መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David #2
In Amharic and English
መዝሙረ ዳዊት 2 |
Psalm 2 |
1 አሕዛብ ለምን ያጕረመርማሉ? ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ? |
1 Why do the heathen rage, and the people imagine a vain thing? |
2 የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። |
2 The kings of the earth set themselves, and the rulers take counsel together, against the Lord, and against his anointed, saying, |
3 ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል። |
3 Let us break their bands asunder, and cast away their cords from us. |
4 በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል። |
4 He that sitteth in the heavens shall laugh: the Lord shall have them in derision. |
5 በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል። |
5 Then shall he speak unto them in his wrath, and vex them in his sore displeasure. |
6 እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ። |
6 Yet have I set my king upon my holy hill of Zion. |
7 ትእዛዙን እናገራለሁ እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ። |
7 I will declare the decree: the Lord hath said unto me, Thou art my Son; this day have I begotten thee. |
8 ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ። |
8 Ask of me, and I shall give thee the heathen for thine inheritance, and the uttermost parts of the earth for thy possession. |
9 በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ። |
9 Thou shalt break them with a rod of iron; thou shalt dash them in pieces like a potter’s vessel. |
10 አሁንም እናንት ነገሥታት፥ ልብ አድርጉ እናንት የምድር ፈራጆችም፥ ተገሠጹ። |
10 Be wise now therefore, O ye kings: be instructed, ye judges of the earth. |
11 ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥ በረዓድም ደስ ይበላችሁ። |
11 Serve the Lord with fear, and rejoice with trembling. |
12 ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው። |
12 Kiss the Son, lest he be angry, and ye perish from the way, when his wrath is kindled but a little. Blessed are all they that put their trust in him. |