ኦሪት ዘኍልቍ Orit ZeHwilQwi
Numbers / Bamidbar #3
In Amharic and English
|
ኦሪት ዘኍልቍ 3 |
Numbers 3 |
1 እግዚአብሔርም በሲና ተራራ ላይ ሙሴን በተናገረበት ቀን የአሮንና የሙሴ ትውልድ ይህ ነበረ። |
1 These also are the generations of Aaron and Moses in the day that the Lord spake with Moses in mount Sinai. |
2 የአሮን ልጆች ስም ይህ ነው በኵሩ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር። |
2 And these are the names of the sons of Aaron; Nadab the firstborn, and Abihu, Eleazar, and Ithamar. |
3 የተቀቡ ካህናት በክህነትም ያገለግሉ ዘንድ የቀደሳቸው የአሮን ልጆች ስም ይህ ነው። |
3 These are the names of the sons of Aaron, the priests which were anointed, whom he consecrated to minister in the priest’s office. |
4 ናዳብና አብዩድ በሲና ምድረ በዳ በእግዚአብሔር ፊት ልዩ እሳት ባቀረቡ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ሞቱ ልጆችም አልነበሩአቸውም። አልዓዛርና ኢታምር በአባታቸው በአሮን ፊት በክህነት ያገለግሉ ነበር። |
4 And Nadab and Abihu died before the Lord, when they offered strange fire before the Lord, in the wilderness of Sinai, and they had no children: and Eleazar and Ithamar ministered in the priest’s office in the sight of Aaron their father. |
5 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
5 And the Lord spake unto Moses, saying, |
6 የሌዊን ነገድ አቅርበህ ያገለግሉት ዘንድ በካህኑ በአሮን ፊት አቁማቸው። |
6 Bring the tribe of Levi near, and present them before Aaron the priest, that they may minister unto him. |
7 የማደሪያውንም ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ እርሱንና ማኅበሩን ሁሉ ለማገልገል የሚያስፈልገውን ነገር በመገናኛው ድንኳን ፊት ይጠብቁ። |
7 And they shall keep his charge, and the charge of the whole congregation before the tabernacle of the congregation, to do the service of the tabernacle. |
8 የማደሪያውንም ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ የመገናኛውን ድንኳን ዕቃ ሁሉ ይጠብቁ፥ የእስራኤልን ልጆች ለማገልገል የሚያስፈልገውንም ነገር ይጠብቁ። |
8 And they shall keep all the instruments of the tabernacle of the congregation, and the charge of the children of Israel, to do the service of the tabernacle. |
9 ሌዋውያንንም ለአሮንና ለልጆቹ ትሰጣለህ ከእስራኤል ልጆች ለእርሱ ፈጽመው ተሰጡ። |
9 And thou shalt give the Levites unto Aaron and to his sons: they are wholly given unto him out of the children of Israel. |
10 አሮንንና ልጆቹን አቁማቸው፥ ክህነታቸውንም ይጠብቁ ሌላ ሰውም ቢቀርብ ይገደል። |
10 And thou shalt appoint Aaron and his sons, and they shall wait on their priest’s office: and the stranger that cometh nigh shall be put to death. |
11 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
11 And the Lord spake unto Moses, saying, |
12 እነሆ፥ እኔ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ማኅፀን በሚከፍተው በበኵሩ ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ወስጄአለሁ |
12 And I, behold, I have taken the Levites from among the children of Israel instead of all the firstborn that openeth the matrix among the children of Israel: therefore the Levites shall be mine; |
13 በኵር ሁሉ ለእኔ ነውና ሌዋውያን ለእኔ ይሁኑ በግብፅ ምድር በኵርን ሁሉ በመታሁ ቀን፥ ከእስራኤል ዘንድ በኵርን ሁሉ፥ ሰውንና እንስሳን፥ ለእኔ ለይቼአለሁ ለእኔ ይሁኑ። እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
13 Because all the firstborn are mine; for on the day that I smote all the firstborn in the land of Egypt I hallowed unto me all the firstborn in Israel, both man and beast: mine shall they be: I am the Lord. |
14 እግዚአብሔርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
14 And the Lord spake unto Moses in the wilderness of Sinai, saying, |
15 የሌዊን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገናቸውም ቍጠር ወንዱን ሁሉ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ቍጠራቸው። |
15 Number the children of Levi after the house of their fathers, by their families: every male from a month old and upward shalt thou number them. |
16 ሙሴም እንደ እግዚአብሔር ቃል እንዳዘዘው ቈጠራቸው። |
16 And Moses numbered them according to the word of the Lord, as he was commanded. |
17 የሌዊ ልጆች በየስማቸው እነዚህ ናቸው ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ። |
17 And these were the sons of Levi by their names; Gershon, and Kohath, and Merari. |
18 የጌድሶንም ልጆች ስሞች በየወገናቸው እነዚህ ናቸው ሎቤኒ፥ ሰሜኢ። |
18 And these are the names of the sons of Gershon by their families; Libni, and Shimei. |
19 የቀዓትም ልጆች በየወገናቸው እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል። |
19 And the sons of Kohath by their families; Amram, and Izehar, Hebron, and Uzziel. |
20 የሜራሪም ልጆች በየወገናቸው ሞሖሊ፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው። |
20 And the sons of Merari by their families; Mahli, and Mushi. These are the families of the Levites according to the house of their fathers. |
21 ለጌድሶን የሎቤናውያን ወገን የሰሜአውያንም ወገን ነበሩት የጌድሶናውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው። |
21 Of Gershon was the family of the Libnites, and the family of the Shimites: these are the families of the Gershonites. |
22 ከእነርሱ የተቈጠሩት የወንዶች ሁሉ ቍጥር ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ የተቈጠሩት ሰባት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። |
22 Those that were numbered of them, according to the number of all the males, from a month old and upward, even those that were numbered of them were seven thousand and five hundred. |
23 የጌድሶናውያን ወገኖች ከማደሪያው በኋላ በምዕራብ በኩል ይሰፍራሉ። |
23 The families of the Gershonites shall pitch behind the tabernacle westward. |
24 የጌድሶናውያንም አባቶች ቤት አለቃ የዳኤል ልጅ ኤሊሳፍ ይሆናል። |
24 And the chief of the house of the father of the Gershonites shall be Eliasaph the son of Lael. |
25 ጌድሶናውያንም በመገናኛው ድንኳን የሚጠብቁት ማደሪያው፥ ድንኳኑም፥ መደረቢያውም፥ የመገናኛው ድንኳን ደጃፍ መጋረጃ፥ |
25 And the charge of the sons of Gershon in the tabernacle of the congregation shall be the tabernacle, and the tent, the covering thereof, and the hanging for the door of the tabernacle of the congregation, |
26 በማደሪያውና በመሠዊያው ዙሪያ ያለው የአደባባዩ መጋረጆች፥ የአደባባዩም ደጃፍ መጋረጃ፥ ለማገልገሉም ያሉት ገመዶች ሁሉ ይሆናል። |
26 And the hangings of the court, and the curtain for the door of the court, which is by the tabernacle, and by the altar round about, and the cords of it for all the service thereof. |
27 ከቀዓትም የእንበረማውያን ወገን፥ የይስዓራውያንም ወገን፥ የኬብሮናውያንም ወገን፥ የዑዝኤላውያንም ወገን ነበሩ የቀዓታውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው። |
27 And of Kohath was the family of the Amramites, and the family of the Izeharites, and the family of the Hebronites, and the family of the Uzzielites: these are the families of the Kohathites. |
28 ወንዶች ሁሉ እንደ ቍጥራቸው ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ መቅደሱንም ይጠብቁ ነበር። |
28 In the number of all the males, from a month old and upward, were eight thousand and six hundred, keeping the charge of the sanctuary. |
29 የቀዓት ልጆች ወገኖች በማደሪያው አጠገብ በደቡብ በኩል ይሰፍራሉ። |
29 The families of the sons of Kohath shall pitch on the side of the tabernacle southward. |
30 የቀዓታውያንም ወገኖች አባቶች ቤት አለቃ የዑዝኤል ልጅ ኤሊሳፈን ይሆናል። |
30 And the chief of the house of the father of the families of the Kohathites shall be Elizaphan the son of Uzziel. |
31 ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ የሚያገለግሉበትንም የመቅደሱን ዕቃ፥ መጋረጃውንም፥ ማገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ። |
31 And their charge shall be the ark, and the table, and the candlestick, and the altars, and the vessels of the sanctuary wherewith they minister, and the hanging, and all the service thereof. |
32 የሌዋውያንም አለቆች አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ይሆናል እርሱም መቅደሱን በሚጠብቁት ላይ ይሆናል። |
32 And Eleazar the son of Aaron the priest shall be chief over the chief of the Levites, and have the oversight of them that keep the charge of the sanctuary. |
33 ከሜራሪ የሞሖላውያን ወገን የሙሳያውያንም ወገን ነበሩ የሜራሪ ወገኖች እነዚህ ናቸው። |
33 Of Merari was the family of the Mahlites, and the family of the Mushites: these are the families of Merari. |
34 ከእነርሱም ወንዶች ሁሉ እንደ ቍጥራቸው ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ የተቈጠሩት ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። |
34 And those that were numbered of them, according to the number of all the males, from a month old and upward, were six thousand and two hundred. |
35 የሜራሪም ወገኖች አባቶች ቤት አለቃ የአቢካኢል ልጅ ሱሪኤል ነበረ በማደሪያው አጠገብ በሰሜን በኩል ይሰፍራሉ። |
35 And the chief of the house of the father of the families of Merari was Zuriel the son of Abihail: these shall pitch on the side of the tabernacle northward. |
36 የሜራሪም ልጆች የሚጠብቁት የማደሪያው ሳንቆች፥ መወርወሪያዎችም፥ ተራዳዎችም፥ እግሮቹም፥ ዕቃውም ሁሉ፥ |
36 And under the custody and charge of the sons of Merari shall be the boards of the tabernacle, and the bars thereof, and the pillars thereof, and the sockets thereof, and all the vessels thereof, and all that serveth thereto, |
37 ማገልገያውም ሁሉ፥ በዙሪያውም የሚቆሙ የአደባባይ ምሰሶች፥ እግሮቹም፥ ካስማዎቹም፥ አውታሮቹም ይሆናሉ። |
37 And the pillars of the court round about, and their sockets, and their pins, and their cords. |
38 በማደሪያውም ፊት በምሥራቅ በኩል በመገናኛው ድንኳን ፊት በስተ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት ሙሴና አሮን ልጆቹም ይሆናሉ፥ መቅደሱንም ለእስራኤል ልጆች ይጠብቃሉ ልዩም ሰው ቢቀርብ ይገደል። |
38 But those that encamp before the tabernacle toward the east, even before the tabernacle of the congregation eastward, shall be Moses, and Aaron and his sons, keeping the charge of the sanctuary for the charge of the children of Israel; and the stranger that cometh nigh shall be put to death. |
39 በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ ከሌዋውያን ወንዶች ሁሉ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ በየወገናቸው የተቈጠሩት ሁሉ ሀያ ሁለት ሺህ ነበሩ። |
39 All that were numbered of the Levites, which Moses and Aaron numbered at the commandment of the Lord, throughout their families, all the males from a month old and upward, were twenty and two thousand. |
40 እግዚአብሔርም ሙሴን። የእስራኤልን ልጆች ወንዱን በኵር ሁሉ ቍጠር ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉትን የስማቸውን ቍጥር ውሰድ |
40 And the Lord said unto Moses, Number all the firstborn of the males of the children of Israel from a month old and upward, and take the number of their names. |
41 ሌዋውያንንም በእስራኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌዋውያንንም እንስሶች በእስራኤል ልጆች እንስሶች በኵር ሁሉ ፋንታ ለእኔ ለእግዚአብሔር ውሰድ አለው። |
41 And thou shalt take the Levites for me (I am the Lord) instead of all the firstborn among the children of Israel; and the cattle of the Levites instead of all the firstlings among the cattle of the children of Israel. |
42 ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው የእስራኤልን ልጆች በኵር ሁሉ ቈጠረ። |
42 And Moses numbered, as the Lord commanded him, all the firstborn among the children of Israel. |
43 ከእነርሱም የተቈጠሩ ወንዶች በኵሮች ሁሉ የበስማቸው ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ሀያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ነበሩ። |
43 And all the firstborn males by the number of names, from a month old and upward, of those that were numbered of them, were twenty and two thousand two hundred and threescore and thirteen. |
44 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
44 And the Lord spake unto Moses, saying, |
45 ሌዋውያንን በእስራኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌዋውያንንም እንስሶች በእንስሶቻቸው ፋንታ ውሰድ ሌዋውያንም ለእኔ ይሁኑ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
45 Take the Levites instead of all the firstborn among the children of Israel, and the cattle of the Levites instead of their cattle; and the Levites shall be mine: I am the Lord. |
46 በሌዋውያን ላይ ከእስራኤል ልጆች በኵር ስለ ተረፉት ስለ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ቤዛ፥ በየራሱ አምስት ሰቅል ውሰድ |
46 And for those that are to be redeemed of the two hundred and threescore and thirteen of the firstborn of the children of Israel, which are more than the Levites; |
47 እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ትወስዳለህ ሰቅሉም ሀያ አቦሊ ነው። |
47 Thou shalt even take five shekels apiece by the poll, after the shekel of the sanctuary shalt thou take them: (the shekel is twenty gerahs:) |
48 ስለ ተረፉትም የመቤዣውን ገንዘብ ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ። |
48 And thou shalt give the money, wherewith the odd number of them is to be redeemed, unto Aaron and to his sons. |
49 ሙሴም በሌዋውያን ከተቤዡት በላይ ከተረፉት ዘንድ የመቤዣውን ገንዘብ ወሰደ። |
49 And Moses took the redemption money of them that were over and above them that were redeemed by the Levites: |
50 ከእስራኤል ልጆች በኵሮች ገንዘቡን ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ወሰደ። |
50 Of the firstborn of the children of Israel took he the money; a thousand three hundred and threescore and five shekels, after the shekel of the sanctuary: |
51 እንደ እግዚአብሔርም ቃል፥ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው፥ ሙሴ የመቤዣውን ገንዘብ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጠ። |
51 And Moses gave the money of them that were redeemed unto Aaron and to his sons, according to the word of the Lord, as the Lord commanded Moses. |