መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #82
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 82

Psalm 82

1 እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።

1 God standeth in the congregation of the mighty; he judgeth among the gods.

2 እስከ መቼ ሐሰትን ትፈርዳላችሁ? እስከ መቼ ለኃጢአተኞች ፊት ታደላላችሁ?

2 How long will ye judge unjustly, and accept the persons of the wicked? Selah.

3 ለድሆችና ለድሀ አደጎች ፍረዱ ለችግረኛውና ለምስኪኑ ጽድቅ አድርጉ

3 Defend the poor and fatherless: do justice to the afflicted and needy.

4 ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ ከኃጢአተኞችም እጅ አስጥሉአቸው።

4 Deliver the poor and needy: rid them out of the hand of the wicked.

5 አያውቁም፥ አያስተውሉም በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።

5 They know not, neither will they understand; they walk on in darkness: all the foundations of the earth are out of course.

6 እኔ ግን። አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ

6 I have said, Ye are gods; and all of you are children of the most High.

7 ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ አልሁ።

7 But ye shall die like men, and fall like one of the princes.

8 አቤቱ፥ ተነሥ፥ በምድር ላይ ፍርድ፥ አንተ አሕዛብን ሁሉ ትወርሳለህና።

8 Arise, O God, judge the earth: for thou shalt inherit all nations.