ኦሪት ዘሌዋውያን Orit ZeLaeWaWiYan
Leviticus / Vayikra #7
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘሌዋውያን 7

Leviticus 7

1 የበደል መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።

1 Likewise this is the law of the trespass offering: it is most holy.

2 የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ የበደሉን መሥዋዕት ያርዱታል ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጨዋል።

2 In the place where they kill the burnt offering shall they kill the trespass offering: and the blood thereof shall he sprinkle round about upon the altar.

3 ስቡንም ሁሉ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ያቀርበዋል።

3 And he shall offer of it all the fat thereof; the rump, and the fat that covereth the inwards,

4 ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጕበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኵላሊቶቹ ጋር ይወስዳል።

4 And the two kidneys, and the fat that is on them, which is by the flanks, and the caul that is above the liver, with the kidneys, it shall he take away:

5 ካህኑም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል እርሱ የበደል መሥዋዕት ነው።

5 And the priest shall burn them upon the altar for an offering made by fire unto the Lord: it is a trespass offering.

6 ከካህናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበላዋል በተቀደሰ ስፍራ ይበሉታል ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።

6 Every male among the priests shall eat thereof: it shall be eaten in the holy place: it is most holy.

7 የኃጢአት መሥዋዕት እንደ ሆነ እንዲሁ የበደል መሥዋዕት ነው ለሁለቱ አንድ ሕግ ነው በእርሱ የሚያስተሰርይ ካህን ይወስደዋል።

7 As the sin offering is, so is the trespass offering: there is one law for them: the priest that maketh atonement therewith shall have it.

8 የማናቸውንም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርብ ካህን ያቀረበው የሚቃጠለው መሥዋዕት ቁርበት ለዚያው ካህን ይሆናል።

8 And the priest that offereth any man’s burnt offering, even the priest shall have to himself the skin of the burnt offering which he hath offered.

9 በእቶን የተጋገረው የእህል ቍርባን ሁሉ፥ በመቀቀያም ወይም በምጣድ የበሰለው ሁሉ ለሚያቀርበው ካህን ይሆናል።

9 And all the meat offering that is baken in the oven, and all that is dressed in the fryingpan, and in the pan, shall be the priest’s that offereth it.

10 በዘይትም የተለወሰው ወይም የደረቀው የእህል ቍርባን ሁሉ ለአሮን ልጆች ሁሉ ይሆናል ለሁሉም ይሆናል።

10 And every meat offering, mingled with oil, and dry, shall all the sons of Aaron have, one as much as another.

11 ሰው ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የደኅንነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው።

11 And this is the law of the sacrifice of peace offerings, which he shall offer unto the Lord.

12 ለምስጋና ቢያቀርበው፥ ከምስጋናው መሥዋዕት ጋር በዘይት የተለወሰ የቂጣ እንጎቻ፥ በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘይትም የተለወሰ መልካም ዱቄት ያቀርባል።

12 If he offer it for a thanksgiving, then he shall offer with the sacrifice of thanksgiving unleavened cakes mingled with oil, and unleavened wafers anointed with oil, and cakes mingled with oil, of fine flour, fried.

13 ለምስጋና የሚሆነውን የደኅንነት መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ እርሾ ያለበትን ኅብስት ያቀርባል።

13 Besides the cakes, he shall offer for his offering leavened bread with the sacrifice of thanksgiving of his peace offerings.

14 ከቍርባኑም ሁሉ ለእግዚአብሔር የማንሣት ቍርባን እንዲሆን ከእነርሱ አንዱን ያነሣል። እርሱም የደኅንነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል።

14 And of it he shall offer one out of the whole oblation for an heave offering unto the Lord, and it shall be the priest’s that sprinkleth the blood of the peace offerings.

15 ለምስጋና የሚሆነው የደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ በሚቀርብበት ቀን ይበሉታል ከእርሱ እስከ ነገ ምንም አያድርም።

15 And the flesh of the sacrifice of his peace offerings for thanksgiving shall be eaten the same day that it is offered; he shall not leave any of it until the morning.

16 የቍርባኑም መሥዋዕት የስእለት ወይም የፈቃድ ቢሆን፥ መሥዋዕቱ በሚቀርብበት ቀን ይብሉት ከእርሱም የቀረውን በነጋው ይብሉት

16 But if the sacrifice of his offering be a vow, or a voluntary offering, it shall be eaten the same day that he offereth his sacrifice: and on the morrow also the remainder of it shall be eaten:

17 ከመሥዋዕቱም ሥጋ እስከ ሦስተኛው ቀን የሚቆየው በእሳት ይቃጠላል።

17 But the remainder of the flesh of the sacrifice on the third day shall be burnt with fire.

18 በሦስተኛው ቀን ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ አይሠምርም ላቀረበው ሰው የተጠላ ይሆንበታል እንጂ ቍርባን ሆኖ አይቈጠርለትም ከእርሱም ቢበላ ኃጢአቱን ይሸከማል።

18 And if any of the flesh of the sacrifice of his peace offerings be eaten at all on the third day, it shall not be accepted, neither shall it be imputed unto him that offereth it: it shall be an abomination, and the soul that eateth of it shall bear his iniquity.

19 ርኩስ ነገር የሚነካውን ሥጋ አይብሉት በእሳት ይቃጠል። ንጹሕ የሆነ ሰው ሁሉ ግን ከሥጋው ይብላ።

19 And the flesh that toucheth any unclean thing shall not be eaten; it shall be burnt with fire: and as for the flesh, all that be clean shall eat thereof.

20 ሰውም የረከሰ ቢሆን፥ ለእግዚአብሔርም ከሆነው ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።

20 But the soul that eateth of the flesh of the sacrifice of peace offerings, that pertain unto the Lord, having his uncleanness upon him, even that soul shall be cut off from his people.

21 ማናቸውንም ርኵስ ነገር ቢነካ፥ የሰውን ወይም የረከሰን እንስሳ ወይም ሌላውን የተጠላ ርኩስን ቢነካ፥ ለእግዚአብሔርም ከሆነው ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።

21 Moreover the soul that shall touch any unclean thing, as the uncleanness of man, or any unclean beast, or any abominable unclean thing, and eat of the flesh of the sacrifice of peace offerings, which pertain unto the Lord, even that soul shall be cut off from his people.

22 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

22 And the Lord spake unto Moses, saying,

23 የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው። የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍየል ስብ ከቶ አትብሉ።

23 Speak unto the children of Israel, saying, Ye shall eat no manner of fat, of ox, or of sheep, or of goat.

24 የሞተውን ስብ፥ አውሬ የሰበረውንም ስብ ለሌላ ተግባር አድርጉት ነገር ግን ከእርሱ ምንም አትብሉ

24 And the fat of the beast that dieth of itself, and the fat of that which is torn with beasts, may be used in any other use: but ye shall in no wise eat of it.

25 ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው ከእንስሳ ስብ የሚበላ ሁሉ፥ ያ የበላ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋልና።

25 For whosoever eateth the fat of the beast, of which men offer an offering made by fire unto the Lord, even the soul that eateth it shall be cut off from his people.

26 በማደሪያዎቻችሁም ሁሉ የወፍ ወይም የእንስሳ ደም ቢሆን አትብሉ።

26 Moreover ye shall eat no manner of blood, whether it be of fowl or of beast, in any of your dwellings.

27 ደም የሚበላ ሰው ሁሉ ያ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ።

27 Whatsoever soul it be that eateth any manner of blood, even that soul shall be cut off from his people.

28 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

28 And the Lord spake unto Moses, saying,

29 የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው። ለእግዚአብሔር የደኅንነት መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ቍርባኑን ለእግዚአብሔር ከደኅንነቱ መሥዋዕት ያመጣል።

29 Speak unto the children of Israel, saying, He that offereth the sacrifice of his peace offerings unto the Lord shall bring his oblation unto the Lord of the sacrifice of his peace offerings.

30 የእርሱ እጆች ለእግዚአብሔር የእሳቱን ቍርባን ያመጣሉ ፍርምባው በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቍርባን ይወዘውዝ ዘንድ ስቡንና ፍርምባውን ያመጣል።

30 His own hands shall bring the offerings of the Lord made by fire, the fat with the breast, it shall he bring, that the breast may be waved for a wave offering before the Lord.

31 ካህኑም ስቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥላል ፍርምባውም ለአሮንና ለልጆቹ ይሁን።

31 And the priest shall burn the fat upon the altar: but the breast shall be Aaron’s and his sons’.

32 ከደኅንነት መሥዋዕታችሁ ቀኝ ወርቹን ለማንሣት ቍርባን እንዲሆን ለካህኑ ትሰጡታላችሁ።

32 And the right shoulder shall ye give unto the priest for an heave offering of the sacrifices of your peace offerings.

33 ከአሮንም ልጆች የደኅንነትን መሥዋዕት ደሙንና ስቡን ለሚያቀርብ ለእርሱ ቀኝ ወርቹ እድል ፈንታው ይሆናል።

33 He among the sons of Aaron, that offereth the blood of the peace offerings, and the fat, shall have the right shoulder for his part.

34 የሚወዘወዘውን ፍርምባና የሚነሣውን ወርች ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕታቸው ወስጄአለሁ፥ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘላለም እድል ፈንታ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ሰጥቼአቸዋለሁ።

34 For the wave breast and the heave shoulder have I taken of the children of Israel from off the sacrifices of their peace offerings, and have given them unto Aaron the priest and unto his sons by a statute for ever from among the children of Israel.

35 እግዚአብሔርን በክህነት ያገለግሉት ዘንድ ባቀረባቸው ቀን ለእግዚአብሔር ከሆነ ከእሳት ቍርባን የአሮንና የልጆቹ እድል ፈንታ ይህ ነው።

35 This is the portion of the anointing of Aaron, and of the anointing of his sons, out of the offerings of the Lord made by fire, in the day when he presented them to minister unto the Lord in the priest’s office;

36 ለልጅ ልጃቸው ለዘላለም እድል ፈንታቸው እንዲሆን በቀባቸው ቀን የእስራኤል ልጆች ይሰጡአቸው ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው።

36 Which the Lord commanded to be given them of the children of Israel, in the day that he anointed them, by a statute for ever throughout their generations.

37 የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቍርባን፥ የኃጢአትና የበደል መሥዋዕት፥ የቅድስናና የደኅንነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው።

37 This is the law of the burnt offering, of the meat offering, and of the sin offering, and of the trespass offering, and of the consecrations, and of the sacrifice of the peace offerings;

38 እግዚአብሔር በሲና ምድረ በዳ ቍርባናቸውን ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘዘው ይህ ነው።

38 Which the Lord commanded Moses in mount Sinai, in the day that he commanded the children of Israel to offer their oblations unto the Lord, in the wilderness of Sinai.