ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #20
In Amharic and English
ኦሪት ዘፍጥረት 20 |
Genesis 20 |
1 አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ አዜብ ምድር ሄደ፥ በቃዴስና በሱር መካከልም ተቀመጠ በጌራራም በእንግድነት ተቀመጠ። |
1 And Abraham journeyed from thence toward the south country, and dwelled between Kadesh and Shur, and sojourned in Gerar. |
2 አብርሃምም ሚስቱን ሣራን፦ እኅቴ ናት አለ የጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክም ላከና ሣራን ወሰዳት። |
2 And Abraham said of Sarah his wife, She is my sister: and Abimelech king of Gerar sent, and took Sarah. |
3 እግዚአብሔርም ሌሊት በሕልም ወደ አቢሜሌክ መጣ፥ እንዲህም አለው፦ እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ምውት ነህ እርስዋ ባለ ባል ናትና። |
3 But God came to Abimelech in a dream by night, and said to him, Behold, thou art but a dead man, for the woman which thou hast taken; for she is a man’s wife. |
4 አቢሜሌክ ግን አልቀረባትም ነበር፤እንዲህም አለ፦ አቤቱ፥ ጻድቁን ሕዝብ ደግሞ ታጠፋለህን? |
4 But Abimelech had not come near her: and he said, Lord, wilt thou slay also a righteous nation? |
5 እኅቴ ናት ያለኝ እርሱ አይደለምን? እርስዋም ደግሞ ራስዋ፦ ወንድሜ ነው አለች በልቤ ቅንነትና በእጄ ንጹሕነት ይህንን አደረግሁ። |
5 Said he not unto me, She is my sister? and she, even she herself said, He is my brother: in the integrity of my heart and innocency of my hands have I done this. |
6 እግዚአብሔርም በሕልም አለው፦ ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ አወቅሁ፥ እኔም ደግሞ በፊቴ ኃጢአትን እንዳትሠራ ከለከልሁህ ስለዚህም ትነካት ዘንድ አልተውሁም። |
6 And God said unto him in a dream, Yea, I know that thou didst this in the integrity of thy heart; for I also withheld thee from sinning against me: therefore suffered I thee not to touch her. |
7 አሁንም የሰውዬውን ሚስት መልስ ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፥ ትድናለህም። ባትመልሳት ግን አንተ እንድትሞት ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንዲሞት በእርግጥ እወቅ። |
7 Now therefore restore the man his wife; for he is a prophet, and he shall pray for thee, and thou shalt live: and if thou restore her not, know thou that thou shalt surely die, thou, and all that are thine. |
8 አቢሜሌክም በነገታው ማለደ፥ ባሪያዎቹንም ሁሉ ጠራ፥ ይህንንም ነገር ሁሉ በጆሮአቸው ተናገረ ሰዎቹም እጅግ ፈሩ። |
8 Therefore Abimelech rose early in the morning, and called all his servants, and told all these things in their ears: and the men were sore afraid. |
9 አቢሜሌክም አብርሃምን ጠርቶ አለው፦ ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው? ምንስ ክፉ ሠራሁብህ? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ትልቅ ኃጢአት አውርደሃልና የማይገባ ሥራ በእኔ ሠራህብኝ። |
9 Then Abimelech called Abraham, and said unto him, What hast thou done unto us? and what have I offended thee, that thou hast brought on me and on my kingdom a great sin? thou hast done deeds unto me that ought not to be done. |
10 አቢሜሌክም አብርሃምን አለው። ይህን ማድረግህ ምን አይተህ ነው? |
10 And Abimelech said unto Abraham, What sawest thou, that thou hast done this thing? |
11 አብርሃምም አለ፦ በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት በእውነት እንደሌለ፥ ለሚስቴም ሲሉ እንደሚገድሉኝ ስላሰብሁ ነው። |
11 And Abraham said, Because I thought, Surely the fear of God is not in this place; and they will slay me for my wife’s sake. |
12 እርስዋም ደግሞ በእውነት እኅቴ ናት የእናቴ ልጅ አይደለችም እንጂ የአባቴ ልጅ ናት ለእኔም ሚስት ሆነች። |
12 And yet indeed she is my sister; she is the daughter of my father, but not the daughter of my mother; and she became my wife. |
13 እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኋት፦ በገባንበት አገር ሁሉ ለእኔ የምታደርጊው ወሮታ ይህ ነው፦ ወንድሜ ነው ብለሽ ስለ እኔ ተናገሪ። |
13 And it came to pass, when God caused me to wander from my father’s house, that I said unto her, This is thy kindness which thou shalt shew unto me; at every place whither we shall come, say of me, He is my brother. |
14 አቢሜሌክም በጎችንና ላሞችን ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችን አመጣ፥ ለአብርሃምም ሰጠው፥ ሚስቱን ሣራንም መለሰለት። |
14 And Abimelech took sheep, and oxen, and menservants, and womenservants, and gave them unto Abraham, and restored him Sarah his wife. |
15 አቢሜሌክም፦ እነሆ፥ ምድሬ በፊትህ ናት በወደድኸው ተቀመጥ አለ። |
15 And Abimelech said, Behold, my land is before thee: dwell where it pleaseth thee. |
16 ሣራንም አላት፦ እነሆ፥ ለወንድምሽ ሺህ ሚዛን ብር ሰጠሁት ያም እነሆ ከአንቺ ጋር ባሉት ሁሉ ፊት የዓይኖች መሸፈኛ ይሁንሽ ጽድቅሽ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና። |
16 And unto Sarah he said, Behold, I have given thy brother a thousand pieces of silver: behold, he is to thee a covering of the eyes, unto all that are with thee, and with all other: thus she was reproved. |
17 አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን ሚስቱንም ባሪያዎቹንም ፈወሳቸው፥ እነርሱም ወለዱ |
17 So Abraham prayed unto God: and God healed Abimelech, and his wife, and his maidservants; and they bare children. |
18 እግዚአብሔር በአብርሃም ሚስት በሣራ ምክንያት በአቢሜሌክ ቤት ማኅፀኖችን ሁሉ በፍጹም ዘግቶ ነበርና። |
18 For the Lord had fast closed up all the wombs of the house of Abimelech, because of Sarah Abraham’s wife. |