ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #6
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘጸአት 6

Exodus 6

1 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ በጸናች እጅ ይለቅቃችኋልና፥ በጸናችም እጅ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋልና አሁን በፈርዖን የማደርገውን ታያለህ።

1 Then the Lord said unto Moses, Now shalt thou see what I will do to Pharaoh: for with a strong hand shall he let them go, and with a strong hand shall he drive them out of his land.

2 እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው አለውም፦ እኔ እግዚአብሔር ነኝ

2 And God spake unto Moses, and said unto him, I am the Lord:

3 ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር።

3 And I appeared unto Abraham, unto Isaac, and unto Jacob, by the name of God Almighty, but by my name Jehovah was I not known to them.

4 የተሰደዱባትንም ምድር፥ የእንግድነታቸውን የከነዓንን ምድር፥ እሰጣቸው ዘንድ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳኔን አቆምሁ።

4 And I have also established my covenant with them, to give them the land of Canaan, the land of their pilgrimage, wherein they were strangers.

5 ደግሞ እኔ ግብፃውያን የገዙአቸውን የእስራኤልን ልጆች ልቅሶ ሰማሁ ቃል ኪዳኔንም አሰብሁ።

5 And I have also heard the groaning of the children of Israel, whom the Egyptians keep in bondage; and I have remembered my covenant.

6 ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው። እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከግብፃውያንም ባርነት አወጣችኋለሁ፥ ከተገዥነታቸውም አድናችኋለሁ በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ፥

6 Wherefore say unto the children of Israel, I am the Lord, and I will bring you out from under the burdens of the Egyptians, and I will rid you out of their bondage, and I will redeem you with a stretched out arm, and with great judgments:

7 ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ እኔም ከግብፃውያን ባርነት ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።

7 And I will take you to me for a people, and I will be to you a God: and ye shall know that I am the Lord your God, which bringeth you out from under the burdens of the Egyptians.

8 ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እሰጣት ዘንድ ወደ ማልሁባት ምድር አገባችኋለሁ እርስዋንም ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

8 And I will bring you in unto the land, concerning the which I did swear to give it to Abraham, to Isaac, and to Jacob; and I will give it you for an heritage: I am the Lord.

9 ሙሴም ይህን ለእስራኤል ልጆች ተናገረ እነርሱ ግን ከሰውነታቸው መጨነቅ ከከባዱም ሥራ የተነሣ ቃሉን አልሰሙትም።

9 And Moses spake so unto the children of Israel: but they hearkened not unto Moses for anguish of spirit, and for cruel bondage.

10 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።

10 And the Lord spake unto Moses, saying,

11 ግባ፥ የእስራኤልንም ልጆች ከአገሩ ይለቅቅ ዘንድ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገር።

11 Go in, speak unto Pharaoh king of Egypt, that he let the children of Israel go out of his land.

12 ሙሴም በእግዚአብሔር ፊት። እነሆ የእስራኤል ልጆች አልሰሙኝም እንዴትስ ፈርዖን ይሰማኛል? ይልቁንም እኔ ከንፈረ ቈላፍ ነኝ ብሎ ተናገረ።

12 And Moses spake before the Lord, saying, Behold, the children of Israel have not hearkened unto me; how then shall Pharaoh hear me, who am of uncircumcised lips?

13 እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን ተናገራቸው፥ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖንም የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ እንዲያወጣቸው ይነግሩት ዘንድ አዘዛቸው።

13 And the Lord spake unto Moses and unto Aaron, and gave them a charge unto the children of Israel, and unto Pharaoh king of Egypt, to bring the children of Israel out of the land of Egypt.

14 የአባታቸውም ቤት አለቆች እነዚህ ናቸው። የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች ሄኖኅ፥ ፈሉስ፥ አስሮን፥ ከርሚ እነዚህ የሮቤል ወገኖች ናቸው።

14 These be the heads of their fathers’ houses: The sons of Reuben the firstborn of Israel; Hanoch, and Pallu, Hezron, and Carmi: these be the families of Reuben.

15 የስምዖንም ልጆች ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ፥ ያኪን፥ ዶሐር፥ የከነዓናዊቱም ልጅ ሳኡል እነዚህ የስምዖን ወገኖች ናቸው።

15 And the sons of Simeon; Jemuel, and Jamin, and Ohad, and Jachin, and Zohar, and Shaul the son of a Canaanitish woman: these are the families of Simeon.

16 እነዚህም እንደ ወገኖቻቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።

16 And these are the names of the sons of Levi according to their generations; Gershon, and Kohath, and Merari: and the years of the life of Levi were an hundred thirty and seven years.

17 የጌድሶንም ልጆች እንደ ወገኖቻቸው ሎቤኒ፥ ሰሜኢ ናቸው።

17 The sons of Gershon; Libni, and Shimi, according to their families.

18 የቀዓትም ልጆች እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል ናቸው የቀዓትም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነው።

18 And the sons of Kohath; Amram, and Izhar, and Hebron, and Uzziel: and the years of the life of Kohath were an hundred thirty and three years.

19 የሜራሪ ልጆች ሞሖሊ፥ ሙሲ ናቸው። እነዚህ እንደ ትውልዳቸው የሌዊ ወገኖች ናቸው።

19 And the sons of Merari; Mahali and Mushi: these are the families of Levi according to their generations.

20 እንበረምም የአጎቱን ልጅ ዮካብድን አገባ፥ አሮንና ሙሴንም ወለደችለት የእንበረምም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።

20 And Amram took him Jochebed his father’s sister to wife; and she bare him Aaron and Moses: and the years of the life of Amram were an hundred and thirty and seven years.

21 የይስዓር ልጆች ቆሬ፥ ናፌግ፥ ዝክሪ ናቸው።

21 And the sons of Izhar; Korah, and Nepheg, and Zichri.

22 የዑዝኤል ልጆች ሚሳኤል፥ ኤልዳፋን፥ ሥትሪ ናቸው።

22 And the sons of Uzziel; Mishael, and Elzaphan, and Zithri.

23 አሮንም የአሚናዳብን የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፥ እርስዋም ናዳብንና አብዮድን አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።

23 And Aaron took him Elisheba, daughter of Amminadab, sister of Naashon, to wife; and she bare him Nadab, and Abihu, Eleazar, and Ithamar.

24 የቆሬ ልጆች አሴር፥ ሕልቃና፥ አብያሳፍ ናቸው እነዚህ የቆሬ ልጆች ወገኖች ናቸው።

24 And the sons of Korah; Assir, and Elkanah, and Abiasaph: these are the families of the Korhites.

25 የአሮንም ልጅ አልዓዛር ከፉትኤል ልጆች ሚስት አገባ፥ እርስዋም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህ እንደ ወገኖቻቸው የሌዋውያን አባቶች አለቆች ናቸው።

25 And Eleazar Aaron’s son took him one of the daughters of Putiel to wife; and she bare him Phinehas: these are the heads of the fathers of the Levites according to their families.

26 እነዚህ አሮንና ሙሴ እግዚአብሔር፦ ከግብፅ ምድር በየሠራዊቶቻቸው የእስራኤልን ልጆች አውጡ ያላቸው ናቸው።

26 These are that Aaron and Moses, to whom the Lord said, Bring out the children of Israel from the land of Egypt according to their armies.

27 እነዚህ የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ያወጡ ዘንድ ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን ጋር የተነጋገሩ ናቸው እነዚህ ሙሴና አሮን ናቸው።

27 These are they which spake to Pharaoh king of Egypt, to bring out the children of Israel from Egypt: these are that Moses and Aaron.

28 እግዚአብሔርም በግብፅ አገር ሙሴን በተናገረው ቀን እንዲህ ሆነ

28 And it came to pass on the day when the Lord spake unto Moses in the land of Egypt,

29 እግዚአብሔር ሙሴን፦ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እኔ የምነግርህን ሁሉ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገር ብሎ ተናገረው።

29 That the Lord spake unto Moses, saying, I am the Lord: speak thou unto Pharaoh king of Egypt all that I say unto thee.

30 ሙሴም በእግዚአብሔር ፊት። እነሆ እኔ ከንፈረ ቈላፍ ነኝ እንዴትስ ፈርዖን ይሰማኛል? አለ።

30 And Moses said before the Lord, Behold, I am of uncircumcised lips, and how shall Pharaoh hearken unto me?