መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #99
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 99

Psalm 99

1 እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።

1 The Lord reigneth; let the people tremble: he sitteth between the cherubims; let the earth be moved.

2 እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።

2 The Lord is great in Zion; and he is high above all the people.

3 ግሩምና ቅዱስ ነውና ሁሉ ታላቅ ስምህን ያመስግኑ።

3 Let them praise thy great and terrible name; for it is holy.

4 የንጉሥ ክብር ፍርድን ይወድዳል አንተ ቅንነትን አጸናህ፥ ለያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ አደረግህ።

4 The king’s strength also loveth judgment; thou dost establish equity, thou executest judgment and righteousness in Jacob.

5 አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መረገጫ ስገዱ።

5 Exalt ye the Lord our God, and worship at his footstool; for he is holy.

6 ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው። እግዚአብሔርን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።

6 Moses and Aaron among his priests, and Samuel among them that call upon his name; they called upon the Lord, and he answered them.

7 በደመና ዓምድም ተናገራቸው ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ።

7 He spake unto them in the cloudy pillar: they kept his testimonies, and the ordinance that he gave them.

8 አቤቱ አምላክችን ሆይ፥ አንተ ሰማሃቸው አቤቱ፥ አንተ ማርሃቸው፥ ሥራቸውን ሁሉ ግን ተበቀልሃቸው።

8 Thou answeredst them, O Lord our God: thou wast a God that forgavest them, though thou tookest vengeance of their inventions.

9 አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ በቅዱስ ተራራውም ስገዱ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።

9 Exalt the Lord our God, and worship at his holy hill; for the Lord our God is holy.