ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #13
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘኍልቍ 13 |
Numbers 13 |
1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
1 And the Lord spake unto Moses, saying, |
2 ለእስራኤል ልጆች የምሰጣትን የከንዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ሰዎችን ላክ ከአባቶች ነገድ ሁሉ እያንዳንዱ በመካከላቸው አለቃ የሆነ አንድ ሰው ትልካላችሁ። |
2 Send thou men, that they may search the land of Canaan, which I give unto the children of Israel: of every tribe of their fathers shall ye send a man, every one a ruler among them. |
3 ሙሴም እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው እነርሱም ሁሉ የእስራኤል ልጆች አለቆች ነበሩ። |
3 And Moses by the commandment of the Lord sent them from the wilderness of Paran: all those men were heads of the children of Israel. |
4 ስማቸውም ይህ ነበረ ከሮቤል ነገድ የዘኩር ልጅ ሰሙኤል |
4 And these were their names: of the tribe of Reuben, Shammua the son of Zaccur. |
5 ከስምዖን ነገድ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ |
5 Of the tribe of Simeon, Shaphat the son of Hori. |
6 ከይሁዳ ነገድ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ |
6 Of the tribe of Judah, Caleb the son of Jephunneh. |
7 ከይሳኮር ነገድ የዮሴፍ ልጅ ይግአል |
7 Of the tribe of Issachar, Igal the son of Joseph. |
8 ከኤፍሬም ነገድ የነዌ ልጅ አውሴ |
8 Of the tribe of Ephraim, Oshea the son of Nun. |
9-10 ከብንያም ነገድ የራፉ ልጅ ፈልጢ ከዛብሎን ነገድ የሰዲ ልጅ ጉዲኤል |
9 Of the tribe of Benjamin, Palti the son of Raphu. |
11 ከዮሴፍ ነገድ እርሱም የምናሴ ነገድ የሱሲ ልጅ ጋዲ |
11 Of the tribe of Joseph, namely, of the tribe of Manasseh, Gaddi the son of Susi. |
12 ከዳን ነገድ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል |
12 Of the tribe of Dan, Ammiel the son of Gemalli. |
13 ከአሴር ነገድ የሚካኤል ልጅ ሰቱር |
13 Of the tribe of Asher, Sethur the son of Michael. |
14 ከንፍታሌም ነገድ የያቢ ልጅ ናቢ |
14 Of the tribe of Naphtali, Nahbi the son of Vophsi. |
15 ከጋድ ነገድ የማኪ ልጅ ጉዲኤል። |
15 Of the tribe of Gad, Geuel the son of Machi. |
16 ምድሪቱን ይሰልሉ ዘንድ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴም የነዌን ልጅ አውሴን ኢያሱ ብሎ ጠራው። |
16 These are the names of the men which Moses sent to spy out the land. And Moses called Oshea the son of Nun Jehoshua. |
17 ሙሴም የከነዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ላካቸው፥ አላቸውም፦ ከዚህ በደቡብ በኩል ውጡ፥ ወደ ተራሮችም ሂዱ |
17 And Moses sent them to spy out the land of Canaan, and said unto them, Get you up this way southward, and go up into the mountain: |
18 ምድሪቱንም እንዴት እንደ ሆነች፥ በእርስዋም የሚኖሩ ሰዎች ብርቱዎች ወይም ደካሞች፥ |
18 And see the land, what it is; and the people that dwelleth therein, whether they be strong or weak, few or many; |
19 ጥቂቶች ወይም ብዙዎች እንደ ሆኑ፥ የሚኖሩባትም ምድር መልካም ወይም ክፉ፥ የሚኖሩባቸውም ከተሞች ሰፈሮች ወይም አምቦች እንደ ሆኑ፥ |
19 And what the land is that they dwell in, whether it be good or bad; and what cities they be that they dwell in, whether in tents, or in strong holds; |
20 ምድሪቱም ወፍራም ወይም ስስ ዛፍ ያለባት ወይም የሌለባት እንደ ሆነች እዩ ከምድሪቱ ፍሬ አምጡ አይዞአችሁ። በዚያን ጊዜም ወይኑ አስቀድሞ ፍሬ የሚያፈራበት ወራት ነበረ። |
20 And what the land is, whether it be fat or lean, whether there be wood therein, or not. And be ye of good courage, and bring of the fruit of the land. Now the time was the time of the firstripe grapes. |
21 ወጡም ምድሪቱንም ከጺን ምድረ በዳ በሐማት ዳር እስካለችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ። |
21 So they went up, and searched the land from the wilderness of Zin unto Rehob, as men come to Hamath. |
22 በደቡብም በኩል ውጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብፅ ካለችው ከጣኔዎስ በፊት ሰባት ዓመት ተሠርታ ነበር። |
22 And they ascended by the south, and came unto Hebron; where Ahiman, Sheshai, and Talmai, the children of Anak, were. (Now Hebron was built seven years before Zoan in Egypt.) |
23 ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጡ፥ ከዚያም ከወይኑ አንድ ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፥ ሁለቱም ሰዎች በመሎጊያ ተሸከሙት ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም አመጡ። |
23 And they came unto the brook of Eshcol, and cut down from thence a branch with one cluster of grapes, and they bare it between two upon a staff; and they brought of the pomegranates, and of the figs. |
24 የእስራኤል ልጆች ከዚያ ስለ ቈረጡት ዘለላ የዚያን ስፍራ ስም የኤሽኮል ሸለቆ ብለው ጠሩት። |
24 The place was called the brook Eshcol, because of the cluster of grapes which the children of Israel cut down from thence. |
25 ምድሪቱንም ሰልለው ከአርባ ቀን በኋላ ተመለሱ። |
25 And they returned from searching of the land after forty days. |
26 በፋራን ምድረ በዳና በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ሄደው ደረሱ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው። |
26 And they went and came to Moses, and to Aaron, and to all the congregation of the children of Israel, unto the wilderness of Paran, to Kadesh; and brought back word unto them, and unto all the congregation, and shewed them the fruit of the land. |
27 እንዲህም ብለው ነገሩት። ወደ ላክኸን ምድር ደረስን፥ እርስዋም ወተትና ማር ታፈስሳለች፥ ፍሬዋም ይህ ነው። |
27 And they told him, and said, We came unto the land whither thou sentest us, and surely it floweth with milk and honey; and this is the fruit of it. |
28 ነገር ግን በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ኃያላን ናቸው። ከተሞቻቸውም የተመሸጉ እጅግም የጸኑ ናቸው ደግሞም በዚያ የዔናቅን ልጆች አየን። |
28 Nevertheless the people be strong that dwell in the land, and the cities are walled, and very great: and moreover we saw the children of Anak there. |
29 በደቡብም ምድር አማሌቅ ተቀምጦአል በተራሮቹም ኬጢያዊና ኢያቡሳዊ አሞራዊም ተቀምጠዋል ከነዓናዊም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ አጠገብ ተቀምጦአል። |
29 The Amalekites dwell in the land of the south: and the Hittites, and the Jebusites, and the Amorites, dwell in the mountains: and the Canaanites dwell by the sea, and by the coast of Jordan. |
30 ካሌብም ሕዝቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰኘና። ማሸነፍ እንችላለንንና እንውጣ፥ እንውረሰው አለ። |
30 And Caleb stilled the people before Moses, and said, Let us go up at once, and possess it; for we are well able to overcome it. |
31 ከእርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን፦ በኃይል ከእኛ ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም አሉ። |
31 But the men that went up with him said, We be not able to go up against the people; for they are stronger than we. |
32 ስለ ሰለሉአትም ምድር ክፉ ወሬ ለእስራኤል ልጆች እያወሩ። እኛ ዞረን የሰለልናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ምድር ናት በእርስዋም ዘንድ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ረጃጅም ሰዎች ናቸው። |
32 And they brought up an evil report of the land which they had searched unto the children of Israel, saying, The land, through which we have gone to search it, is a land that eateth up the inhabitants thereof; and all the people that we saw in it are men of a great stature. |
33 በዚያም ከኔፊሊም ወገን የሆኑትን ኔፊሊም፥ የዔናቅን ልጆች፥ አየን እኛም በዓይናችን ግምት እንደ አንበጣዎች ነበርን፥ ደግሞም እኛ በዓይናቸው ዘንድ እንዲሁ ነበርን አሉ። |
33 And there we saw the giants, the sons of Anak, which come of the giants: and we were in our own sight as grasshoppers, and so we were in their sight. |