ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #2
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘኍልቍ 2

Numbers 2

1 እግዚአብሔርም ለሙሴና ለአሮን እንዲህ ብሎ ተናገረ።

1 And the Lord spake unto Moses and unto Aaron, saying,

2 የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየዓላማው በየአባቶቻቸው ቤቶች ምልክት ይስፈሩ በመገናኛው ድንኳን አፋዛዥ ዙሪያ ይስፈሩ።

2 Every man of the children of Israel shall pitch by his own standard, with the ensign of their father’s house: far off about the tabernacle of the congregation shall they pitch.

3 በምሥራቅ በኩል ወደ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት እንደ ሠራዊቶቻቸው የይሁዳ ሰፈር ዓላማ ሰዎች ይሆናሉ የይሁዳ ልጆችም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ።

3 And on the east side toward the rising of the sun shall they of the standard of the camp of Judah pitch throughout their armies: and Nahshon the son of Amminadab shall be captain of the children of Judah.

4 ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።

4 And his host, and those that were numbered of them, were threescore and fourteen thousand and six hundred.

5 በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩ የይሳኮር ነገድ ይሆናሉ የይሳኮርም ልጆች አለቃ የሶገር ልጅ ናትናኤል ነበረ።

5 And those that do pitch next unto him shall be the tribe of Issachar: and Nethaneel the son of Zuar shall be captain of the children of Issachar.

6 ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

6 And his host, and those that were numbered thereof, were fifty and four thousand and four hundred.

7 በእነርሱም አጠገብ የዛብሎን ነገድ ነበረ የዛብሎንም ልጆች አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ነበረ።

7 Then the tribe of Zebulun: and Eliab the son of Helon shall be captain of the children of Zebulun.

8 ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

8 And his host, and those that were numbered thereof, were fifty and seven thousand and four hundred.

9 ከይሁዳ ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። እነዚህም አስቀድመው ይጓዛሉ።

9 All that were numbered in the camp of Judah were an hundred thousand and fourscore thousand and six thousand and four hundred, throughout their armies. These shall first set forth.

10 በደቡብ በኩል በየሠራዊቶቻቸው የሮቤል ሰፈር ዓላማ ይሆናል የሮቤልም ልጆች አለቃ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነበረ።

10 On the south side shall be the standard of the camp of Reuben according to their armies: and the captain of the children of Reuben shall be Elizur the son of Shedeur.

11 ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።

11 And his host, and those that were numbered thereof, were forty and six thousand and five hundred.

12 በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩ የስምዖን ነገድ ናቸው የስምዖንም ልጆች አለቃ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል ነበረ።

12 And those which pitch by him shall be the tribe of Simeon: and the captain of the children of Simeon shall be Shelumiel the son of Zurishaddai.

13 ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ።

13 And his host, and those that were numbered of them, were fifty and nine thousand and three hundred.

14 በእነርሱም አጠገብ የጋድ ነገድ ነበረ የጋድም ልጆች አለቃ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ነበረ።

14 Then the tribe of Gad: and the captain of the sons of Gad shall be Eliasaph the son of Reuel.

15 ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አምሳ ነበሩ።

15 And his host, and those that were numbered of them, were forty and five thousand and six hundred and fifty.

16 ከሮቤል ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ አምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ አምሳ ነበሩ። እነርሱም ቀጥለው ይጓዛሉ።

16 All that were numbered in the camp of Reuben were an hundred thousand and fifty and one thousand and four hundred and fifty, throughout their armies. And they shall set forth in the second rank.

17 ከዚያም በኋላ የመገናኛው ድንኳን በሰፈሮቹም መካከል የሌዋውያን ሰፈር ይጓዛል እንደ ሰፈራቸው ሰው ሁሉ በየስፍራው በየዓላማውም ይጓዛሉ።

17 Then the tabernacle of the congregation shall set forward with the camp of the Levites in the midst of the camp: as they encamp, so shall they set forward, every man in his place by their standards.

18 በምዕራብ በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የኤፍሬም ሰፈር ዓላማ ይሆናል የኤፍሬም ልጆች አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነበረ።

18 On the west side shall be the standard of the camp of Ephraim according to their armies: and the captain of the sons of Ephraim shall be Elishama the son of Ammihud.

19 ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።

19 And his host, and those that were numbered of them, were forty thousand and five hundred.

20 በእነርሱም አጠገብ የምናሴ ነገድ ይሆናል የምናሴም ልጆች አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ነበረ።

20 And by him shall be the tribe of Manasseh: and the captain of the children of Manasseh shall be Gamaliel the son of Pedahzur.

21 ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።

21 And his host, and those that were numbered of them, were thirty and two thousand and two hundred.

22 በእነርሱም አጠገብ የብንያም ነገድ ይሆናል ይብንያምም ልጆች አለቃ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነበረ።

22 Then the tribe of Benjamin: and the captain of the sons of Benjamin shall be Abidan the son of Gideoni.

23 ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

23 And his host, and those that were numbered of them, were thirty and five thousand and four hundred.

24 ከኤፍሬም ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ። እነርሱም ሦስተኛ ሆነው ይጓዛሉ።

24 All that were numbered of the camp of Ephraim were an hundred thousand and eight thousand and an hundred, throughout their armies. And they shall go forward in the third rank.

25 በሰሜን በኩል እንደ ሠራዊቶቻቸው የዳን ሰፈር ዓላማ ይሆናል የዳንም ልጆች አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበረ።

25 The standard of the camp of Dan shall be on the north side by their armies: and the captain of the children of Dan shall be Ahiezer the son of Ammishaddai.

26 ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ስድሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ።

26 And his host, and those that were numbered of them, were threescore and two thousand and seven hundred.

27 በእነርሱም አጠገብ የሚሰፍሩ የአሴር ነገድ ይሆናሉ የአሴርም ልጆች አለቃ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ነበረ።

27 And those that encamp by him shall be the tribe of Asher: and the captain of the children of Asher shall be Pagiel the son of Ocran.

28 ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።

28 And his host, and those that were numbered of them, were forty and one thousand and five hundred.

29 በእነርሱም አጠገብ የንፍታሌም ነገድ ይሆናል የንፍታሌምም ልጆች አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ነበረ።

29 Then the tribe of Naphtali: and the captain of the children of Naphtali shall be Ahira the son of Enan.

30 ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

30 And his host, and those that were numbered of them, were fifty and three thousand and four hundred.

31 ከዳን ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ መቶ አምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። እነርሱም በየዓላሞቻቸው በመጨረሻ ይጓዛሉ።

31 All they that were numbered in the camp of Dan were an hundred thousand and fifty and seven thousand and six hundred. They shall go hindmost with their standards.

32 ከእስራኤል ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች የተቈጠሩ እነዚህ ናቸው ከየሰፈሩ በየሠራዊቶቻቸው የተቈጠሩ ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ነበሩ።

32 These are those which were numbered of the children of Israel by the house of their fathers: all those that were numbered of the camps throughout their hosts were six hundred thousand and three thousand and five hundred and fifty.

33 ሌዋውያን ግን እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም።

33 But the Levites were not numbered among the children of Israel; as the Lord commanded Moses.

34 የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ በዓላሞቻቸው አጠገብ ሰፈሩ፥ እንዲሁም በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች ተጓዙ።

34 And the children of Israel did according to all that the Lord commanded Moses: so they pitched by their standards, and so they set forward, every one after their families, according to the house of their fathers.