ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #18
In Amharic and English
ኦሪት ዘፍጥረት 18 |
Genesis 18 |
1 በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት። |
1 And the Lord appeared unto him in the plains of Mamre: and he sat in the tent door in the heat of the day; |
2 ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፥እንዲህም አለ፦ |
2 And he lift up his eyes and looked, and, lo, three men stood by him: and when he saw them, he ran to meet them from the tent door, and bowed himself toward the ground, |
3 አቤቱ፥ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ |
3 And said, My Lord, if now I have found favour in thy sight, pass not away, I pray thee, from thy servant: |
4 ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ፥ እግራችሁን ታጠቡ፥ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ |
4 Let a little water, I pray you, be fetched, and wash your feet, and rest yourselves under the tree: |
5 ቍራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፥ ልባችሁንም ደግፋ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ ስለዚህ ወደ ባሪያችሁ መጥታችኋልና። እነርሱም፦ እንዳልህ አድርግ አሉት። |
5 And I will fetch a morsel of bread, and comfort ye your hearts; after that ye shall pass on: for therefore are ye come to your servant. And they said, So do, as thou hast said. |
6 አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ገባና፦ ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፥ ለውሺውም፥ እንጎቻም አድርጊ አላት። |
6 And Abraham hastened into the tent unto Sarah, and said, Make ready quickly three measures of fine meal, knead it, and make cakes upon the hearth. |
7 አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፥ እጅግ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴናው ሰጠው፥ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኰለ። |
7 And Abraham ran unto the herd, and fetcht a calf tender and good, and gave it unto a young man; and he hasted to dress it. |
8 እርጎና ወተትም ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፥ በፊታቸውም አቀረበው እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ነበር፥ እነርሱም በሉ። |
8 And he took butter, and milk, and the calf which he had dressed, and set it before them; and he stood by them under the tree, and they did eat. |
9 እነርሱም፦ ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? አሉት። እርሱም፦ በድንኳኑ ውስጥ ናት አላቸው። |
9 And they said unto him, Where is Sarah thy wife? And he said, Behold, in the tent. |
10 እርሱም፦ የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች አለ። ሣራም በድንኳን ደጃፍ በስተ ኋላው ሳለች ይህንን ሰማች። |
10 And he said, I will certainly return unto thee according to the time of life; and, lo, Sarah thy wife shall have a son. And Sarah heard it in the tent door, which was behind him. |
11 አብርሃምና ሣራም በዕድሜአቸው ሸምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር በሴቶች የሚሆነውም ልማድ ከሣራ ተቋርጦ ነበር። |
11 Now Abraham and Sarah were old and well stricken in age; and it ceased to be with Sarah after the manner of women. |
12 ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች፦ ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም ፈጽሞ ሸምግሎአል። |
12 Therefore Sarah laughed within herself, saying, After I am waxed old shall I have pleasure, my lord being old also? |
13 እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው። ካረጀሁ በኋላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች? |
13 And the Lord said unto Abraham, Wherefore did Sarah laugh, saying, Shall I of a surety bear a child, which am old? |
14 በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ ሣራም ልጅን ታገኛለች። |
14 Is any thing too hard for the Lord? At the time appointed I will return unto thee, according to the time of life, and Sarah shall have a son. |
15 ሣራም ስለ ፈራች፦ አልሳቅሁም ስትል ካደች። እርሱም፦ አይደለም፥ ሳቅሽ እንጂ አላት። |
15 Then Sarah denied, saying, I laughed not; for she was afraid. And he said, Nay; but thou didst laugh. |
16 ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶም አቀኑ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ። |
16 And the men rose up from thence, and looked toward Sodom: and Abraham went with them to bring them on the way. |
17 እግዚአብሔርም አለ፦ እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለሁን? |
17 And the Lord said, Shall I hide from Abraham that thing which I do; |
18 አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናልና፥ የምድር አሕዛብም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉና። |
18 Seeing that Abraham shall surely become a great and mighty nation, and all the nations of the earth shall be blessed in him? |
19 ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው። |
19 For I know him, that he will command his children and his household after him, and they shall keep the way of the Lord, to do justice and judgment; that the Lord may bring upon Abraham that which he hath spoken of him. |
20 እግዚአብሔርም አለ፦ የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቶአልና፥ ኃጢአታቸውም እጅግ ከብዳለችና፥ |
20 And the Lord said, Because the cry of Sodom and Gomorrah is great, and because their sin is very grievous; |
21 እንግዲህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸትዋ አድርገው እንደ ሆነ ወርጄ አያለሁ እንዲሁም ባይሆን አውቃለሁ። |
21 I will go down now, and see whether they have done altogether according to the cry of it, which is come unto me; and if not, I will know. |
22 ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ፥ ወደ ሰዶምም ሄዱ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር። |
22 And the men turned their faces from thence, and went toward Sodom: but Abraham stood yet before the Lord. |
23 አብርሃምም ቀረበ አለም። በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ታጠፋለህን? |
23 And Abraham drew near, and said, Wilt thou also destroy the righteous with the wicked? |
24 አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን? |
24 Peradventure there be fifty righteous within the city: wilt thou also destroy and not spare the place for the fifty righteous that are therein? |
25 ይህ ከአንተ ይራቅ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን? |
25 That be far from thee to do after this manner, to slay the righteous with the wicked: and that the righteous should be as the wicked, that be far from thee: Shall not the Judge of all the earth do right? |
26 እግዚአብሔርም፦ በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ አምሳ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለ እነርሱ እምራለሁ አለ። |
26 And the Lord said, If I find in Sodom fifty righteous within the city, then I will spare all the place for their sakes. |
27 አብርሃምም መለሰ አለም። እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርሁ |
27 And Abraham answered and said, Behold now, I have taken upon me to speak unto the Lord, which am but dust and ashes: |
28 ከአምሳው ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ ከተማይቱን ሁሉ በአምስቱ ምክንያት ታጠፋለህን? ከዚያ አርባ አምስት ባገኝ አላጠፋትም አለ። |
28 Peradventure there shall lack five of the fifty righteous: wilt thou destroy all the city for lack of five? And he said, If I find there forty and five, I will not destroy it. |
29 ደግሞም ተናገረው፥ እንዲህም አለ፦ ምናልባት ከዚያ አርባ ቢገኙሳ? እርሱም፦ ለአርባው ስል አላደርገውም አለ። |
29 And he spake unto him yet again, and said, Peradventure there shall be forty found there. And he said, I will not do it for forty’s sake. |
30 እርሱም፦ ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ? አለ። እርሱም ከዚያ ሰላሳ ባገኝ አላጠፋም አለ። |
30 And he said unto him, Oh let not the Lord be angry, and I will speak: Peradventure there shall thirty be found there. And he said, I will not do it, if I find thirty there. |
31 ደግሞም፦ እነሆ፥ ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ አንድ ጊዜ ጀመርሁ ምናልባት ከዚያ ሀያ ቢገኙሳ? አለ። እርሱም፦ ከዚያ ሀያ ቢገኙ ስለ ሀያው አላደርገውም አለ። |
31 And he said, Behold now, I have taken upon me to speak unto the Lord: Peradventure there shall be twenty found there. And he said, I will not destroy it for twenty’s sake. |
32 እርሱም፦ እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ ምናልባት ከዚያ አሥር ቢገኙሳ? አለ። እርሱም፦ ስለ አሥሩ አላጠፋትም አለ። |
32 And he said, Oh let not the Lord be angry, and I will speak yet but this once: Peradventure ten shall be found there. And he said, I will not destroy it for ten’s sake. |
33 እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሄደ አብርሃምም ወደ ስፍራው ተመለሰ። |
33 And the Lord went his way, as soon as he had left communing with Abraham: and Abraham returned unto his place. |