መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #84
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 84

Psalm 84

1 የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ ማደሪያዎችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው!

1 How amiable are thy tabernacles, O Lord of hosts!

2 ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትወድዳለች ትናፍቅማለች ልቤም ሥጋዬም በሕያው አምላክ ደስ ተሰኘ።

2 My soul longeth, yea, even fainteth for the courts of the Lord: my heart and my flesh crieth out for the living God.

3 ወፍ ለእርስዋ ቤትን አገኘች፥ ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች የሠራዊት አምላክ ንጉሤም አምላኬም ሆይ፥ እርሱ መሠዊያህ ነው።

3 Yea, the sparrow hath found an house, and the swallow a nest for herself, where she may lay her young, even thine altars, O Lord of hosts, my King, and my God.

4 በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው ለዓለምና ለዘላለምም ያመሰግኑሃል።

4 Blessed are they that dwell in thy house: they will be still praising thee. Selah.

5 አቤቱ፥ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት፥ በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው።

5 Blessed is the man whose strength is in thee; in whose heart are the ways of them.

6 በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰነው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና።

6 Who passing through the valley of Baca make it a well; the rain also filleth the pools.

7 ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።

7 They go from strength to strength, every one of them in Zion appeareth before God.

8 የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ አድምጥ።

8 O Lord God of hosts, hear my prayer: give ear, O God of Jacob. Selah.

9 አቤቱ፥ መታመናችንን እይልን፥ ወደ ቀባኸውም ፊት ተመልከት።

9 Behold, O God our shield, and look upon the face of thine anointed.

10 ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ።

10 For a day in thy courts is better than a thousand. I had rather be a doorkeeper in the house of my God, than to dwell in the tents of wickedness.

11 እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትንና እውነትን ስለ ወደደ፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም።

11 For the Lord God is a sun and shield: the Lord will give grace and glory: no good thing will he withhold from them that walk uprightly.

12 የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በአንተ የታመነ ሰው ምስጉን ነው።

12 O Lord of hosts, blessed is the man that trusteth in thee.