መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #20
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 20

Psalm 20

1 በመከራ ቀን እግዚአብሔር ይስማህ የያዕቆብ አምላክ ስም ያቁምህ።

1 The Lord hear thee in the day of trouble; the name of the God of Jacob defend thee;

2 ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክልህ፥ ከጽዮንም ያጥናህ።

2 Send thee help from the sanctuary, and strengthen thee out of Zion;

3 ቍርባንህን ሁሉ ያስብልህ የሚቃጠል መሥዋዕትህን ያለምልምልህ።

3 Remember all thy offerings, and accept thy burnt sacrifice; Selah.

4 እንደ ልብህ ይስጥህ ፈቃድህንም ሁሉ ይፈጽምልህ።

4 Grant thee according to thine own heart, and fulfil all thy counsel.

5 በማዳንህ ደስ ይለናል በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን ልመናህን ሁሉ እግዚአብሔር ይፈጽምልህ።

5 We will rejoice in thy salvation, and in the name of our God we will set up our banners: the Lord fulfil all thy petitions.

6 እግዚአብሔር የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ አወቅሁ ከሰማይ መቅደሱ ይመልስለታል በቀኙ ብርታት ማዳን።

6 Now know I that the Lord saveth his anointed; he will hear him from his holy heaven with the saving strength of his right hand.

7 እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን።

7 Some trust in chariots, and some in horses: but we will remember the name of the Lord our God.

8 እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ እኛ ግን ተነሣን፥ ጸንተንም ቆምን።

8 They are brought down and fallen: but we are risen, and stand upright.

9 አቤቱ፥ ንጉሥን አድነው፥ በጠራንህም ቀን ስማን።

9 Save, Lord: let the king hear us when we call.