መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #83
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 83 |
Psalm 83 |
1 አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል። |
1 Keep not thou silence, O God: hold not thy peace, and be not still, O God. |
2 እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና። |
2 For, lo, thine enemies make a tumult: and they that hate thee have lifted up the head. |
3 ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ። |
3 They have taken crafty counsel against thy people, and consulted against thy hidden ones. |
4 ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ። |
4 They have said, Come, and let us cut them off from being a nation; that the name of Israel may be no more in remembrance. |
5 አንድ ሆነው በአንተ ላይ ተማከሩ በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ |
5 For they have consulted together with one consent: they are confederate against thee: |
6 የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥ |
6 The tabernacles of Edom, and the Ishmaelites; of Moab, and the Hagarenes; |
7 ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር |
7 Gebal, and Ammon, and Amalek; the Philistines with the inhabitants of Tyre; |
8 አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኑአቸው። |
8 Assur also is joined with them: they have holpen the children of Lot. Selah. |
9 እንደ ምድያምና እንደ ሲሣራ፥ በቂሶንም ወንዝ እንደ ኢያቢስ አድርግባቸው። |
9 Do unto them as unto the Midianites; as to Sisera, as to Jabin, at the brook of Kison: |
10 በዓይንዶር ጠፉ፥ እንደ ምድርም ጕድፍ ሆኑ። |
10 Which perished at Endor: they became as dung for the earth. |
11 አለቆቻቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፥ ታላላቆቻቸውንም እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው። |
11 Make their nobles like Oreb, and like Zeeb: yea, all their princes as Zebah, and as Zalmunna: |
12 የእግዚአብሔርን መሠዊያ እንወርሳለን የሚሉትን። |
12 Who said, Let us take to ourselves the houses of God in possession. |
13 አምላኬ ሆይ፥ እንደ ትቢያ በነፋስ ፊትም እንደ ገለባ አድርጋቸው። |
13 O my God, make them like a wheel; as the stubble before the wind. |
14 እሳት ዱርን እንደሚያቃጥል፥ ነበልባልም ተራሮች እንደሚያነድድ፥ |
14 As the fire burneth a wood, and as the flame setteth the mountains on fire; |
15 እንዲሁ በቍጣህ አሳድዳቸው፥ በመቅሠፍትህም አስደንግጣቸው። |
15 So persecute them with thy tempest, and make them afraid with thy storm. |
16 ፊታቸውን እፍረት ሙላው፥ አቤቱ፥ ስምህንም ይፈልጋሉ። |
16 Fill their faces with shame; that they may seek thy name, O Lord. |
17 ይፈሩ ለዘላለሙም ይታወኩ ይጐስቍሉ ይጥፉም። |
17 Let them be confounded and troubled for ever; yea, let them be put to shame, and perish: |
18 ስምህም እግዚአብሔር እንደ ሆነ፥ በምድር ሁሉ ላይም አንተ ብቻ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ። |
18 That men may know that thou, whose name alone is Jehovah, art the most high over all the earth. |