ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #23
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘሌዋውያን 23

Leviticus 23

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

1 And the Lord spake unto Moses, saying,

2 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። የተቀደሰ ጉባኤ ብላችሁ የምታውጁአቸው በዓላቶቼ፥ የእግዚአብሔር በዓላት፥ እነዚህ ናቸው።

2 Speak unto the children of Israel, and say unto them, Concerning the feasts of the Lord, which ye shall proclaim to be holy convocations, even these are my feasts.

3 ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት ነው የተቀደሰ ጉባኤ ይሆንበታል ምንም ሥራ አትሠሩም በምትኖሩበት ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው።

3 Six days shall work be done: but the seventh day is the sabbath of rest, an holy convocation; ye shall do no work therein: it is the sabbath of the Lord in all your dwellings.

4 እነዚህ የእግዚአብሔር በዓላት፥ በየዘመናቸው የምታውጁአቸው፥ የተቀደሰ ጉባኤ ናቸው።

4 These are the feasts of the Lord, even holy convocations, which ye shall proclaim in their seasons.

5 በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ሲመሽ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው።

5 In the fourteenth day of the first month at even is the Lord’s passover.

6 በዚህም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን ለእግዚአብሔር የቂጣ በዓል ነው ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ብሉ።

6 And on the fifteenth day of the same month is the feast of unleavened bread unto the Lord: seven days ye must eat unleavened bread.

7 በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ የተግባር ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።

7 In the first day ye shall have an holy convocation: ye shall do no servile work therein.

8 ሰባት ቀንም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን አቅርቡ በሰባተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ነው የተግባር ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።

8 But ye shall offer an offering made by fire unto the Lord seven days: in the seventh day is an holy convocation: ye shall do no servile work therein.

9 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

9 And the Lord spake unto Moses, saying,

10 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ መከሩንም ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ

10 Speak unto the children of Israel, and say unto them, When ye be come into the land which I give unto you, and shall reap the harvest thereof, then ye shall bring a sheaf of the firstfruits of your harvest unto the priest:

11 እርሱም ነዶውን በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምርላችሁ ይወዝውዘው በማግስቱ ከሰንበት በኋላ ካህኑ ይወዝውዘው።

11 And he shall wave the sheaf before the Lord, to be accepted for you: on the morrow after the sabbath the priest shall wave it.

12 ነዶውንም በወዘወዛችሁበት ቀን ነውር የሌለበትን የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር አቅርቡ።

12 And ye shall offer that day when ye wave the sheaf an he lamb without blemish of the first year for a burnt offering unto the Lord.

13 የእህልም ቍርባን ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ለእሳት ቍርባን ይሁን የመጠጡም ቍርባን የወይን ጠጅ የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ ይሁን።

13 And the meat offering thereof shall be two tenth deals of fine flour mingled with oil, an offering made by fire unto the Lord for a sweet savour: and the drink offering thereof shall be of wine, the fourth part of an hin.

14 እንጀራውንም፥ የተጠበሰውንም እሸት፥ ለምለሙንም እሸት የአምላካችሁን ቍርባን እስከምታቀርቡበት እስከዚህ ቀን ድረስ አትብሉ። ይህ በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው።

14 And ye shall eat neither bread, nor parched corn, nor green ears, until the selfsame day that ye have brought an offering unto your God: it shall be a statute for ever throughout your generations in all your dwellings.

15 የወዘወዛችሁትን ነዶ ከምታመጡበት ቀን በኋላ ከሰንበት ማግስት ፍጹም ሰባት ጊዜ ሰባት ቀን ቍጠሩ

15 And ye shall count unto you from the morrow after the sabbath, from the day that ye brought the sheaf of the wave offering; seven sabbaths shall be complete:

16 እስከ ሰባተኛ ሰንበት ማግስት ድረስ አምሳ ቀን ቍጠሩ አዲሱንም የእህል ቍርባን ወደ እግዚአብሔር አቅርቡ።

16 Even unto the morrow after the seventh sabbath shall ye number fifty days; and ye shall offer a new meat offering unto the Lord.

17 ከየማደሪያችሁ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ ከሆነ መልካም ዱቄት የተሠራ ሁለት የመወዝወዝ እንጀራ ታመጣላችሁ ለእግዚአብሔር ለበኵራት ቍርባን እንዲሆን በእርሾ ይጋገራል።

17 Ye shall bring out of your habitations two wave loaves of two tenth deals: they shall be of fine flour; they shall be baken with leaven; they are the firstfruits unto the Lord.

18 ከእንጀራውም ጋር ነውር የሌለባቸውን የአንድ ዓመት ሰባት ጠቦቶች፥ አንድ ወይፈንም፥ ሁለትም አውራ በጎች ታቀርባላችሁ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ይሁኑ ከእህልም ቍርባን፥ ከመጠጡም ቍርባን ጋር ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የእሳት ቍርባን ይሁኑ።

18 And ye shall offer with the bread seven lambs without blemish of the first year, and one young bullock, and two rams: they shall be for a burnt offering unto the Lord, with their meat offering, and their drink offerings, even an offering made by fire, of sweet savour unto the Lord.

19 አንድም አውራ ፍየል ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሁለትም የአንድ ዓመት ተባት ጠቦቶች ለደኅንነት መሥዋዕት አቅርቡ።

19 Then ye shall sacrifice one kid of the goats for a sin offering, and two lambs of the first year for a sacrifice of peace offerings.

20 ካህኑም ከበኵራቱ እንጀራ ከሁለቱም ጠቦቶች ጋር በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቍርባን ይወዘውዛቸዋል ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ፈንታ ነው ለካህኑ ይሁን።

20 And the priest shall wave them with the bread of the firstfruits for a wave offering before the Lord, with the two lambs: they shall be holy to the Lord for the priest.

21 በዚያም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሆንላችሁ ዘንድ ታውጃላችሁ የተግባር ሥራ ሁሉ አታድርጉበት በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው።

21 And ye shall proclaim on the selfsame day, that it may be an holy convocation unto you: ye shall do no servile work therein: it shall be a statute for ever in all your dwellings throughout your generations.

22 የምድራችሁንም መከር በሰበሰባችሁ ጊዜ የእርሻችሁን ድንበር ፈጽማችሁ አትጨዱ፥ የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ ለድሆችና ለእንግዶች ተዉት እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

22 And when ye reap the harvest of your land, thou shalt not make clean riddance of the corners of thy field when thou reapest, neither shalt thou gather any gleaning of thy harvest: thou shalt leave them unto the poor, and to the stranger: I am the Lord your God.

23 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

23 And the Lord spake unto Moses, saying,

24 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት፥ በመለከት ድምፅ መታሰቢያ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ።

24 Speak unto the children of Israel, saying, In the seventh month, in the first day of the month, shall ye have a sabbath, a memorial of blowing of trumpets, an holy convocation.

25 የተግባር ሥራ ሁሉ አታድርጉበት፥ ለእግዚአብሔርም የእሳት ቍርባንን አቅርቡ።

25 Ye shall do no servile work therein: but ye shall offer an offering made by fire unto the Lord.

26 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

26 And the Lord spake unto Moses, saying,

27 በዚህ በሰባተኛው ወር አሥረኛው ቀን የማስተስረያ ቀን ነው የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ ሰውነታችሁን አስጨንቋት፥ ለእግዚአብሔርም የእሳት ቍርባንን አቅርቡ።

27 Also on the tenth day of this seventh month there shall be a day of atonement: it shall be an holy convocation unto you; and ye shall afflict your souls, and offer an offering made by fire unto the Lord.

28 በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ፊት ማስተስረያ ይሆንላችሁ ዘንድ የማስተስረያ ቀን ነውና በዚያ ቀን ሥራ ሁሉ አትሥሩ።

28 And ye shall do no work in that same day: for it is a day of atonement, to make an atonement for you before the Lord your God.

29 በዚያም ቀን የማይዋረድ ሰው ሁሉ ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።

29 For whatsoever soul it be that shall not be afflicted in that same day, he shall be cut off from among his people.

30 በዚያም ቀን ሥራ የሚሠራውን ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል አጠፋዋለሁ።

30 And whatsoever soul it be that doeth any work in that same day, the same soul will I destroy from among his people.

31 ሥራ ሁሉ አታድርጉበት በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው።

31 Ye shall do no manner of work: it shall be a statute for ever throughout your generations in all your dwellings.

32 የዕረፍት ሰንበት ይሁንላችሁ፥ ሰውነታችሁንም አዋርዱ በወሩ በዘጠነኛው ቀን በማታ ጊዜ፥ ከማታ ጀምራችሁ እስከ ማታ ድረስ፥ ሰንበታችሁን አድርጉ።

32 It shall be unto you a sabbath of rest, and ye shall afflict your souls: in the ninth day of the month at even, from even unto even, shall ye celebrate your sabbath.

33 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

33 And the Lord spake unto Moses, saying,

34 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። በዚህ በሰባተኛው ወር ከአሥራ አምስተኛው ቀን ጀምሮ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የዳስ በዓል ይሆናል።

34 Speak unto the children of Israel, saying, The fifteenth day of this seventh month shall be the feast of tabernacles for seven days unto the Lord.

35 በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁን የተግባር ሥራ ሁሉ አታድርጉበት።

35 On the first day shall be an holy convocation: ye shall do no servile work therein.

36 ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባንን አቅርቡ በስምንተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፥ ለእግዚአብሔርም የሚቃጠለውን ቍርባን አቅርቡ ዋና ጉባኤ ነው የተግባር ሥራ ሁሉ አታድርጉበት።

36 Seven days ye shall offer an offering made by fire unto the Lord: on the eighth day shall be an holy convocation unto you; and ye shall offer an offering made by fire unto the Lord: it is a solemn assembly; and ye shall do no servile work therein.

37 የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህሉንም ቍርባን፥ መሥዋዕቱንም፥ የመጠጡንም ቍርባን፥ በየቀኑ የእሳት ቍርባን ወደ እግዚአብሔር ታቀርቡባቸው ዘንድ የተቀደሱ ጉባኤዎች እንዲሆኑ የምታውጁአቸው የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው።

37 These are the feasts of the Lord, which ye shall proclaim to be holy convocations, to offer an offering made by fire unto the Lord, a burnt offering, and a meat offering, a sacrifice, and drink offerings, every thing upon his day:

38 እነዚህም ከእግዚአብሔር ሰንበታት ሌላ፥ ለእግዚአብሔርም ከምትሰጡት ከስጦታችሁ ሌላ፥ ከስእለታችሁም ሁሉ ሌላ፥ በፈቃዳችሁም ከምታቀርቡአቸው ሁሉ ሌላ ናቸው።

38 Beside the sabbaths of the Lord, and beside your gifts, and beside all your vows, and beside all your freewill offerings, which ye give unto the Lord.

39 ከሰባተኛውም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን የምድሩን ፍሬ ካከማቻችሁ በኋላ፥ የእግዚአብሔርን በዓል ሰባት ቀን ጠብቁ በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት ይሁን፥ በስምንተኛውም ቀን ዕረፍት ይሁን።

39 Also in the fifteenth day of the seventh month, when ye have gathered in the fruit of the land, ye shall keep a feast unto the Lord seven days: on the first day shall be a sabbath, and on the eighth day shall be a sabbath.

40 በመጀመሪያው ቀን የመልካም ዛፍ ፍሬ፥ የሰሌን ቅርንጫፍ፥ የለመለመውን ዛፍ ቅርንጫፍ፥ የወንዝም አኻያ ዛፍ ውሰዱ በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ፊት ሰባት ቀን ደስ ይበላችሁ።

40 And ye shall take you on the first day the boughs of goodly trees, branches of palm trees, and the boughs of thick trees, and willows of the brook; and ye shall rejoice before the Lord your God seven days.

41 ይህንንም በዓል በየዓመቱ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር አድርጉ ለልጅ ልጃችሁ የዘላለም ሥርዓት ነው በሰባተኛው ወር ትጠብቁታላችሁ።

41 And ye shall keep it a feast unto the Lord seven days in the year. It shall be a statute for ever in your generations: ye shall celebrate it in the seventh month.

42-43 ሰባት ቀን በዳሶች ውስጥ ትቀመጣላችሁ ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በዳስ ውስጥ እንዳስቀመጥኋቸው የልጅ ልጆቻችሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእስራኤል ያሉት የአገር ልጆች ሁሉ በዳስ ውስጥ ይቀመጡ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

42 Ye shall dwell in booths seven days; all that are Israelites born shall dwell in booths:
43 That your generations may know that I made the children of Israel to dwell in booths, when I brought them out of the land of Egypt: I am the Lord your God.

44 ሙሴም የእግዚአብሔርን በዓላት ለእስራኤል ልጆች ተናገረ።

44 And Moses declared unto the children of Israel the feasts of the Lord.