መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #68
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 68

Psalm 68

1 እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።

1 Let God arise, let his enemies be scattered: let them also that hate him flee before him.

2 ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ ኅጥኣን ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።

2 As smoke is driven away, so drive them away: as wax melteth before the fire, so let the wicked perish at the presence of God.

3 ጻድቃንም ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ፥ በደስታም ደስ ይበላቸው።

3 But let the righteous be glad; let them rejoice before God: yea, let them exceedingly rejoice.

4 ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ በፊቱም ይደነግጣሉ።

4 Sing unto God, sing praises to his name: extol him that rideth upon the heavens by his name Jah, and rejoice before him.

5 እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድሀ አደጎች አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው።

5 A father of the fatherless, and a judge of the widows, is God in his holy habitation.

6 እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤት ያሳድራቸዋል፥ እስረኞችንም በኃይሉ ያወጣቸዋል ዓመፀኞች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ።

6 God setteth the solitary in families: he bringeth out those which are bound with chains: but the rebellious dwell in a dry land.

7 አቤቱ፥ በሕዝብም ፊት በወጣህ ጊዜ፥ በምድረ በዳም ባለፍህ ጊዜ፥ ምድር ተናወጠች፥

7 O God, when thou wentest forth before thy people, when thou didst march through the wilderness; Selah:

8 ከሲና አምላክ ፊት፥ ከእስራኤል አምላክ ፊት ሰማያትም አንጠበጠቡ።

8 The earth shook, the heavens also dropped at the presence of God: even Sinai itself was moved at the presence of God, the God of Israel.

9 አቤቱ፥ የሞገስን ዝናብ ለርስትህ አዘነብህ፥ በደከመም ጊዜ አንተ አጸናኸው።

9 Thou, O God, didst send a plentiful rain, whereby thou didst confirm thine inheritance, when it was weary.

10 እንስሶችህ በውስጡ አደሩ አቤቱ፥ በቸርነትህ ለድሆች አዘጋጀህ።

10 Thy congregation hath dwelt therein: thou, O God, hast prepared of thy goodness for the poor.

11 እግዚአብሔር ቃሉን ሰጠ የሚያወሩት ብዙ ሠራዊት ናቸው።

11 The Lord gave the word: great was the company of those that published it.

12 የሠራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ በቤትም የምትኖር ምርኮን ተካፈለች።

12 Kings of armies did flee apace: and she that tarried at home divided the spoil.

13 በርስቶች መካከል ብታድሩ፥ ከብር እንደ ተሠሩ እንደ ርግብ ክንፎች፥ በቅጠልያ ወርቅም እንደ ተለበጡ ላባዎችዋ ትሆናላችሁ።

13 Though ye have lien among the pots, yet shall ye be as the wings of a dove covered with silver, and her feathers with yellow gold.

14 ሰማያዊ ንጉሥ በላይዋ ባዘዘ ጊዜ፥ በሰልሞን ላይ በረዶ ዘነበ።

14 When the Almighty scattered kings in it, it was white as snow in Salmon.

15 የእግዚአብሔር ተራራ የለመለመ ተራራ ነው የጸና ተራራና የለመለመ ተራራ ነው።

15 The hill of God is as the hill of Bashan; an high hill as the hill of Bashan.

16 የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ? እግዚአብሔር ይህን ተራራ ያድርበት ዘንድ ወደደው በእውነት እግዚአብሔር ለዘላለም ያድርበታል።

16 Why leap ye, ye high hills? this is the hill which God desireth to dwell in; yea, the Lord will dwell in it for ever.

17 የእግዚአብሔር ሰረገላዎች የብዙ ብዙ ሺህ ናቸው ጌታ በመቅደሱ በሲና በመካከላቸው ነው።

17 The chariots of God are twenty thousand, even thousands of angels: the Lord is among them, as in Sinai, in the holy place.

18 ወደ ላይ ዓረግህ፥ ምርኮን ማረክህ፥ ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ፥ ደግሞም ለዓመፀኞች በዚያ ያድሩ ዘንድ።

18 Thou hast ascended on high, thou hast led captivity captive: thou hast received gifts for men; yea, for the rebellious also, that the Lord God might dwell among them.

19 እግዚአብሔር አምላክ ቡሩክ ነው እግዚአብሔር በየዕለቱ ቡሩክ ነው የመድኃኒታችን አምላክ ይረዳናል።

19 Blessed be the Lord, who daily loadeth us with benefits, even the God of our salvation. Selah.

20 አምላካችንስ የደኅንነት አምላክ ነው ከሞት መውጣትም ከእግዚአብሔር ነው።

20 He that is our God is the God of salvation; and unto God the Lord belong the issues from death.

21 ነገር ግን እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ፥ በኃጢአት የሚሄድንም የጠጕሩን አናት ይቀጠቅጣል።

21 But God shall wound the head of his enemies, and the hairy scalp of such an one as goeth on still in his trespasses.

22 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ ከባሳን አመጣቸዋለሁ፥ ከባሕርም ጥልቅ እመልሳቸዋለሁ፥

22 The Lord said, I will bring again from Bashan, I will bring my people again from the depths of the sea:

23 እግሮችህ በደም ይረገጡ ዘንድ፥ የውሾችህ ምላስ በጠላቶች ላይ ይሆን ዘንድ።

23 That thy foot may be dipped in the blood of thine enemies, and the tongue of thy dogs in the same.

24 የአምላኬ የንጉሥ መንገድ በመቅደሱ፥ አቤቱ፥ መንገድህ ተገለጠ።

24 They have seen thy goings, O God; even the goings of my God, my King, in the sanctuary.

25 አለቆች ቀደሙ፥ መዘምራንም ተከተሉ ከበሮን በሚመቱ በቈነጃጅት መካከል።

25 The singers went before, the players on instruments followed after; among them were the damsels playing with timbrels.

26 እግዚአብሔርን በጉባኤ፥ ጌታችንንም በእስራኤል ምንጭ አመስግኑት።

26 Bless ye God in the congregations, even the Lord, from the fountain of Israel.

27 ወጣቱ ብንያም በጕልበቱ በዚያ አለ፥ ገዦቻቸው የይሁዳ አለቆች የዛብሎን አለቆችና የንፍታሌምም አለቆች።

27 There is little Benjamin with their ruler, the princes of Judah and their council, the princes of Zebulun, and the princes of Naphtali.

28 አቤቱ፥ ኃይልህን እዘዝ አቤቱ፥ ይህንም ለእኛ የሠራኸውን አጽናው።

28 Thy God hath commanded thy strength: strengthen, O God, that which thou hast wrought for us.

29 በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስህ ነገሥታት እጅ መንሻን ለአንተ ያመጣሉ።

29 Because of thy temple at Jerusalem shall kings bring presents unto thee.

30 በሸምበቆ ውስጥ ያሉትን አራዊት፥ በአሕዛብ ውስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን ጉባኤ ገሥጽ፥ እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው።

30 Rebuke the company of spearmen, the multitude of the bulls, with the calves of the people, till every one submit himself with pieces of silver: scatter thou the people that delight in war.

31 መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።

31 Princes shall come out of Egypt; Ethiopia shall soon stretch out her hands unto God.

32 የምድር ነገሥታት፥ ለእግዚአብሔር ተቀኙ፥ ለጌታም ዘምሩ።

32 Sing unto God, ye kingdoms of the earth; O sing praises unto the Lord; Selah:

33 በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ የኃይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።

33 To him that rideth upon the heavens of heavens, which were of old; lo, he doth send out his voice, and that a mighty voice.

34 ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ ግርማው በእስራኤል ላይ፥ ኃይሉም በደመናት ላይ ነው።

34 Ascribe ye strength unto God: his excellency is over Israel, and his strength is in the clouds.

35 እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል እግዚአብሔርም ይመስገን።

35 O God, thou art terrible out of thy holy places: the God of Israel is he that giveth strength and power unto his people. Blessed be God.