበሩና ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ እንደ ጢስ ይጠፋሉ። |
20 But the wicked shall perish, and the enemies of the Lord shall be as the fat of lambs: they shall consume; into smoke shall they consume away. |
21 ኃጢአተኛ ይበደራል አይከፍልምም ጻድቅ ግን ይራራል ይሰጣልም። |
21 The wicked borroweth, and payeth not again: but the righteous sheweth mercy, and giveth. |
22 እርሱን የሚባርኩት ምድርን ይወርሳሉና የሚረግሙት ግን ይጠፋሉ። |
22 For such as be blessed of him shall inherit the earth; and they that be cursed of him shall be cut off. |
23 የሰው አካሄድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይጸናል፥ መንገዱንም ይወድዳል። |
23 The steps of a good man are ordered by the Lord: and he delighteth in his way. |
24 ቢወድቅም ለድንጋፄ አይጣልም፥ እግዚአብሔር እጁን ይዞ ይደግፈዋልና። |
24 Though he fall, he shall not be utterly cast down: for the Lord upholdeth him with his hand. |
25 ጐለመስሁ አረጀሁም ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም። |
25 I have been young, and now am old; yet have I not seen the righteous forsaken, nor his seed begging bread. |
26 ሁልጊዜ ይራራል ያበድርማል፥ ዘሩም በበረከት ይኖራል። |
26 He is ever merciful, and lendeth; and his seed is blessed. |
27 ከክፉ ሽሽ፥ መልካምንም አድርግ ለዘላለምም ትኖራለህ። |
27 Depart from evil, and do good; and dwell for evermore. |
28 እግዚአብሔር ፍርዱን ይወድዳልና፥ ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል የኅጥኣን ዘር ግን ይጠፋል። |
28 For the Lord loveth judgment, and forsaketh not his saints; they are preserved for ever: but the seed of the wicked shall be cut off. |
29 ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፥ በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ። |
29 The righteous shall inherit the land, and dwell therein for ever. |
30 የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል፥ አንደበቱም ፍርድን ይናገራል። |
30 The mouth of the righteous speaketh wisdom, and his tongue talketh of judgment. |
31 የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው፥ በእርምጃውም አይሰናከልም። |
31 The law of his God is in his heart; none of his steps shall slide. |
32 ኃጢአተኛ ጻድቁን ይመለከተዋል፥ ሊገድለውም ይወድዳል። |
32 The wicked watcheth the righteous, and seeketh to slay him. |
33 እግዚአብሔር ግን በእጁ አይተወውም፥ በተፋረደውም ጊዜ አያሸንፈውም። |
33 The Lord will not leave him in his hand, nor condemn him when he is judged. |
34 እግዚአብሔርን ደጅ ጥና፥ መንገዱንም ጠብቅ፥ ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል ኃጢአተኞችም ሲጠፉ ታያለህ። |
34 Wait on the Lord, and keep his way, and he shall exalt thee to inherit the land: when the wicked are cut off, thou shalt see it. |
35 ኃጥአን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት። |
35 I have seen the wicked in great power, and spreading himself like a green bay tree. |
36 ብመለስ ግን አጣሁት ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም። |
36 Yet he passed away, and, lo, he was not: yea, I sought him, but he could not be found. |
37 ቅንነትን ጠብቅ፥ ጽድቅንም እይ ለሰላም ሰው ቅሬታ አለውና። |
37 Mark the perfect man, and behold the upright: for the end of that man is peace. |
38 በደለኞች በአንድነት ይጠፋሉ። የኃጢአተኞች ቅሬታ ይጠፋል። |
38 But the transgressors shall be destroyed together: the end of the wicked shall be cut off. |
39 የጻድቃን መድኃኒታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው በመከራቸውም ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው። |
39 But the salvation of the righteous is of the Lord: he is their strength in the time of trouble. |
40 እግዚአብሔር ይረዳቸዋል፥ ያድናቸዋልም፥ ከኃጢአተኞችም እጅ ያወጣቸዋል፥ ያድናቸዋል፥ በእርሱ ታምነዋልና። |
40 And the Lord shall help them, and deliver them: he shall deliver them from the wicked, and save them, because they trust in him. |