ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #23
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘኍልቍ 23

Numbers 23

1 በለዓምም ባላቅን፦ ሰባት መሠዊያ በዚህ ሥራልኝ፥ ሰባትም ወይፈን ሰባትም አውራ በግ በዚህ አዘጋጅልኝ አለው።

1 And Balaam said unto Balak, Build me here seven altars, and prepare me here seven oxen and seven rams.

2 ባላቅም በለዓም እንደ ተናገረ አደረገ ባላቅና በለዓምም በየመሠዊያው ላይ አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ አሳረጉ።

2 And Balak did as Balaam had spoken; and Balak and Balaam offered on every altar a bullock and a ram.

3 በለዓምም ባላቅን፦ በመሥዋዕትህ ዘንድ ቆይ፥ እኔም እሄዳለሁ ምናልባት እግዚአብሔር ሊገናኘኝ ይመጣል እርሱም የሚገልጥልኝን እነግርሃለሁ አለው። ወደ ጉብታም ሄደ።

3 And Balaam said unto Balak, Stand by thy burnt offering, and I will go: peradventure the Lord will come to meet me: and whatsoever he sheweth me I will tell thee. And he went to an high place.

4 እግዚአብሔርም ከበለዓም ጋር ተገናኘ እርሱም፦ ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጀሁ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ አሳረግሁ አለው።

4 And God met Balaam: and he said unto him, I have prepared seven altars, and I have offered upon every altar a bullock and a ram.

5 እግዚአብሔርም ቃልን በበለዓም አፍ አድርጎ። ወደ ባላቅ ተመለስ፥ እንዲህም በል አለው።

5 And the Lord put a word in Balaam’s mouth, and said, Return unto Balak, and thus thou shalt speak.

6 ወደ እርሱም ተመለሰ፥ እነሆም፥ እርሱና የሞዓብ አለቆች ሁሉ በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር።

6 And he returned unto him, and, lo, he stood by his burnt sacrifice, he, and all the princes of Moab.

7 ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፥እንዲህም አለ፦ ባላቅ ከአራም አመጣኝ፥ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን ተጣላልኝ ብሎ።

7 And he took up his parable, and said, Balak the king of Moab hath brought me from Aram, out of the mountains of the east, saying, Come, curse me Jacob, and come, defy Israel.

8 እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ?

8 How shall I curse, whom God hath not cursed? or how shall I defy, whom the Lord hath not defied?

9 በአምቦች ራስ ላይ ሆኜ አየዋለሁ፥ በኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ እነሆ፥ ብቻውን የሚቀመጥ ሕዝብ ነው፥ በአሕዛብም መካከል አይቈጠርም።

9 For from the top of the rocks I see him, and from the hills I behold him: lo, the people shall dwell alone, and shall not be reckoned among the nations.

10 የያዕቆብን ትቢያ ማን ይቈጥራል? የእስራኤልስ እርቦ ማን ይቈጥራል? የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።

10 Who can count the dust of Jacob, and the number of the fourth part of Israel? Let me die the death of the righteous, and let my last end be like his!

11 ባላቅም በለዓምን፦ ያደረግህብኝ ምንድር ነው? ጠላቶቼን ትረግምልኝ ዘንድ ጠራሁህ እነሆም፥ ፈጽመህ ባረክሃቸው አለው።

11 And Balak said unto Balaam, What hast thou done unto me? I took thee to curse mine enemies, and, behold, thou hast blessed them altogether.

12 እርሱም መልሶ፦ በውኑ እግዚአብሔር በአፌ ያደረገውን እናገር ዘንድ አልጠነቀቅምን? አለው።

12 And he answered and said, Must I not take heed to speak that which the Lord hath put in my mouth?

13 ባላቅም። በዚያ ሆነህ ታያቸው ዘንድ፥ እባክህ፥ ከእኔ ጋር ወደ ሌላ ቦታ ና ዳርቻቸውንም ብቻ ታያለህ፥ ሁሉን ግን አታይም በዚያም ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ አለው።

13 And Balak said unto him, Come, I pray thee, with me unto another place, from whence thou mayest see them: thou shalt see but the utmost part of them, and shalt not see them all: and curse me them from thence.

14 ወደ ጾፊምም ሜዳ ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ ላይ ወሰደው ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን አንድም አውራ በግ አሳረገ።

14 And he brought him into the field of Zophim, to the top of Pisgah, and built seven altars, and offered a bullock and a ram on every altar.

15 ባላቅንም። እኔ ወደዚያ ለመገናኘት ስሄድ በዚህ በመሥዋዕትህ ዘንድ ቆይ አለው።

15 And he said unto Balak, Stand here by thy burnt offering, while I meet the Lord yonder.

16 እግዚአብሔርም በለዓምን ተገናኘ፥ ቃልንም በአፉ አድርጎ። ወደ ባላቅ ተመለስ፥ እንዲህም በል አለው።

16 And the Lord met Balaam, and put a word in his mouth, and said, Go again unto Balak, and say thus.

17 ወደ እርሱም መጣ፥ እነሆም፥ እርሱ ከእርሱም ጋር የሞዓብ አለቆች በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር ባላቅም። እግዚአብሔር የተናገረው ምንድር ነው? አለው።

17 And when he came to him, behold, he stood by his burnt offering, and the princes of Moab with him. And Balak said unto him, What hath the Lord spoken?

18 ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፥እንዲህም አለ፦ ባላቅ ሆይ፥ ተነሣ፥ ስማ፤ የሴፎር ልጅ ሆይ፥ አድምጠኝ፤

18 And he took up his parable, and said, Rise up, Balak, and hear; hearken unto me, thou son of Zippor:

19 ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?

19 God is not a man, that he should lie; neither the son of man, that he should repent: hath he said, and shall he not do it? or hath he spoken, and shall he not make it good?

20 እነሆ፥ ለመባረክ ትእዛዝን ተቀብያለሁ እርሱ ባርኮአል፥ እመልሰውም ዘንድ አልችልም።

20 Behold, I have received commandment to bless: and he hath blessed; and I cannot reverse it.

21 በያዕቆብ ላይ ክፋትን አልተመለከተም፥ በእስራኤልም ጠማምነትን አላየም፤ አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነው፥ የንጉሥም እልልታ በመካከላቸው አለ።

21 He hath not beheld iniquity in Jacob, neither hath he seen perverseness in Israel: the Lord his God is with him, and the shout of a king is among them.

22 እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶአቸዋል ጕልበቱ አንድ ቀንድ እንዳለው ነው።

22 God brought them out of Egypt; he hath as it were the strength of an unicorn.

23 በያዕቆብ ላይ አስማት የለም፥ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤ በጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል። እግዚአብሔር ምን አደረገ! ይባላል።

23 Surely there is no enchantment against Jacob, neither is there any divination against Israel: according to this time it shall be said of Jacob and of Israel, What hath God wrought!

24 እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይቆማል፥ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን አስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አይተኛም።

24 Behold, the people shall rise up as a great lion, and lift up himself as a young lion: he shall not lie down until he eat of the prey, and drink the blood of the slain.

25 ባላቅም በለዓምን፦ ከቶ አትርገማቸው፥ ከቶም አትባርካቸው አለው።

25 And Balak said unto Balaam, Neither curse them at all, nor bless them at all.

26 በለዓምም መልሶ ባላቅን፦ እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ አደርጋለሁ ብዬ አልተናገርሁህምን? አለው።

26 But Balaam answered and said unto Balak, Told not I thee, saying, All that the Lord speaketh, that I must do?

27 ባላቅም በለዓምን፦ ና፥ ወደ ሌላ ስፍራ እወስድሃለሁ ምናልባት በዚህ ሆነህ እነርሱን ትረግምልኝ ዘንድ እግዚአብሔር ይወድዳል አለው።

27 And Balak said unto Balaam, Come, I pray thee, I will bring thee unto another place; peradventure it will please God that thou mayest curse me them from thence.

28 ባላቅም ምድረ በዳውን ከላይ ወደሚመለከተው ወደ ፌጎር ላይ በለዓምን ወሰደው።

28 And Balak brought Balaam unto the top of Peor, that looketh toward Jeshimon.

29 በለዓምም ባላቅን፦ በዚህ ሰባት መሠዊያዎች ሥራልኝ፥ በዚህም ሰባት ወይፈን ሰባትም አውራ በግ አዘጋጅልኝ አለው።

29 And Balaam said unto Balak, Build me here seven altars, and prepare me here seven bullocks and seven rams.

30 ባላቅም በለዓም እንዳለው አደረገ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ አሳረገ።

30 And Balak did as Balaam had said, and offered a bullock and a ram on every altar.