ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #23
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘጸአት 23 |
Exodus 23 |
1 ሐሰተኛ ወሬ አትቀበል ሐሰተኛ ምስክርም ትሆን ዘንድ ከኃጢአተኛ ጋር እጅህን አታንሣ። |
1 Thou shalt not raise a false report: put not thine hand with the wicked to be an unrighteous witness. |
2 ክፉውን ለማድረግ ብዙ ሰዎችን አትከተል ፍርድንም ለማጥመም ከብዙ ሰዎች ጋር ተስማምተህ አትመስክር። |
2 Thou shalt not follow a multitude to do evil; neither shalt thou speak in a cause to decline after many to wrest judgment: |
3 በፍርድ ነገርም ለድሀው አታድላ። |
3 Neither shalt thou countenance a poor man in his cause. |
4 የጠላትህን በሬ ወይም አህያውን ጠፍቶ ብታገኘው በፍጹም መልስለት። |
4 If thou meet thine enemy’s ox or his ass going astray, thou shalt surely bring it back to him again. |
5 የሚጠላህን ሰው አህያ ከሸክሙ በታች ወድቆ ብታየው አትተወው፥ ነገር ግን ከእርሱ ጋር አንሣው። |
5 If thou see the ass of him that hateth thee lying under his burden, and wouldest forbear to help him, thou shalt surely help with him. |
6 በሚምዋገትበት ጊዜ የድሀህን ፍርድ አታጥምም። |
6 Thou shalt not wrest the judgment of thy poor in his cause. |
7 ከሐሰት ነገር ራቅ እኔ ኃጢአተኛውን አላጸድቅምና ንጹሕንና ጻድቅን አትግደል። |
7 Keep thee far from a false matter; and the innocent and righteous slay thou not: for I will not justify the wicked. |
8 ማማለጃን አትቀበል ማማለጃ የዓይናማዎችን ሰዎች ዓይን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። |
8 And thou shalt take no gift: for the gift blindeth the wise, and perverteth the words of the righteous. |
9 በስደተኛው ግፍ አታድርጉ እናንተ በግብፅ ምድር ስደተኞች ስለ ነበራችሁ የስደተኛ ነፍስ እንዴት እንደ ሆነች አውቃችኋልና። |
9 Also thou shalt not oppress a stranger: for ye know the heart of a stranger, seeing ye were strangers in the land of Egypt. |
10 ስድስት ዓመት ምድርህን ዝራ፥ ፍሬዋንም አግባ |
10 And six years thou shalt sow thy land, and shalt gather in the fruits thereof: |
11 በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት አሳርፋትም የሕዝብህም ድሆች ይበሉታል ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። እንዲሁም በወይንህና በወይራህ አድርግ። |
11 But the seventh year thou shalt let it rest and lie still; that the poor of thy people may eat: and what they leave the beasts of the field shall eat. In like manner thou shalt deal with thy vineyard, and with thy oliveyard. |
12 ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ በሬህና አህያህ ያርፉ ዘንድ ለባሪያህም ልጅ ለመጻተኛውም ዕረፍት ይሆን ዘንድ በሰባተኛው ቀን ዕረፍ። |
12 Six days thou shalt do thy work, and on the seventh day thou shalt rest: that thine ox and thine ass may rest, and the son of thy handmaid, and the stranger, may be refreshed. |
13 ያልኋችሁንም ነገር ሁሉ ጠብቁ የሌሎችንም አማልክት ስም አትጥሩ፥ ከአፋችሁም አይሰማ። |
13 And in all things that I have said unto you be circumspect: and make no mention of the name of other gods, neither let it be heard out of thy mouth. |
14 በዓመት ሦስት ጊዜ በዓል ታደርግልኛለህ። |
14 Three times thou shalt keep a feast unto me in the year. |
15 የቂጣውን በዓል ጠብቅ በአቢብ ወር ከግብፅ ምድር ወጥታችኋልና በዚህ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላለህ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ። |
15 Thou shalt keep the feast of unleavened bread: (thou shalt eat unleavened bread seven days, as I commanded thee, in the time appointed of the month Abib; for in it thou camest out from Egypt: and none shall appear before me empty:) |
16 በእርሻም የምትዘራትን የፍሬህን በኵራት የመከር በዓል፥ ዓመቱም ሳያልቅ ፍሬህን ከእርሻ ባከማቸህ ጊዜ የመክተቻውን በዓል ጠብቅ። |
16 And the feast of harvest, the firstfruits of thy labours, which thou hast sown in the field: and the feast of ingathering, which is in the end of the year, when thou hast gathered in thy labours out of the field. |
17 በዓመት ሦስት ጊዜ በአንተ ዘንድ ያለው ወንድ ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ። |
17 Three times in the year all thy males shall appear before the Lord God. |
18 የመሥዋዕቴን ደም ከቦካ እንጀራ ጋር አትሠዋ የበዓሌም ስብ እስኪነጋ አይደር። |
18 Thou shalt not offer the blood of my sacrifice with leavened bread; neither shall the fat of my sacrifice remain until the morning. |
19 የተመረጠውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ። ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል። |
19 The first of the firstfruits of thy land thou shalt bring into the house of the Lord thy God. Thou shalt not seethe a kid in his mother’s milk. |
20 በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ። |
20 Behold, I send an Angel before thee, to keep thee in the way, and to bring thee into the place which I have prepared. |
21 በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት። |
21 Beware of him, and obey his voice, provoke him not; for he will not pardon your transgressions: for my name is in him. |
22 አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፥ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ። |
22 But if thou shalt indeed obey his voice, and do all that I speak; then I will be an enemy unto thine enemies, and an adversary unto thine adversaries. |
23 መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፥ ወደ አሞራውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ከነዓናውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ያገባሃል እኔም አጠፋቸዋለሁ። |
23 For mine Angel shall go before thee, and bring thee in unto the Amorites, and the Hittites, and the Perizzites, and the Canaanites, the Hivites, and the Jebusites: and I will cut them off. |
24 ለአማልክቶቻቸው አትስገድ፥ አታምልካቸውም እንደ ሥራቸውም አትሥራ ነገር ግን ፈጽመህ አፍርሳቸው፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብራቸው። |
24 Thou shalt not bow down to their gods, nor serve them, nor do after their works: but thou shalt utterly overthrow them, and quite break down their images. |
25 አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ታመልኩታላችሁ፥ እርሱም እህልህንና ውኃህን ይባርካል በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ። |
25 And ye shall serve the Lord your God, and he shall bless thy bread, and thy water; and I will take sickness away from the midst of thee. |
26 በምድርህም መካን ወይም የምትጨነግፍ አትሆንም የዘመንህን ቍጥር እሞላለሁ። |
26 There shall nothing cast their young, nor be barren, in thy land: the number of thy days I will fulfil. |
27 መፈራቴንም በፊትህ እሰድዳለሁ፥ የምትሄድበትንም ሕዝብ ሁሉ አስደነግጣቸዋለሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ በፊትህ ጀርባቸውን እንዲያዞሩ አደርጋለሁ። |
27 I will send my fear before thee, and will destroy all the people to whom thou shalt come, and I will make all thine enemies turn their backs unto thee. |
28 በፊትህም ተርብ እሰድዳለሁ፥ ኤዊያዊውንም ከነዓናዊውንም ኬጢያዊውንም ከፊትህ አባርራለሁ። |
28 And I will send hornets before thee, which shall drive out the Hivite, the Canaanite, and the Hittite, from before thee. |
29 ምድር ባድማ እንዳትሆን፥ የምድር አራዊትም እንዳይበዙብህ፥ በአንድ ዓመት ከፊታችሁ አላባርራቸውም። |
29 I will not drive them out from before thee in one year; lest the land become desolate, and the beast of the field multiply against thee. |
30 ነገር ግን እስክትበዛ ምድርንም እስክትወርስ ድረስ በጥቂት በጥቂት አባርራቸዋለሁ። |
30 By little and little I will drive them out from before thee, until thou be increased, and inherit the land. |
31 ድንበርህንም ከኤርትራ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳም እስከ ወንዙ ድረስ አደርጋለሁ በምድር የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና ከፊትህም ታባርራቸዋለሁ። |
31 And I will set thy bounds from the Red sea even unto the sea of the Philistines, and from the desert unto the river: for I will deliver the inhabitants of the land into your hand; and thou shalt drive them out before thee. |
32 ከእነርሱና ከአማልክቶቻቸው ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ። |
32 Thou shalt make no covenant with them, nor with their gods. |
33 አማልክቶቻቸውንም ብታመልክ ወጥመድ ይሆኑብሃልና እኔን እንድትበድል እንዳያደርጉህ በአገርህ አይቀመጡ። |
33 They shall not dwell in thy land, lest they make thee sin against me: for if thou serve their gods, it will surely be a snare unto thee. |