ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #14
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘኍልቍ 14

Numbers 14

1 ማኅበሩም ሁሉ ድምፃቸውን አንሥተው ጮኹ ሕዝቡም በዚያ ሌሊት አለቀሱ።

1 And all the congregation lifted up their voice, and cried; and the people wept that night.

2 የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ ማኅበሩም ሁሉ። በግብፅ ምድር ሳለን ምነው በሞትን ኖሮ! ወይም በዚህ ምድረ በዳ ምነው በሞትን ኖሮ!

2 And all the children of Israel murmured against Moses and against Aaron: and the whole congregation said unto them, Would God that we had died in the land of Egypt! or would God we had died in this wilderness!

3 እግዚአብሔርም በሰይፍ እንሞት ዘንድ ወደዚች ምድር ለምን ያገባናል? ሴቶቻችንና ልጆቻችን ምርኮ ይሆናሉ ወደ ግብፅ መመለስ አይሻለንምን? አሉአቸው።

3 And wherefore hath the Lord brought us unto this land, to fall by the sword, that our wives and our children should be a prey? were it not better for us to return into Egypt?

4 እርስ በርሳቸውም። ኑ፥ አለቃ ሾመን ወደ ግብፅ እንመለስ ተባባሉ።

4 And they said one to another, Let us make a captain, and let us return into Egypt.

5 ሙሴና አሮንም በእስራኤል ልጆች ጉባኤ ፊት በግምባራቸው ወደቁ።

5 Then Moses and Aaron fell on their faces before all the assembly of the congregation of the children of Israel.

6 ምድርን ከሰለሉት ጋር የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ

6 And Joshua the son of Nun, and Caleb the son of Jephunneh, which were of them that searched the land, rent their clothes:

7 ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ። ዞረን የሰለልናት ምድር እጅግ መልካም ናት።

7 And they spake unto all the company of the children of Israel, saying, The land, which we passed through to search it, is an exceeding good land.

8 እግዚአብሔርስ ከወደደን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርስዋንም ይሰጠናል።

8 If the Lord delight in us, then he will bring us into this land, and give it us; a land which floweth with milk and honey.

9 ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው።

9 Only rebel not ye against the Lord, neither fear ye the people of the land; for they are bread for us: their defence is departed from them, and the Lord is with us: fear them not.

10 ማኅበሩ ሁሉ ግን በድንጋይ ይወግሩአቸው ዘንድ ተማከሩ። የእግዚአብሔርም ክብር ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ተገለጠ።

10 But all the congregation bade stone them with stones. And the glory of the Lord appeared in the tabernacle of the congregation before all the children of Israel.

11 እግዚአብሔርም ሙሴን። ይህ ሕዝብ እስከ መቼ ይንቀኛል? በፊቱስ ባደረግሁት ተአምራት ሁሉ እስከ መቼ አያምንብኝም?

11 And the Lord said unto Moses, How long will this people provoke me? and how long will it be ere they believe me, for all the signs which I have shewed among them?

12 ከርስታቸው አጠፋቸው ዘንድ በቸነፈር እመታቸዋለሁ አንተም ከእነርሱ ለሚበዛና ለሚጠነክር ሕዝብ አደርግሃለሁ አለው።

12 I will smite them with the pestilence, and disinherit them, and will make of thee a greater nation and mightier than they.

13 ሙሴም እግዚአብሔርን አለው። ግብፃውያን ይሰማሉ ይህን ሕዝብ ከመካከላቸው በኃይልህ አውጥተኸዋልና

13 And Moses said unto the Lord, Then the Egyptians shall hear it, (for thou broughtest up this people in thy might from among them;)

14 ለዚችም ምድር ሰዎች ይናገራሉ። አንተ እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ መካከል እንደ ሆንህ ሰምተዋል አንተም፥ አቤቱ፥ ፊት ለፊት ተገልጠሃል፥ ደመናህም በላያቸው ቆሞአል፥ በቀንም በደመና ዓምድ፥ በሌሊትም በእሳት ዓምድ በፊታቸው ትሄዳለህ።

14 And they will tell it to the inhabitants of this land: for they have heard that thou Lord art among this people, that thou Lord art seen face to face, and that thy cloud standeth over them, and that thou goest before them, by day time in a pillar of a cloud, and in a pillar of fire by night.

15 ይህን ሕዝብ እንደ አንድ ሰው ብትገድል ዝናህን የሰሙ አሕዛብ።

15 Now if thou shalt kill all this people as one man, then the nations which have heard the fame of thee will speak, saying,

16 እግዚአብሔር ይህን ሕዝብ ወደ ማለላቸው ምድር ያገባቸው ዘንድ አልቻለምና በምድረ በዳ ገደላቸው ብለው ይናገራሉ።

16 Because the Lord was not able to bring this people into the land which he sware unto them, therefore he hath slain them in the wilderness.

17-18 አሁንም፥ እባክህ። እግዚአብሔር ታጋሽና ምሕረቱ የበዛ፥ አበሳንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ ኃጢአተኞችንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኃጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው ብለህ እንደ ተናገርህ፥ የጌታ ኃይል ታላቅ ይሁን።

17 And now, I beseech thee, let the power of my Lord be great, according as thou hast spoken, saying,
18 The Lord is longsuffering, and of great mercy, forgiving iniquity and transgression, and by no means clearing the guilty, visiting the iniquity of the fathers upon the children unto the third and fourth generation.

19 ይህን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ካወጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይቅር እንዳልሃቸው፥ እባክህ፥ እንደ ምሕረትህ ብዛት የዚህን ሕዝብ ኃጢአት ይቅር በል።

19 Pardon, I beseech thee, the iniquity of this people according unto the greatness of thy mercy, and as thou hast forgiven this people, from Egypt even until now.

20 እግዚአብሔርም አለ፦ እንደ ቃልህ ይቅር አልሁ

20 And the Lord said, I have pardoned according to thy word:

21 ነገር ግን እኔ ሕያው ነኝና በእውነት የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል።

21 But as truly as I live, all the earth shall be filled with the glory of the Lord.

22 በግብፅ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ተአምራቴንና ክብሬን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ አሥር ጊዜ ስለ ተፈታተኑኝ፥

22 Because all those men which have seen my glory, and my miracles, which I did in Egypt and in the wilderness, and have tempted me now these ten times, and have not hearkened to my voice;

23 ነገሬንም ስላልሰሙ፥ በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም ከእነርሱም የናቀኝ ሰው ሁሉ አያያትም

23 Surely they shall not see the land which I sware unto their fathers, neither shall any of them that provoked me see it:

24 ባሪያዬ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ ከእርሱ ጋር ስለ ሆነ ፈጽሞም ስለተከተለኝ እርሱ ወደ ገባባት ምድር አገባዋለሁ ዘሩም ይወርሳታል።

24 But my servant Caleb, because he had another spirit with him, and hath followed me fully, him will I bring into the land whereinto he went; and his seed shall possess it.

25 አማሌቅና ከነዓናዊውም በሸለቆው ውስጥ ተቀምጦአል በነጋው ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።

25 (Now the Amalekites and the Canaanites dwelt in the valley.) To morrow turn you, and get you into the wilderness by the way of the Red sea.

26 እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው።

26 And the Lord spake unto Moses and unto Aaron, saying,

27 የሚያጕረመርምብኝን ይህን ክፉ ሕዝብ እስከ መቼ እታገሠዋለሁ? በእኔ ላይ የሚያጕረመርሙትን የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ሰማሁ።

27 How long shall I bear with this evil congregation, which murmur against me? I have heard the murmurings of the children of Israel, which they murmur against me.

28 እንዲህ በላቸው። እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር

28 Say unto them, As truly as I live, saith the Lord, as ye have spoken in mine ears, so will I do to you:

29 በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ የተቆጠራችሁ ሁሉ፥ እንደቁጥራችሁ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ እናንተ ያጕረመረማችሁብኝ፥

29 Your carcases shall fall in this wilderness; and all that were numbered of you, according to your whole number, from twenty years old and upward, which have murmured against me,

30 ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር በእርስዋ አስቀምጣችሁ ዘንድ እጄን ዘርግቼ ወደ ማልሁላችሁ ምድር በእውነት እናንተ አትገቡም።

30 Doubtless ye shall not come into the land, concerning which I sware to make you dwell therein, save Caleb the son of Jephunneh, and Joshua the son of Nun.

31 ምርኮኛ ይሆናሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን እነርሱን አገባቸዋለሁ፥ እናንተም የናቃችኋትን ምድር ያውቃሉ።

31 But your little ones, which ye said should be a prey, them will I bring in, and they shall know the land which ye have despised.

32 እናንተ ግን በድኖቻችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃሉ።

32 But as for you, your carcases, they shall fall in this wilderness.

33 ልጆቻችሁም በምድረ በዳ አርባ ዓመት ይቅበዘበዛሉ፥ በድኖቻችሁም በምድረ በዳ እስኪጠፉ ድረስ ግልሙትናችሁን ይሸከማሉ።

33 And your children shall wander in the wilderness forty years, and bear your whoredoms, until your carcases be wasted in the wilderness.

34 ምድሪቱን በሰላለችሁባት ቀን ቍጥር፥ አርባ ቀን፥ ስለ አንድ ቀንም አንድ ዓመት፥ ኃጢአታችሁን አርባ ዓመት ትሸከማላችሁ፥ ቍጣዬንም ታውቃላችሁ።

34 After the number of the days in which ye searched the land, even forty days, each day for a year, shall ye bear your iniquities, even forty years, and ye shall know my breach of promise.

35 እኔ እግዚአብሔር፦ በእኔ ላይ በተሰበሰበ በዚህ ክፉ ማኅበር ሁሉ ላይ እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ ተናገርሁ በዚህ ምድረ በዳ ያልቃሉ፥ በዚያም ይሞታሉ።

35 I the Lord have said, I will surely do it unto all this evil congregation, that are gathered together against me: in this wilderness they shall be consumed, and there they shall die.

36 ምድሪቱንም ሊሰልሉ ሙሴ ልኮአቸው የተመለሱት ሰዎች ክፉ ወሬም ስለ ምድሪቱ እያወሩ በእርሱ ላይ ማኅበሩ ሁሉ እንዲያጕረመርሙ ያደረጉ፥

36 And the men, which Moses sent to search the land, who returned, and made all the congregation to murmur against him, by bringing up a slander upon the land,

37 ክፉ ወሬ ያወሩ እነዚያ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በመቅሠፍት ሞቱ።

37 Even those men that did bring up the evil report upon the land, died by the plague before the Lord.

38 ነገር ግን ምድሪቱን ሊሰልሉ ከሄዱ ሰዎች የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ በሕይወት ተቀመጡ።

38 But Joshua the son of Nun, and Caleb the son of Jephunneh, which were of the men that went to search the land, lived still.

39 ሙሴም ይህን ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ነገረ፥ ሕዝቡም እጅግ አዘኑ።

39 And Moses told these sayings unto all the children of Israel: and the people mourned greatly.

40 በነጋውም ማልደው ተነሡ፥ ወደ ተራራውም ራስ መጥተው። እነሆ፥ መጣን እኛ በድለናልና እግዚአብሔር ወዳለው ስፍራ እንወጣለን አሉ።

40 And they rose up early in the morning, and gat them up into the top of the mountain, saying, Lo, we be here, and will go up unto the place which the Lord hath promised: for we have sinned.

41 ሙሴም አለ። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? አይጠቅማችሁም።

41 And Moses said, Wherefore now do ye transgress the commandment of the Lord? but it shall not prosper.

42 እግዚአብሔር በእናንተ መካከል አይደለምና በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትወድቁ አትውጡ።

42 Go not up, for the Lord is not among you; that ye be not smitten before your enemies.

43 አማሌቃዊና ከነዓናዊ በፊታችሁ ናቸውና በሰይፍ ትወድቃላችሁ እግዚአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋልና እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይሆንም።

43 For the Amalekites and the Canaanites are there before you, and ye shall fall by the sword: because ye are turned away from the Lord, therefore the Lord will not be with you.

44 እነርሱ ግን ወደ ተራራው ራስ ሊወጡ ደፈሩ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦትና ሙሴ ከሰፈሩ አልተነሡም።

44 But they presumed to go up unto the hill top: nevertheless the ark of the covenant of the Lord, and Moses, departed not out of the camp.

45 በዚያም ተራራ ላይ የተቀመጡ አማሌቃዊና ከነዓናዊ ወረዱ፥ መትተዋቸውም እስከ ሔርማ ድረስ አሳደዱአቸው።

45 Then the Amalekites came down, and the Canaanites which dwelt in that hill, and smote them, and discomfited them, even unto Hormah.