ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #25
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘጸአት 25

Exodus 25

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው።

1 And the Lord spake unto Moses, saying,

2 ስጦታ ያመጡልኝ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ተናገር በገዛ እጁ ሊሰጠኝ በልቡ ከሚያምረው ሰው ሁሉ መባ ተቀበሉ።

2 Speak unto the children of Israel, that they bring me an offering: of every man that giveth it willingly with his heart ye shall take my offering.

3 ከእነርሱም የምትቀበሉት መባ ይህ ነው

3 And this is the offering which ye shall take of them; gold, and silver, and brass,

4 ወርቅ፥ ብር፥ ናስም፥ ሰማያዊና ሐምራዊ ቀይም ግምጃ፥ ጥሩ በፍታም፥

4 And blue, and purple, and scarlet, and fine linen, and goats’ hair,

5 የፍየልም ጠጕር፥ ቀይ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአቆስጣ ቁርበት፥ የግራርም እንጨት፥

5 And rams’ skins dyed red, and badgers’ skins, and shittim wood,

6 የመብራትም ዘይት፥ ለቅብዓት ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን ቅመም፥

6 Oil for the light, spices for anointing oil, and for sweet incense,

7 መረግድም፥ ለኤፉድና ለደረት ኪስ የሚደረግ ፈርጥ።

7 Onyx stones, and stones to be set in the ephod, and in the breastplate.

8 በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ።

8 And let them make me a sanctuary; that I may dwell among them.

9 እኔ እንደማሳይህ ሁሉ፥ እንደ ማደሪያው ምሳሌ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ፥ እንዲሁ ሥሩት።

9 According to all that I shew thee, after the pattern of the tabernacle, and the pattern of all the instruments thereof, even so shall ye make it.

10 ከግራር እንጨትም ታቦትን ይሥሩ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።

10 And they shall make an ark of shittim wood: two cubits and a half shall be the length thereof, and a cubit and a half the breadth thereof, and a cubit and a half the height thereof.

11 በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው በእርሱም ላይ በዙሪያው የወርቅ አክሊል አድርግለት።

11 And thou shalt overlay it with pure gold, within and without shalt thou overlay it, and shalt make upon it a crown of gold round about.

12 አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፥ እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኑር በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላው ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ።

12 And thou shalt cast four rings of gold for it, and put them in the four corners thereof; and two rings shall be in the one side of it, and two rings in the other side of it.

13 መሎጊያዎችንም ከግራር እንጨት ሥራ፥ በወርቅም ለብጣቸው።

13 And thou shalt make staves of shittim wood, and overlay them with gold.

14 ለታቦቱ መሸከሚያ በታቦቱ ጐን ባሉት ቀለበቶች መሎጊያዎቹን አግባ።

14 And thou shalt put the staves into the rings by the sides of the ark, that the ark may be borne with them.

15 መሎጊያዎቹም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ ይኑሩ፥ ከቶም አይውጡ።

15 The staves shall be in the rings of the ark: they shall not be taken from it.

16 በታቦቱም ውስጥ እኔ የምሰጥህን ምስክር ታስቀምጣለህ።

16 And thou shalt put into the ark the testimony which I shall give thee.

17 ከጥሩ ወርቅም ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ሥራ።

17 And thou shalt make a mercy seat of pure gold: two cubits and a half shall be the length thereof, and a cubit and a half the breadth thereof.

18 ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፥ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ።

18 And thou shalt make two cherubims of gold, of beaten work shalt thou make them, in the two ends of the mercy seat.

19 ከስርየት መክደኛውም ጋር አንዱን ኪሩብ በአንድ ወገን፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ወገን አድርገህ በአንድ ላይ ትሠራዋለህ።

19 And make one cherub on the one end, and the other cherub on the other end: even of the mercy seat shall ye make the cherubims on the two ends thereof.

20 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፥ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው ይመለከታሉ።

20 And the cherubims shall stretch forth their wings on high, covering the mercy seat with their wings, and their faces shall look one to another; toward the mercy seat shall the faces of the cherubims be.

21 የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ እኔም የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታኖረዋለህ።

21 And thou shalt put the mercy seat above upon the ark; and in the ark thou shalt put the testimony that I shall give thee.

22 በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ የእስራኤልንም ልጆች ታዝዝ ዘንድ የምሰጥህን ነገር ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛውም ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ።

22 And there I will meet with thee, and I will commune with thee from above the mercy seat, from between the two cherubims which are upon the ark of the testimony, of all things which I will give thee in commandment unto the children of Israel.

23 ርዝመቱም ሁለት ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ፥ ቁመቱ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ገበታ ከግራር እንጨት ሥራ።

23 Thou shalt also make a table of shittim wood: two cubits shall be the length thereof, and a cubit the breadth thereof, and a cubit and a half the height thereof.

24 በጥሩም ወርቅ ትለብጠዋለህ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አድርግለት

24 And thou shalt overlay it with pure gold, and make thereto a crown of gold round about.

25 በዙሪያውም አንድ ጋት የሚያህል ክፈፍ አድርግለት የወርቅም አክሊል በክፈፉ ዙሪያ አድርግለት።

25 And thou shalt make unto it a border of an hand breadth round about, and thou shalt make a golden crown to the border thereof round about.

26 አራትም የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት ቀለበቶቹንም አራቱ እግሮቹ ባሉበት በአራቱ ማዕዘኖች አድርግ።

26 And thou shalt make for it four rings of gold, and put the rings in the four corners that are on the four feet thereof.

27 ገበታውንም ለመሸከም መሎጊያዎቹ እንዲሰኩባቸው ቀለበቶቹ በክፈፉ አቅራቢያ ይሁኑ።

27 Over against the border shall the rings be for places of the staves to bear the table.

28 ገበታውን ይሸከሙባቸው ዘንድ መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው።

28 And thou shalt make the staves of shittim wood, and overlay them with gold, that the table may be borne with them.

29 ለማፍሰሻም ይሆኑ ዘንድ ወጭቶችዋን ጭልፋዎችዋንም መቅጃዎችዋንም ጽዋዎችዋንም አድርግ እነርሱንም ከጥሩ ወርቅ አድርጋቸው።

29 And thou shalt make the dishes thereof, and spoons thereof, and covers thereof, and bowls thereof, to cover withal: of pure gold shalt thou make them.

30 በገበታም ላይ የገጽ ኅብስት ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ።

30 And thou shalt set upon the table shewbread before me alway.

31 መቅረዝንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ መቅረዙ ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀጠቀጠ ሥራ ይደረግ ጽዋዎቹም ጕብጕቦቹም አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት።

31 And thou shalt make a candlestick of pure gold: of beaten work shall the candlestick be made: his shaft, and his branches, his bowls, his knops, and his flowers, shall be of the same.

32 በስተጎኑ ስድስት ቅርንጫፎች ይውጡለት ሦስት የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስትም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ ወገን ይውጡ።

32 And six branches shall come out of the sides of it; three branches of the candlestick out of the one side, and three branches of the candlestick out of the other side:

33 በአንደኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕብና አበባ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕብና አበባ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች እንዲሁም ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አድርግ።

33 Three bowls made like unto almonds, with a knop and a flower in one branch; and three bowls made like almonds in the other branch, with a knop and a flower: so in the six branches that come out of the candlestick.

34 በመቅረዙም ጕብጕቦቹንና አበቦቹን አራትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች አድርግ።

34 And in the candlestick shall be four bowls made like unto almonds, with their knops and their flowers.

35 ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ፥ ከሁለትም ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ፥ ደግሞ ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ ይሁን።

35 And there shall be a knop under two branches of the same, and a knop under two branches of the same, and a knop under two branches of the same, according to the six branches that proceed out of the candlestick.

36 ጕብጕቦቹና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከእርሱ ጋር አንድ ይሁኑ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተቀረጸ ከጥሩ ወርቅ ይደረግ።

36 Their knops and their branches shall be of the same: all it shall be one beaten work of pure gold.

37 ሰባቱንም መብራቶች ሥራ በፊቱ ያበሩ ዘንድ መብራቶቹን ያቀጣጥሉአቸዋል።

37 And thou shalt make the seven lamps thereof: and they shall light the lamps thereof, that they may give light over against it.

38 መኰስተሪያዎችዋን የኵስታሪ ማድረጊያዎችዋንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ።

38 And the tongs thereof, and the snuffdishes thereof, shall be of pure gold.

39 መቅረዙም ዕቃውም ሁሉ ከአንድ መክሊት ጥሩ ወርቅ ይሠሩ።

39 Of a talent of pure gold shall he make it, with all these vessels.

40 በተራራ ላይ እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንድትሠራ ተጠንቀቅ።

40 And look that thou make them after their pattern, which was shewed thee in the mount.