ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #22
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘሌዋውያን 22

Leviticus 22

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

1 And the Lord spake unto Moses, saying,

2 የእስራኤል ልጆች ለእኔ ከሚቀድሱአቸው ከቅዱሳን ነገሮች ራሳቸውን እንዲለዩ፥ የተቀደሰውንም ስሜን እንዳያረክሱ ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

2 Speak unto Aaron and to his sons, that they separate themselves from the holy things of the children of Israel, and that they profane not my holy name in those things which they hallow unto me: I am the Lord.

3 እንዲህ በላቸው። ማናቸውም ሰው ከዘራችሁ በትውልዳችሁ ርኵሰት እያለበት የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር ወደሚቀድሱት ወደ ቅዱስ ነገር ቢቀርብ፥ ያ ሰው ከፊቴ ተለይቶ ይጥፋ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

3 Say unto them, Whosoever he be of all your seed among your generations, that goeth unto the holy things, which the children of Israel hallow unto the Lord, having his uncleanness upon him, that soul shall be cut off from my presence: I am the Lord.

4 ከአሮን ዘር ለምጽ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለበት ሁሉ ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ከተቀደሰው አይብላ። ከበድንም የተነሣ ርኩስ የሆነውን፥ ወይም ዘሩ ከእርሱ የሚፈስስበትን የሚነካ፥

4 What man soever of the seed of Aaron is a leper, or hath a running issue; he shall not eat of the holy things, until he be clean. And whoso toucheth any thing that is unclean by the dead, or a man whose seed goeth from him;

5 ወይም የሚያረክሰውን ተንቀሳቃሽ፥ ወይም በሁሉ ዓይነት የረከሰውን ሰው የሚነካ፥

5 Or whosoever toucheth any creeping thing, whereby he may be made unclean, or a man of whom he may take uncleanness, whatsoever uncleanness he hath;

6 እነዚህን ሁሉ የሚነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል ገላውን በውኃ ካልታጠበ ከተቀደሰው አይብላ።

6 The soul which hath touched any such shall be unclean until even, and shall not eat of the holy things, unless he wash his flesh with water.

7 ፀሐይም በገባች ጊዜ ንጹሕ ይሆናል ከዚያም በኋላ እንጀራው ነውና ከተቀደሰው ይብላ።

7 And when the sun is down, he shall be clean, and shall afterward eat of the holy things; because it is his food.

8 በእርሱም እንዳይረክስ፥ የሞተውን አውሬም የሰበረውን አይብላ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

8 That which dieth of itself, or is torn with beasts, he shall not eat to defile himself therewith: I am the Lord.

9 ቢያረክሱአት እንዳይሞቱ ስለ እርስዋም ኃጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ሕግን ይጠብቁ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

9 They shall therefore keep mine ordinance, lest they bear sin for it, and die therefore, if they profane it: I the Lord do sanctify them.

10 ልዩ ሰው ከተቀደሰው አይብላ የካህኑም እንግዳ ደመወዘኛውም ከተቀደሰው አይብላ።

10 There shall no stranger eat of the holy thing: a sojourner of the priest, or an hired servant, shall not eat of the holy thing.

11 ካህኑ ግን በገንዘቡ ባሪያ ቢገዛ እርሱ ይብላው በቤቱም የተወለዱት ከእንጀራው ይብሉ።

11 But if the priest buy any soul with his money, he shall eat of it, and he that is born in his house: they shall eat of his meat.

12 የካህንም ልጅ ከልዩ ሰው ጋር ብትጋባ፥ እርስዋ ከተቀደሰው ቍርባን አትብላ።

12 If the priest’s daughter also be married unto a stranger, she may not eat of an offering of the holy things.

13 የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነትዋ እንደ ነበረች ወደ አባትዋ ቤት ብትመለስ፥ ከአባትዋ እንጀራ ትብላ ልዩ ሰው ግን ከእርሱ አይብላ።

13 But if the priest’s daughter be a widow, or divorced, and have no child, and is returned unto her father’s house, as in her youth, she shall eat of her father’s meat: but there shall no stranger eat thereof.

14 ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ከተቀደሰው ቢበላ አምስተኛ እጅ ጨምሮ የተቀደሰውን ለካህኑ ይስጥ።

14 And if a man eat of the holy thing unwittingly, then he shall put the fifth part thereof unto it, and shall give it unto the priest with the holy thing.

15-16 የምቀድሳቸውም እግዚአብሔር እኔ ነኝና ከተቀደሰው በበሉ ጊዜ ኃጢአትንና በደልን እንዳይሸከሙ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡትን በእስራኤል ልጆች ዘንድ የተቀደሰውን ነገር አያርክሱ።

15 And they shall not profane the holy things of the children of Israel, which they offer unto the Lord;
16 Or suffer them to bear the iniquity of trespass, when they eat their holy things: for I the Lord do sanctify them.

17 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

17 And the Lord spake unto Moses, saying,

18 ለአሮንና ለልጆቹ ለእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው። ከእስራኤል ቤት ወይም ከእናንተ መካከል ከሚቀመጡት እንግዶች ማናቸውም ሰው ስእለቱን ሁሉ፥ በፈቃዱም የሚያቀርበውን ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርበውን ቍርባን ቢያቀርብ፥

18 Speak unto Aaron, and to his sons, and unto all the children of Israel, and say unto them, Whatsoever he be of the house of Israel, or of the strangers in Israel, that will offer his oblation for all his vows, and for all his freewill offerings, which they will offer unto the Lord for a burnt offering;

19 ይሠምርላችሁ ዘንድ ከበሬ ወይም ከበግ ወይም ከፍየል ነውር የሌለበትን ተባቱን አቅርቡ።

19 Ye shall offer at your own will a male without blemish, of the beeves, of the sheep, or of the goats.

20 ነገር ግን አይሠምርላችሁምና ነውር ያለበትን አታቅርቡ።

20 But whatsoever hath a blemish, that shall ye not offer: for it shall not be acceptable for you.

21 ማናቸውም ሰው ስእለቱን ለመፈጸም ወይም በፈቃዱ ለማቅረብ የደኅንነትን መሥዋዕት፥ ወይም በሬን ወይም በግን፥ ለእግዚአብሔር ቢያቀርብ፥ ይሠምርለት ዘንድ ፍጹም ይሁን፥ ነውርም አይሁንበት።

21 And whosoever offereth a sacrifice of peace offerings unto the Lord to accomplish his vow, or a freewill offering in beeves or sheep, it shall be perfect to be accepted; there shall be no blemish therein.

22 ዕውር ወይም ሰባራ ወይም ጕንድሽ ወይም የሚመግል ቍስል ያለበት ወይም እከካም ወይም ቋቍቻም ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ ለእግዚአብሔር አታቅርቡ እነዚህም ለእሳት ቍርባን በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር አታሳርጉ።

22 Blind, or broken, or maimed, or having a wen, or scurvy, or scabbed, ye shall not offer these unto the Lord, nor make an offering by fire of them upon the altar unto the Lord.

23 በሬው ወይም በጉ የተጨመረበት ወይም የጐደለበት ነገር ቢሆን፥ ለፈቃድ መሥዋዕት ማቅረብ ትችላለህ ለስእለት ግን አይሠምርም።

23 Either a bullock or a lamb that hath any thing superfluous or lacking in his parts, that mayest thou offer for a freewill offering; but for a vow it shall not be accepted.

24 የተሰነጋውን ወይም የተቀጠቀጠውን ወይም የተሰበረውን ወይም የተቈረጠውን ለእግዚአብሔር አታቅርቡ በምድራችሁም እነዚህን አትሠዉ።

24 Ye shall not offer unto the Lord that which is bruised, or crushed, or broken, or cut; neither shall ye make any offering thereof in your land.

25 ከእነዚህም ከእንግዳ ሰው እጅ ለአምላካችሁ እንጀራ አታቅርቡ ርኵሰትም ነውርም አለባቸውና አይሠምሩላችሁም።

25 Neither from a stranger’s hand shall ye offer the bread of your God of any of these; because their corruption is in them, and blemishes be in them: they shall not be accepted for you.

26 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

26 And the Lord spake unto Moses, saying,

27 በሬ ወይም በግ ወይም ፍየል ሲወለድ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ በስምንተኛውም ቀን ከዚያም በላይ ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን የሠመረ ይሆናል።

27 When a bullock, or a sheep, or a goat, is brought forth, then it shall be seven days under the dam; and from the eighth day and thenceforth it shall be accepted for an offering made by fire unto the Lord.

28 ላም ወይም በግ ብትሆን እርስዋንና ልጅዋን በአንድ ቀን አትረዱ።

28 And whether it be cow or ewe, ye shall not kill it and her young both in one day.

29 የምስጋናንም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ስትሠዉ እንዲሠምርላችሁ ሠዉለት።

29 And when ye will offer a sacrifice of thanksgiving unto the Lord, offer it at your own will.

30 በዚያው ቀን ይበላል ከእርሱ እስከ ነገ ምንም አትተዉ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

30 On the same day it shall be eaten up; ye shall leave none of it until the morrow: I am the Lord.

31 ትእዛዛቴን ጠብቁ፥ አድርጉትም እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

31 Therefore shall ye keep my commandments, and do them: I am the Lord.

32 የተቀደሰውንም ስሜን አታርክሱ እኔ ግን በእስራኤል ልጆች መካከል እቀደሳለሁ

32 Neither shall ye profane my holy name; but I will be hallowed among the children of Israel: I am the Lord which hallow you,

33 የምቀድሳችሁ፥ አምላካችሁም እሆን ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር ነኝ። እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

33 That brought you out of the land of Egypt, to be your God: I am the Lord.