ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #24
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘጸአት 24

Exodus 24

1 ሙሴንም። አንተ አሮንም ናዳብም አብዩድም ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወደ እግዚአብሔር ውጡ፥ በሩቁም ስገዱ

1 And he said unto Moses, Come up unto the Lord, thou, and Aaron, Nadab, and Abihu, and seventy of the elders of Israel; and worship ye afar off.

2 ሙሴም ብቻውን ወደ እግዚአብሔር ይቅረብ፥ እነርሱ ግን አይቅረቡ ሕዝቡም ከእርሱ ጋር አይውጡ አለው።

2 And Moses alone shall come near the Lord: but they shall not come nigh; neither shall the people go up with him.

3 ሙሴም መጣ ለሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃሎች ሁሉ ሥርዓቱንም ሁሉ ነገረ ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ። እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እናደርጋለን ብለው መለሱ።

3 And Moses came and told the people all the words of the Lord, and all the judgments: and all the people answered with one voice, and said, All the words which the Lord hath said will we do.

4 ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ጻፈ ማለዳም ተነሣ፥ ከተራራውም በታች መሠዊያን፥ አሥራ ሁለትም ሐውልቶች ለአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ሠራ።

4 And Moses wrote all the words of the Lord, and rose up early in the morning, and builded an altar under the hill, and twelve pillars, according to the twelve tribes of Israel.

5 የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ ለእግዚአብሔርም ስለ ደኅንነት መሥዋዕት በሬዎችን እንዲሠዉ የእስራኤልን ልጆች ጐበዛዝት ሰደደ።

5 And he sent young men of the children of Israel, which offered burnt offerings, and sacrificed peace offerings of oxen unto the Lord.

6 ሙሴም የደሙን እኵሌታ ወስዶ በቆሬ ውስጥ አደረገው የደሙንም እኵሌታ በመሠዊያው ረጨው።

6 And Moses took half of the blood, and put it in basons; and half of the blood he sprinkled on the altar.

7 የቃል ኪዳኑንም መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ አነበበላቸው እርሱም፦ እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለንም አሉ።

7 And he took the book of the covenant, and read in the audience of the people: and they said, All that the Lord hath said will we do, and be obedient.

8 ሙሴም ደሙን ውስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው። በዚህ ቃል ሁሉ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ያደረገው የቃል ኪዳኑ ደም እነሆ አለ።

8 And Moses took the blood, and sprinkled it on the people, and said, Behold the blood of the covenant, which the Lord hath made with you concerning all these words.

9 ሙሴም አሮንም ናዳብም አብዩድም ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወጡ

9 Then went up Moses, and Aaron, Nadab, and Abihu, and seventy of the elders of Israel:

10 የእስራኤልንም አምላክ አዩ ከእግሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚያበራ እንደ ብሩህ ሰንፔር ድንጋይ የሚመስል ወለል ነበረ።

10 And they saw the God of Israel: and there was under his feet as it were a paved work of a sapphire stone, and as it were the body of heaven in his clearness.

11 እጁንም በእስራኤል አዛውንቶች ላይ አልዘረጋም እነርሱም እግዚአብሔርን አዩ፥ በሉም ጠጡም።

11 And upon the nobles of the children of Israel he laid not his hand: also they saw God, and did eat and drink.

12 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን እነርሱን ታስተምር ዘንድ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ አለው።

12 And the Lord said unto Moses, Come up to me into the mount, and be there: and I will give thee tables of stone, and a law, and commandments which I have written; that thou mayest teach them.

13 ሙሴና ሎሌው ኢያሱ ተነሡ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወጣ።

13 And Moses rose up, and his minister Joshua: and Moses went up into the mount of God.

14 ሽማግሌዎችንም። ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ በዚህ ቆዩን አሮንና ሖርም እነሆ ከእናንተ ጋር ናቸው፥ ነገረተኛም ቢኖር ወደ እነርሱ ይምጣ አላቸው።

14 And he said unto the elders, Tarry ye here for us, until we come again unto you: and, behold, Aaron and Hur are with you: if any man have any matters to do, let him come unto them.

15 ሙሴም ወደ ተራራ ወጣ፥ ደመናውም ተራራውን ሸፈነው።

15 And Moses went up into the mount, and a cloud covered the mount.

16 የእግዚአብሔርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ተቀመጠ፥ ደመናውም ስድስት ቀን ሸፈነው በሰባተኛውም ቀን ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።

16 And the glory of the Lord abode upon mount Sinai, and the cloud covered it six days: and the seventh day he called unto Moses out of the midst of the cloud.

17 በተራራው ራስ ላይ በእስራኤል ልጆች ፊት የእግዚአብሔር ክብር መታየት እንደሚያቃጥል እሳት ነበረ።

17 And the sight of the glory of the Lord was like devouring fire on the top of the mount in the eyes of the children of Israel.

18 ሙሴም ወደ ደመናው ውስጥ ገባ ወደ ተራራውም ወጣ ሙሴም በተራራው ላይ አርባ ቀን አርባ ሌሊትም ቆየ።

18 And Moses went into the midst of the cloud, and gat him up into the mount: and Moses was in the mount forty days and forty nights.