መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #139
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 139 |
Psalm 139 |
1 አቤቱ፥ መረመርኸኝ፥ አወቅኸኝም። |
1 O Lord, thou hast searched me, and known me. |
2 አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ አሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ። |
2 Thou knowest my downsitting and mine uprising, thou understandest my thought afar off. |
3 ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ፥ |
3 Thou compassest my path and my lying down, and art acquainted with all my ways. |
4 የዓመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ። |
4 For there is not a word in my tongue, but, lo, O Lord, thou knowest it altogether. |
5 አቤቱ፥ አንተ እነሆ የቀድሞውንና የኋላውን አወቅህ አንተ ፈጠርኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ። |
5 Thou hast beset me behind and before, and laid thine hand upon me. |
6 እውቀትህ ከእኔ ይልቅ ተደነቀች በረታች፥ ወደ እርስዋም ለመድረስ አልችልም። |
6 Such knowledge is too wonderful for me; it is high, I cannot attain unto it. |
7 ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? |
7 Whither shall I go from thy spirit? or whither shall I flee from thy presence? |
8 ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ። ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። |
8 If I ascend up into heaven, thou art there: if I make my bed in hell, behold, thou art there. |
9 እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ |
9 If I take the wings of the morning, and dwell in the uttermost parts of the sea; |
10 በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች። |
10 Even there shall thy hand lead me, and thy right hand shall hold me. |
11 በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል፥ ሌሊት በዙሪያዬ ብርሃን ትሆናለች |
11 If I say, Surely the darkness shall cover me; even the night shall be light about me. |
12 ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና፥ ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና እንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃንዋ ነው። |
12 Yea, the darkness hideth not from thee; but the night shineth as the day: the darkness and the light are both alike to thee. |
13 አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል። |
13 For thou hast possessed my reins: thou hast covered me in my mother’s womb. |
14 ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች። |
14 I will praise thee; for I am fearfully and wonderfully made: marvellous are thy works; and that my soul knoweth right well. |
15 እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም። |
15 My substance was not hid from thee, when I was made in secret, and curiously wrought in the lowest parts of the earth. |
16 ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ። |
16 Thine eyes did see my substance, yet being unperfect; and in thy book all my members were written, which in continuance were fashioned, when as yet there was none of them. |
17 አቤቱ፥ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደ ምን እጅግ የተከበሩ ናቸው! ቍጥራቸውም እንደ ምን በዛ! |
17 How precious also are thy thoughts unto me, O God! how great is the sum of them! |
18 ብቈጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ ተነሣሁም፥ እኔም ገና ከአንተ ጋር ነኝ። |
18 If I should count them, they are more in number than the sand: when I awake, I am still with thee. |
19 አቤቱ፥ አንተ ኃጢአተኞችን የምትገድል ከሆንህስ፥ የደም ሰዎች ሆይ፥ ከእኔ ፈቀቅ በሉ። |
19 Surely thou wilt slay the wicked, O God: depart from me therefore, ye bloody men. |
20 በክፋት ይናገሩብሃልና ጠላቶችህም በከንቱ ያምፁብሃል። |
20 For they speak against thee wickedly, and thine enemies take thy name in vain. |
21 አቤቱ፥ የሚጠሉህን እኔ የጠላሁ አይደለሁምን? ስለ ጠላቶችህም አልተሰቀቅሁምን? |
21 Do not I hate them, O Lord, that hate thee? and am not I grieved with those that rise up against thee? |
22 ፍጹም ጥል ጠላኋቸው፥ ጠላቶችም ሆኑኝ። |
22 I hate them with perfect hatred: I count them mine enemies. |
23 አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ |
23 Search me, O God, and know my heart: try me, and know my thoughts: |
24 በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ። |
24 And see if there be any wicked way in me, and lead me in the way everlasting. |