ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #44
In Amharic and English
ኦሪት ዘፍጥረት 44 |
Genesis 44 |
1 ዮሴፍም የቤቱን አዛዥ እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ ዓይበታቸው የሚያነሣውን ያህል እህል ሙላላቸው፥ የሁሉንም ብር በየዓይበታቸው አፍ ጨምረው |
1 And he commanded the steward of his house, saying, Fill the men’s sacks with food, as much as they can carry, and put every man’s money in his sack’s mouth. |
2 በታናሹም ዓይበት አፍ የብሩን ጽዋዬንና የእህሉን ዋጋ ጨምረው። እርሱም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ። |
2 And put my cup, the silver cup, in the sack’s mouth of the youngest, and his corn money. And he did according to the word that Joseph had spoken. |
3 ነግህ በሆነ ጊዜም ሰዎቹ አህዮቻቸውን ይዘው ይሄዱ ዘንድ ተሰናበቱ። |
3 As soon as the morning was light, the men were sent away, they and their asses. |
4 ከከተማይቱም ወጥተው ገና ሳይርቁ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ አለ፦ ተነሥተህ ሰዎቹን ተከተላቸው በደረስህባቸውም ጊዜ እንዲህ በላቸው። በመልካሙ ፋንታ ስለ ምን ክፉን መለሳችሁ? |
4 And when they were gone out of the city, and not yet far off, Joseph said unto his steward, Up, follow after the men; and when thou dost overtake them, say unto them, Wherefore have ye rewarded evil for good? |
5 ጌታዬ የሚጠጣበት ምሥጢርንም የሚያውቅበት ጽዋ አይደለምን? ባደረጋችሁት ነገር በደላችሁ። |
5 Is not this it in which my lord drinketh, and whereby indeed he divineth? ye have done evil in so doing. |
6 እርሱም ደርሰባቸው ይህንም ቃል ነገራቸው። |
6 And he overtook them, and he spake unto them these same words. |
7 እነርሱም አሉት። ጌታዬ እንደዚህ ያለውን ቃል ለምን ይናገራል? ባሪያዎችህ ይህን ነገር የሚያደርጉ አይደሉም። |
7 And they said unto him, Wherefore saith my lord these words? God forbid that thy servants should do according to this thing: |
8 እነሆ፥ በዓይበታችን አፍ ያገኘነውን ብር ይዘን ከከነዓን አገር ወደ አንተ ተመልሰናል ከጌታህ ቤት ወርቅ ወይስ ብር እንዴት እንሰርቃለን? |
8 Behold, the money, which we found in our sacks’ mouths, we brought again unto thee out of the land of Canaan: how then should we steal out of thy lord’s house silver or gold? |
9 ከባሪያዎችህ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ይሙት እኛም ደግሞ ለጌታችን ባሪያዎች እንሁን። |
9 With whomsoever of thy servants it be found, both let him die, and we also will be my lord’s bondmen. |
10 እርሱም አለ፦ አሁንም እንዲሁ እንደ ነገራችሁ ይሁን ጽዋው የተገኘበት እርሱ ለእኔ ባሪያ ይሁነኝ፥ እናንተም ንጹሐን ትሆናላችሁ። |
10 And he said, Now also let it be according unto your words: he with whom it is found shall be my servant; and ye shall be blameless. |
11 እየራሳቸውም ፈጥነው ዓይበታቸውን ወደ ምድር አወረዱ፥ እየራሳቸውም ዓይበታቸውን ፈቱ። |
11 Then they speedily took down every man his sack to the ground, and opened every man his sack. |
12 እርሱም ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በረበራቸው፥ ጽዋውንም በብንያም ዓይበት ውስጥ አገኘው። |
12 And he searched, and began at the eldest, and left at the youngest: and the cup was found in Benjamin’s sack. |
13 ልብሳቸውንም ቀደዱ፥ ዓይበታቸውንም በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማይቱ ተመለሱ። |
13 Then they rent their clothes, and laded every man his ass, and returned to the city. |
14 ይሁዳም ከወንድሞቹ ጋር ወደ ዮሴፍ ገባ፥ እርሱም ገና ከዚያው ነበረ በፊቱም በምድር ላይ ወደቁ። |
14 And Judah and his brethren came to Joseph’s house; for he was yet there: and they fell before him on the ground. |
15 ዮሴፍም። ይህ ያደረጋችሁት ነገር ምንድር ነው? እንደ እኔ ያለ ሰው ምሥጢርን እንዲያውቅ አታውቁምን? አላቸው። |
15 And Joseph said unto them, What deed is this that ye have done? wot ye not that such a man as I can certainly divine? |
16 ይሁዳም አለ። ለጌታዬ ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይስ በምን እንነጻለን? እግዚአብሔር የባሪያዎችህን ኃጢአት ገለጠ እነሆ፥ እኛም ጽዋው ከእርሱ ዘንድ የተገኘበቱም ደግሞ ለጌታዬ ባሪያዎቹ ነን። |
16 And Judah said, What shall we say unto my lord? what shall we speak? or how shall we clear ourselves? God hath found out the iniquity of thy servants: behold, we are my lord’s servants, both we, and he also with whom the cup is found. |
17 እርሱም እላቸው። ይህን አደርግ ዘንድ አይሆንልኝም ጽዋው የተገኘበቱ ሰው እርሱ ባሪያ ይሁነኝ እናንተም ወደ አባታችሁ በደኅና ውጡ። |
17 And he said, God forbid that I should do so: but the man in whose hand the cup is found, he shall be my servant; and as for you, get you up in peace unto your father. |
18 ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበእንዲህም አለ፦ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ ባርያህ በጌታዬ ጆሮ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ እኔንም ባሪያህን አትቆጣኝ አንተ እንደ ፈርዖን ነህና። |
18 Then Judah came near unto him, and said, Oh my lord, let thy servant, I pray thee, speak a word in my lord’s ears, and let not thine anger burn against thy servant: for thou art even as Pharaoh. |
19 ጌታዬ ባሪያዎቹን፦ አባት አላችሁን ወይስ ወንድም? ብሎ ጠየቀ። |
19 My lord asked his servants, saying, Have ye a father, or a brother? |
20 እኛም ለጌታዬ እንዲህ አልነ። ሸማግሌ አባት አለን፥ በሽምግልናው የወለደውም ታናሽ ብላቴና አለ ወንድሙም ሞተ፥ ከእናቱም እርሱ ብቻውን ቀረ፥ አባቱም ይወድደዋል። |
20 And we said unto my lord, We have a father, an old man, and a child of his old age, a little one; and his brother is dead, and he alone is left of his mother, and his father loveth him. |
21 አንተም ለባሪያዎችህ። ወደ እኔ አምጡት፥ እኔም አየዋለሁ አልህ። |
21 And thou saidst unto thy servants, Bring him down unto me, that I may set mine eyes upon him. |
22 ጌታዬንም። ብላቴናው አባቱን መተው አይሆንለትም የተወው እንደ ሆነ አባቱ ይሞታልና አልነው። |
22 And we said unto my lord, The lad cannot leave his father: for if he should leave his father, his father would die. |
23 ባርያዎችህንም። ታናሽ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልመጣ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም አልኽን። |
23 And thou saidst unto thy servants, Except your youngest brother come down with you, ye shall see my face no more. |
24 ወደ ባርያህ ወደ አባታችን በተመለስን ጊዜም የጌታዬን ቃል ነገርነው። |
24 And it came to pass when we came up unto thy servant my father, we told him the words of my lord. |
25 አባታችንም። ተመልሳችሁ ጥቂት እህል ሸምቱልን አለ። |
25 And our father said, Go again, and buy us a little food. |
26 እኛም አልነው። እንሄድ ዘንድ አይሆንልንም ታናሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ይወርድ እንደ ሆነ እኛም እንወርዳለን ታናሹ ወንድማችን ከእኛ ጋር ከሌለ የዚያን ሰው ፊት ማየት አይቻለንምና። |
26 And we said, We cannot go down: if our youngest brother be with us, then will we go down: for we may not see the man’s face, except our youngest brother be with us. |
27 ባሪያህ አባቴም እንዲህ አለን፦ ሚስቴ ሁለት ወንዶች ልጆችን እንደ ወለደችልኝ እናንተ ታውቃላችሁ |
27 And thy servant my father said unto us, Ye know that my wife bare me two sons: |
28 አንዱም ከእኔ ወጣ። አውሬ በላው አላችሁኝ፥ እስከ ዛሬም አላየሁትም |
28 And the one went out from me, and I said, Surely he is torn in pieces; and I saw him not since: |
29 ይህንም ከእኔ ለይታችሁ ደግሞ ብትወስዱት ክፋም ቢያገኘው፥ ሽበቴን በኅዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ። |
29 And if ye take this also from me, and mischief befall him, ye shall bring down my gray hairs with sorrow to the grave. |
30 አሁንም እኔ ወደ አባቴ ወደ ባሪያህ ብሄድ፥ ብላቴናውም ከእኛ ጋር ከሌለ፥ ነፍሱ በብላቴናው ነፍስ ታስራለችና ብላቴናው ከእኛ ጋር እንደሌለ ባየ ጊዜ ይሞታል |
30 Now therefore when I come to thy servant my father, and the lad be not with us; seeing that his life is bound up in the lad’s life; |
31 ባሪያዎችህም የባሪያህን የአባታችንን ሽበት በኅዘን ወደ መቃብር ያወርዳሉ። |
31 It shall come to pass, when he seeth that the lad is not with us, that he will die: and thy servants shall bring down the gray hairs of thy servant our father with sorrow to the grave. |
32 እኔ ባሪያህ በአባቴ ዘንድ ስለ ብላቴናው እንዲህ ብዬ ተውሼአለሁና። እርሱንስ ወደ አንተ ባላመጣው በአባቴ ዘንድ በዘመናት ሁሉ ኃጢአተኛ እሆናለሁ። |
32 For thy servant became surety for the lad unto my father, saying, If I bring him not unto thee, then I shall bear the blame to my father for ever. |
33 ስለዚህም እኔ ባሪያህ በጌታዬ ዘንድ ባሪያ ሆኜ በብላቴናው ፋንታ ልቀመጥ ብላቴናውም ከወንድሞቹ ጋር ይውጣ። |
33 Now therefore, I pray thee, let thy servant abide instead of the lad a bondman to my lord; and let the lad go up with his brethren. |
34 አለዚያም ብላቴናው ከእኔ ጋር ከሌለ ወደ አባቴ እንዴት እወጣለሁ? አባቴን የሚያገኘውን መከራ እንዳላይ። |
34 For how shall I go up to my father, and the lad be not with me? lest peradventure I see the evil that shall come on my father. |