መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #19
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 19

Psalm 19

1 ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።

1 The heavens declare the glory of God; and the firmament sheweth his handywork.

2 ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።

2 Day unto day uttereth speech, and night unto night sheweth knowledge.

3 ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም።

3 There is no speech nor language, where their voice is not heard.

4 ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።

4 Their line is gone out through all the earth, and their words to the end of the world. In them hath he set a tabernacle for the sun,

5 በእነርሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል እንደ አርበኛ በመንገዱ ለመሮጥ ደስ ይለዋል።

5 Which is as a bridegroom coming out of his chamber, and rejoiceth as a strong man to run a race.

6 አወጣጡ ከሰማያት ዳርቻ ነው፥ ዙረቱም እስከ ዳርቻቸው ነው ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም።

6 His going forth is from the end of the heaven, and his circuit unto the ends of it: and there is nothing hid from the heat thereof.

7 የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ነፍስን ይመልሳል የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።

7 The law of the Lord is perfect, converting the soul: the testimony of the Lord is sure, making wise the simple.

8 የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።

8 The statutes of the Lord are right, rejoicing the heart: the commandment of the Lord is pure, enlightening the eyes.

9 የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው ለዘላለም ይኖራል የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው።

9 The fear of the Lord is clean, enduring for ever: the judgments of the Lord are true and righteous altogether.

10 ከወርቅና ከክቡር ዕንቍ ይልቅ ይወደዳል ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል።

10 More to be desired are they than gold, yea, than much fine gold: sweeter also than honey and the honeycomb.

11 ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።

11 Moreover by them is thy servant warned: and in keeping of them there is great reward.

12 ስሕተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።

12 Who can understand his errors? cleanse thou me from secret faults.

13 የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፥ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።

13 Keep back thy servant also from presumptuous sins; let them not have dominion over me: then shall I be upright, and I shall be innocent from the great transgression.

14 አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።

14 Let the words of my mouth, and the meditation of my heart, be acceptable in thy sight, O Lord, my strength, and my redeemer.