መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #148
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 148 |
Psalm 148 |
1 ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን ከሰማያት አመስግኑት በአርያም አመስግኑት። |
1 Praise ye the Lord. Praise ye the Lord from the heavens: praise him in the heights. |
2 መላእክቱ ሁሉ፥ አመስግኑት ሠራዊቱ ሁሉ፥ አመስግኑት። |
2 Praise ye him, all his angels: praise ye him, all his hosts. |
3 ፀሐይና ጨረቃ፥ አመስግኑት ከዋክብትና ብርሃን ሁሉ፥ አመስግኑት። |
3 Praise ye him, sun and moon: praise him, all ye stars of light. |
4 ሰማየ ሰማያት፥ አመስግኑት የሰማያት በላይም ውኃ። |
4 Praise him, ye heavens of heavens, and ye waters that be above the heavens. |
5 እርሱ ብሎአልና፥ ሆኑም እርሱም አዝዞአልና፥ ተፈጠሩም የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑት። |
5 Let them praise the name of the Lord: for he commanded, and they were created. |
6 ለዘላለም ዓለም አቆማቸው ትእዛዝን ሰጠ፥ አያልፉምም። |
6 He hath also stablished them for ever and ever: he hath made a decree which shall not pass. |
7 እባቦች ጥልቆችም ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑት |
7 Praise the Lord from the earth, ye dragons, and all deeps: |
8 እሳትና በረዶ አመዳይና ውርጭ፥ ቃሉን የሚያደርግ ዐውሎ ነፋስም |
8 Fire, and hail; snow, and vapour; stormy wind fulfilling his word: |
9 ተራሮች ኰረብቶችም ሁሉ፥ የሚያፈራም ዛፍ ዝግባም ሁሉ |
9 Mountains, and all hills; fruitful trees, and all cedars: |
10 አራዊትም እንስሳትም ሁሉ፥ ተንቀሳቃሾችም የሚበርሩ ወፎችም |
10 Beasts, and all cattle; creeping things, and flying fowl: |
11 የምድር ነገሥታት አሕዛብም ሁሉ፥ አለቆች የምድርም ፈራጆች ሁሉ፥ |
11 Kings of the earth, and all people; princes, and all judges of the earth: |
12 ጕልማሶችና ቈነጃጅቶች፥ ሽማግሌዎችና ልጆች |
12 Both young men, and maidens; old men, and children: |
13 የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ ምስጋናውም በሰማይና በምድር ላይ ነው። |
13 Let them praise the name of the Lord: for his name alone is excellent; his glory is above the earth and heaven. |
14 የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል የቅዱሳኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል። ሃሌ ሉያ። |
14 He also exalteth the horn of his people, the praise of all his saints; even of the children of Israel, a people near unto him. Praise ye the Lord. |