ኦሪት ዘፍጥረት Orit ZeFiTret
Genesis / Bereisheit #7
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

ኦሪት ዘፍጥረት 7

Genesis 7

1 እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፦ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ በዚህ ትውልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይቼሃለሁና።

1 And the Lord said unto Noah, Come thou and all thy house into the ark; for thee have I seen righteous before me in this generation.

2-3 ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት፥ ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ።

2 Of every clean beast thou shalt take to thee by sevens, the male and his female: and of beasts that are not clean by two, the male and his female.
3 Of fowls also of the air by sevens, the male and the female; to keep seed alive upon the face of all the earth.

4 ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ላይ አጠፉለሁና።

4 For yet seven days, and I will cause it to rain upon the earth forty days and forty nights; and every living substance that I have made will I destroy from off the face of the earth.

5 ኖኅም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ።

5 And Noah did according unto all that the Lord commanded him.

6 ኖኅም የጥፋት ውኃ በምድር ላይ በሆነ ጊዜ የስድስት መቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ።

6 And Noah was six hundred years old when the flood of waters was upon the earth.

7 ኖኅም ስለ ጥፋት ውኃ ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወደ መርከብ ገባ።

7 And Noah went in, and his sons, and his wife, and his sons’ wives with him, into the ark, because of the waters of the flood.

8 ከንጹሕ እንስሳ ንጹሕም ካልሆነው እንስሳ፥ ከወፎችና በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሰውም ሁሉ፥

8 Of clean beasts, and of beasts that are not clean, and of fowls, and of every thing that creepeth upon the earth,

9 እግዚአብሔር ኖኅን እንዳዘዘው፥ ሁለት ሁለት ተባትና እንስት እየሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መርከብ ውስጥ ገቡ።

9 There went in two and two unto Noah into the ark, the male and the female, as God had commanded Noah.

10 ከሰባት ቀንም በኋላ የጥፋት ውኃ በምድር ላይ ሆነ።

10 And it came to pass after seven days, that the waters of the flood were upon the earth.

11 በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ዕለት፥ በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፥ የሰማይም መስኮቶች ተከፈቱ

11 In the six hundredth year of Noah’s life, in the second month, the seventeenth day of the month, the same day were all the fountains of the great deep broken up, and the windows of heaven were opened.

12 ዝናቡም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ሆነ።

12 And the rain was upon the earth forty days and forty nights.

13 በዚያውም ቀን ኖኅ ወደ መርከብ ገባ፥ የኖኅ ልጆችም ሴም ካም ያፌትና የኖኅ ሚስት ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከርሱ ጋር ገቡ።

13 In the selfsame day entered Noah, and Shem, and Ham, and Japheth, the sons of Noah, and Noah’s wife, and the three wives of his sons with them, into the ark;

14 እነርሱ፥ አራዊትም ሁሉ በየወገናቸው፥ እንስሳትም ሁሉ በየወገናቸው፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾችም ሁሉ በየወገናቸው፥ ወፎችም ሁሉ በየወገናቸው፥ የሚበሩ ወፎችም ሁሉ፥

14 They, and every beast after his kind, and all the cattle after their kind, and every creeping thing that creepeth upon the earth after his kind, and every fowl after his kind, every bird of every sort.

15 ሥጋ ያላቸው ሕያዋን ሁሉ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ ኖኅ ወደ መርከብ ውስጥ ገቡ።

15 And they went in unto Noah into the ark, two and two of all flesh, wherein is the breath of life.

16 ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ገቡ እግዚአብሔርም በስተ ኋላው ዘጋበት።

16 And they that went in, went in male and female of all flesh, as God had commanded him: and the Lord shut him in.

17 የጥፋትም ውኃ በምድር ላይ አርባ ቀን ነበረ ውኃውም በዛ መርከቢቱንም አነሣ፥ ከምድርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች።

17 And the flood was forty days upon the earth; and the waters increased, and bare up the ark, and it was lift up above the earth.

18 ውኃውም አሸነፈ፥ በምድር ላይም እጅግ በዛ መርከቢቱም በውኃ ላይ ሄደች።

18 And the waters prevailed, and were increased greatly upon the earth; and the ark went upon the face of the waters.

19 ውኃውም በምድር ላይ እጅግ በጣም አሸነፈ ከሰማይም በታች ያሉ ታላላቆች ተራሮች ሁሉ ተሸፈኑ።

19 And the waters prevailed exceedingly upon the earth; and all the high hills, that were under the whole heaven, were covered.

20 ውኃው ወደ ላይ አሥራ አምስት ክንድ ከፍ ከፍ አለ ተራሮችም ተሸፈኑ።

20 Fifteen cubits upward did the waters prevail; and the mountains were covered.

21 በምድር ላይ ሥጋ ያለው የሚንቀሳቀሰው ሁሉ፥ ወፉም፥ እንስሳውም፥ አራዊቱም፥ በምድር ላይ የሚርመሰመሰው ተንቀሳቃሹም ሁሉ፥ ሰውም ሁሉ ጠፋ።

21 And all flesh died that moved upon the earth, both of fowl, and of cattle, and of beast, and of every creeping thing that creepeth upon the earth, and every man:

22 በየብስ የነበረው በአፍንጫው የሕይወት ነፍስ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ሞተ።

22 All in whose nostrils was the breath of life, of all that was in the dry land, died.

23 በምድር ላይ የነበረውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ፥ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍ ድረስ ተደመሰሰ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ።

23 And every living substance was destroyed which was upon the face of the ground, both man, and cattle, and the creeping things, and the fowl of the heaven; and they were destroyed from the earth: and Noah only remained alive, and they that were with him in the ark.

24 ውኃውም መቶ አምሳ ቀን በምድር ላይ አሸነፈ።

24 And the waters prevailed upon the earth an hundred and fifty days.