መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit
Psalms Of David  #124
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

መዝሙረ ዳዊት 124

Psalm 124

1 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል።

1 If it had not been the Lord who was on our side, now may Israel say;

2 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥

2 If it had not been the Lord who was on our side, when men rose up against us:

3 ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር

3 Then they had swallowed us up quick, when their wrath was kindled against us:

4 በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር

4 Then the waters had overwhelmed us, the stream had gone over our soul:

5 በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።

5 Then the proud waters had gone over our soul.

6 ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ።

6 Blessed be the Lord, who hath not given us as a prey to their teeth.

7 ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች። ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።

7 Our soul is escaped as a bird out of the snare of the fowlers: the snare is broken, and we are escaped.

8 ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በእግዚአብሔር ስም ነው።

8 Our help is in the name of the Lord, who made heaven and earth.