መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #75
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 75 |
Psalm 75 |
1 አቤቱ፥ እናመሰግንሃለን እናመሰግንሃለን ስምህንም እንጠራለን ተኣምራትህን ሁሉ እናገራለሁ። |
1 Unto thee, O God, do we give thanks, unto thee do we give thanks: for that thy name is near thy wondrous works declare. |
2 ጊዜውን ስቀበል እኔ በቅን እፈርዳለሁ። |
2 When I shall receive the congregation I will judge uprightly. |
3 ምድርና በእርስዋ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ ቀለጡ፥ እኔም ምሰሶችዋን አጠናሁ። |
3 The earth and all the inhabitants thereof are dissolved: I bear up the pillars of it. Selah. |
4 ዓመፀኞችን፦ አትበድሉ አልኋቸው፥ ኃጢአተኞችንም። ቀንዳችሁን አታንሡ |
4 I said unto the fools, Deal not foolishly: and to the wicked, Lift not up the horn: |
5 ቀንዳችሁን እስከ ላይ አታንሡ፥ በእግዚአብሔርም ላይ ዓመፅን አትናገሩ። |
5 Lift not up your horn on high: speak not with a stiff neck. |
6 ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድረ በዳ የለምና |
6 For promotion cometh neither from the east, nor from the west, nor from the south. |
7 እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ይህን ያዋርዳል ይህንም ያከብራል። |
7 But God is the judge: he putteth down one, and setteth up another. |
8 ጽዋ በእግዚአብሔር እጅ ነውና ያልተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሞላበት ከዚህ ወደዚያ አገላበጠው፥ ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም የምድር ኃጢአተኞች ሁሉ ይጠጡታል። |
8 For in the hand of the Lord there is a cup, and the wine is red; it is full of mixture; and he poureth out of the same: but the dregs thereof, all the wicked of the earth shall wring them out, and drink them. |
9 እኔ ግን ለዘላለም ደስ ይለኛል፥ ለያዕቆብም አምላክ ዝማሬን አቀርባለሁ። |
9 But I will declare for ever; I will sing praises to the God of Jacob. |
10 የኅጥኣንን ቀንዶች ሁሉ እሰብራለሁ የጻድቃን ቀንዶች ግን ከፍ ከፍ ይላሉ። |
10 All the horns of the wicked also will I cut off; but the horns of the righteous shall be exalted. |