መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #149
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 149 |
Psalm 149 |
1 ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲሱን ቅኔ ተቀኙለት ምስጋናው በቅዱሳኑ ጉባኤ ነው። |
1 Praise ye the Lord. Sing unto the Lord a new song, and his praise in the congregation of saints. |
2 እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፥ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤትን ያድርጉ። |
2 Let Israel rejoice in him that made him: let the children of Zion be joyful in their King. |
3 ስሙን በዘፈን ያመስግኑ፥ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት። |
3 Let them praise his name in the dance: let them sing praises unto him with the timbrel and harp. |
4 እግዚአብሔር በሕዝቡ ተደስቶአልና፥ የዋሃንንም በማዳኑ ከፍ ከፍ ያደርጋልና። |
4 For the Lord taketh pleasure in his people: he will beautify the meek with salvation. |
5 ቅዱሳን በክብር ይመካሉ በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ። |
5 Let the saints be joyful in glory: let them sing aloud upon their beds. |
6 የእግዚአብሔር ምስጋና በጕሮሮአቸው ነው ሁለት አፍ ያለውም ሰይፍ በእጃቸው ነው፥ |
6 Let the high praises of God be in their mouth, and a twoedged sword in their hand; |
7 በአሕዛብ ላይ በቀልን በሰዎችም መካከል ቅጣትን ያደርጉ ዘንድ |
7 To execute vengeance upon the heathen, and punishments upon the people; |
8 ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት፥ አለቆቻቸውንም በእግር ብረት ያስሩ ዘንድ |
8 To bind their kings with chains, and their nobles with fetters of iron; |
9 የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉባቸው ዘንድ። ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት። ሃሌ ሉያ። |
9 To execute upon them the judgment written: this honour have all his saints. Praise ye the Lord. |