ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #28
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘኍልቍ 28

Numbers 28

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

1 And the Lord spake unto Moses, saying,

2 የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው። መብሌን፥ ለእኔ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት የተደረገውን ቍርባኔን፥ መባዬን በየጊዜው ታቀርቡልኝ ዘንድ ጠብቁ።

2 Command the children of Israel, and say unto them, My offering, and my bread for my sacrifices made by fire, for a sweet savour unto me, shall ye observe to offer unto me in their due season.

3 እንዲህም በላቸው። በእሳት ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት ቍርባን ይህ ነው ለዘወትር ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ።

3 And thou shalt say unto them, This is the offering made by fire which ye shall offer unto the Lord; two lambs of the first year without spot day by day, for a continual burnt offering.

4 አንዱን ጠቦት በማለዳ፥ ሌላውንም ጠቦት በማታ አቅርብ

4 The one lamb shalt thou offer in the morning, and the other lamb shalt thou offer at even;

5 ለእህልም ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት ታቀርባለህ።

5 And a tenth part of an ephah of flour for a meat offering, mingled with the fourth part of an hin of beaten oil.

6 በእሳት ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የቀረበ በሲና ተራራ የተሠራ ለዘወትር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።

6 It is a continual burnt offering, which was ordained in mount Sinai for a sweet savour, a sacrifice made by fire unto the Lord.

7 የመጠጡ ቍርባን ለአንድ ጠቦት የኢን መስፈሪያ አራተኛው እጅ ነው በመቅደሱ ውስጥ ለእግዚአብሔር ለመጠጥ ቍርባን መጠጥ ታፈስሳለህ።

7 And the drink offering thereof shall be the fourth part of an hin for the one lamb: in the holy place shalt thou cause the strong wine to be poured unto the Lord for a drink offering.

8 ሌላውንም ጠቦት በማታ ጊዜ ታቀርባለህ የእህሉን ቍርባንና የመጠጡን ቍርባን በማለዳ እንዳቀረብህ በእሳት ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ታቀርበዋለህ።

8 And the other lamb shalt thou offer at even: as the meat offering of the morning, and as the drink offering thereof, thou shalt offer it, a sacrifice made by fire, of a sweet savour unto the Lord.

9 በሰንበትም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ ለእህልም ቍርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ የመጠጡንም ቍርባን ታቀርባላችሁ።

9 And on the sabbath day two lambs of the first year without spot, and two tenth deals of flour for a meat offering, mingled with oil, and the drink offering thereof:

10 በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ፥ በየሰንበቱ ሁሉ የምታቀርቡት የሚቃጠለው መሥዋዕት ይህ ነው።

10 This is the burnt offering of every sabbath, beside the continual burnt offering, and his drink offering.

11 በወሩም መባቻ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ ሁለት ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውርም የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥

11 And in the beginnings of your months ye shall offer a burnt offering unto the Lord; two young bullocks, and one ram, seven lambs of the first year without spot;

12 ለእያንዳንዱም ወይፈን ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሦስት እጅ መልካም ዱቄት፥ ለአውራው በግም ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥

12 And three tenth deals of flour for a meat offering, mingled with oil, for one bullock; and two tenth deals of flour for a meat offering, mingled with oil, for one ram;

13 ለእያንዳንዱም ጠቦት ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት ታቀርባላችሁ።

13 And a several tenth deal of flour mingled with oil for a meat offering unto one lamb; for a burnt offering of a sweet savour, a sacrifice made by fire unto the Lord.

14 የመጠጥ ቍርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሢሶ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።

14 And their drink offerings shall be half an hin of wine unto a bullock, and the third part of an hin unto a ram, and a fourth part of an hin unto a lamb: this is the burnt offering of every month throughout the months of the year.

15 ለእግዚአብሔርም ለኃጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቍርባን ሌላ ይቀርባል።

15 And one kid of the goats for a sin offering unto the Lord shall be offered, beside the continual burnt offering, and his drink offering.

16 በመጀመሪያው ወር ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው።

16 And in the fourteenth day of the first month is the passover of the Lord.

17 ከዚህም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ።

17 And in the fifteenth day of this month is the feast: seven days shall unleavened bread be eaten.

18 በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሆናል በእርሱም የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።

18 In the first day shall be an holy convocation; ye shall do no manner of servile work therein:

19 በእሳትም የተደረገውን ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት ታቀርባላችሁ ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነውር የሌለባቸው ይሁኑላችሁ።

19 But ye shall offer a sacrifice made by fire for a burnt offering unto the Lord; two young bullocks, and one ram, and seven lambs of the first year: they shall be unto you without blemish:

20 የእህል ቍርባናቸውንም በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለአንድ ወይፈን ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአውራውም በግ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ፥

20 And their meat offering shall be of flour mingled with oil: three tenth deals shall ye offer for a bullock, and two tenth deals for a ram;

21 ለሰባቱም ጠቦቶች ለእያንዳንዱ ጠቦት ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ ታቀርባላችሁ።

21 A several tenth deal shalt thou offer for every lamb, throughout the seven lambs:

22 ማስተስረያ የሚሆንላችሁን አንድ አውራ ፍየል ለኃጢአት መሥዋዕት ታቀርባላችሁ።

22 And one goat for a sin offering, to make an atonement for you.

23 ማልዶ ከሚቀርበው በዘወትር ከሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ እነዚህን ታቀርባላችሁ።

23 Ye shall offer these beside the burnt offering in the morning, which is for a continual burnt offering.

24 ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚደረገውን የቍርባኑን መብል ሰባት ቀን በየዕለቱ እንዲሁ ታቀርባላችሁ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቍርባን ሌላ ይቀርባል።

24 After this manner ye shall offer daily, throughout the seven days, the meat of the sacrifice made by fire, of a sweet savour unto the Lord: it shall be offered beside the continual burnt offering, and his drink offering.

25 በሰባተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።

25 And on the seventh day ye shall have an holy convocation; ye shall do no servile work.

26 ደግሞ በበኵራት ቀን ከሰባቱ ሱባዔ በዓላችሁ አዲሱን የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ባቀረባችሁ ጊዜ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይሆንላችኋል የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።

26 Also in the day of the firstfruits, when ye bring a new meat offering unto the Lord, after your weeks be out, ye shall have an holy convocation; ye shall do no servile work:

27 ለእግዚአብሔርም ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ታቀርባላችሁ ሁለት ወይፈኖች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥

27 But ye shall offer the burnt offering for a sweet savour unto the Lord; two young bullocks, one ram, seven lambs of the first year;

28 ለእህል ቍርባናቸው በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለእያንዳንዱ ወይፈን ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአንዱም አውራ በግ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ፥

28 And their meat offering of flour mingled with oil, three tenth deals unto one bullock, two tenth deals unto one ram,

29 ለሰባቱም ጠቦቶች ለእያንዳንዱ ጠቦት ከመስፈሪያው አሥረኛ እጅ ታቀርባላችሁ።

29 A several tenth deal unto one lamb, throughout the seven lambs;

30 ማስተስረያ የሚሆንላችሁን አንድ አውራ ፍየል ለኃጢአት መሥዋዕት ታቀርባላችሁ።

30 And one kid of the goats, to make an atonement for you.

31 በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ሌላ እነርሱንና የመጠጥ ቍርባናቸውን ታቀርባላችሁ ነውርም የሌለባቸው ይሁኑ።

31 Ye shall offer them beside the continual burnt offering, and his meat offering, (they shall be unto you without blemish) and their drink offerings.