ኦሪት ዘጸአት Orit ZeTseAt
Exodus / Shemot #7
In Amharic and English

Can’t see Amharic font?

 

ኦሪት ዘጸአት 7

Exodus 7

1 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ እይ፥ እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ ወንድምህም አሮን ነቢይ ይሆንልሃል።

1 And the Lord said unto Moses, See, I have made thee a god to Pharaoh: and Aaron thy brother shall be thy prophet.

2 ያዘዝሁህን ነገር ሁሉ አንተ ትነግረዋለህ ወንድምህም አሮን የእስራኤልን ልጆች ከአገሩ ይለቅቅ ዘንድ ከፈርዖን ጋር ይናገራል።

2 Thou shalt speak all that I command thee: and Aaron thy brother shall speak unto Pharaoh, that he send the children of Israel out of his land.

3 እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፥ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ።

3 And I will harden Pharaoh’s heart, and multiply my signs and my wonders in the land of Egypt.

4 ፈርዖንም አይሰማችሁም፥ እጄንም በግብፅ ላይ አደርጋለሁ፥ ሠራዊቴንም የእስራኤልን ልጆች ሕዝቤን በታላቅ ፍርድ ከግብፅ አገር አወጣለሁ።

4 But Pharaoh shall not hearken unto you, that I may lay my hand upon Egypt, and bring forth mine armies, and my people the children of Israel, out of the land of Egypt by great judgments.

5 ግብፃውያንም፥ እጄን በግብፅ ላይ በዘረጋሁ ጊዜ፥ የእስራኤልንም ልጆች ከመካከላቸው ባወጣሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆነሁ ያውቃሉ።

5 And the Egyptians shall know that I am the Lord, when I stretch forth mine hand upon Egypt, and bring out the children of Israel from among them.

6 ሙሴና አሮንም እንዲህ አደረጉ እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ።

6 And Moses and Aaron did as the Lord commanded them, so did they.

7 ፈርዖንንም በተናገሩት ጊዜ ሙሴ የሰማንያ ዓመት ሰው ነበረ፥ አሮንም የሰማንያ ሦስት ዓመት ሰው ነበረ።

7 And Moses was fourscore years old, and Aaron fourscore and three years old, when they spake unto Pharaoh.

8 እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው።

8 And the Lord spake unto Moses and unto Aaron, saying,

9 ፈርዖን፦ ተአምራትን አሳዩኝ ሲላችሁ፥ አሮንን፦ በትርህን ወስደህ እባብ እንድትሆን በፈርዖን ፊት ጣላት በለው።

9 When Pharaoh shall speak unto you, saying, Shew a miracle for you: then thou shalt say unto Aaron, Take thy rod, and cast it before Pharaoh, and it shall become a serpent.

10 ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ እግዚአብሔርም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ አሮንም በትሩን በፈርዖንና በባሮቹ ፊት ጣለ፥ እባብም ሆነች።

10 And Moses and Aaron went in unto Pharaoh, and they did so as the Lord had commanded: and Aaron cast down his rod before Pharaoh, and before his servants, and it became a serpent.

11 ፈርዖንም ጠቢባንንና መተተኞችን ጠራ የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው እንዲሁ ደግሞ አደረጉ።

11 Then Pharaoh also called the wise men and the sorcerers: now the magicians of Egypt, they also did in like manner with their enchantments.

12 እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፥ እባቦችም ሆኑ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠች።

12 For they cast down every man his rod, and they became serpents: but Aaron’s rod swallowed up their rods.

13 እግዚአብሔር እንደ ተናገረ፥ የፈርዖን ልብ ጸና፥ አልሰማቸውምም።

13 And he hardened Pharaoh’s heart, that he hearkened not unto them; as the Lord had said.

14 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ የፈርዖን ልብ ደነደነ፥ ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ።

14 And the Lord said unto Moses, Pharaoh’s heart is hardened, he refuseth to let the people go.

15 ማልደህ ወደ ፈርዖን ሂድ እነሆ ወደ ውኃ ይወጣል፥ ትገናኘውም ዘንድ አንተ በወንዝ ዳር ትቆማለህ እባብም ሆና የተለወጠችውን በትር በእጅህ ትወስዳለህ።

15 Get thee unto Pharaoh in the morning; lo, he goeth out unto the water; and thou shalt stand by the river’s brink against he come; and the rod which was turned to a serpent shalt thou take in thine hand.

16 እንዲህም ትለዋለህ። የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር፦ በምድረ በዳ እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ እነሆም እስከ ዛሬ አልሰማህም።

16 And thou shalt say unto him, The Lord God of the Hebrews hath sent me unto thee, saying, Let my people go, that they may serve me in the wilderness: and, behold, hitherto thou wouldest not hear.

17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ እነሆ እኔ የወንዙን ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ፥ ውኃውም ተለውጦ ደም ይሆናል።

17 Thus saith the Lord, In this thou shalt know that I am the Lord: behold, I will smite with the rod that is in mine hand upon the waters which are in the river, and they shall be turned to blood.

18 በወንዙም ያሉት ዓሦች ይሞታሉ፥ ወንዙም ይገማል ግብፃውያንም የወንዙን ውኃ ለመጠጣት ይጠላሉ።

18 And the fish that is in the river shall die, and the river shall stink; and the Egyptians shall lothe to drink of the water of the river.

19 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ አሮንን፦ በትርህን ውሰድ፥ ደምም እንዲሆኑ በግብፅ ውኆች በወንዞቻቸውም በመስኖቻቸውም በኩሬዎቻቸውም በውኃ ማከማቻዎቻቸውም ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ በለው በግብፅም አገር ሁሉ በእንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ይሆናል።

19 And the Lord spake unto Moses, Say unto Aaron, Take thy rod, and stretch out thine hand upon the waters of Egypt, upon their streams, upon their rivers, and upon their ponds, and upon all their pools of water, that they may become blood; and that there may be blood throughout all the land of Egypt, both in vessels of wood, and in vessels of stone.

20 ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ በትሩንም አነሣ፥ በፈርዖንና በባሪያዎቹም ፊት የወንዙን ውኃ መታ የወንዙም ውኃ ሁሉ ተለውጦ ደም ሆነ።

20 And Moses and Aaron did so, as the Lord commanded; and he lifted up the rod, and smote the waters that were in the river, in the sight of Pharaoh, and in the sight of his servants; and all the waters that were in the river were turned to blood.

21 በወንዙም የነበሩ ዓሦች ሞቱ ወንዙም ገማ፥ ግብፃውያንም ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉም ደሙም በግብፅ አገር ሁሉ ነበረ።

21 And the fish that was in the river died; and the river stank, and the Egyptians could not drink of the water of the river; and there was blood throughout all the land of Egypt.

22 የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ እግዚአብሔርም እንደተናገረ የፈርዖን ልብ ጸና፥ አልሰማቸውምም።

22 And the magicians of Egypt did so with their enchantments: and Pharaoh’s heart was hardened, neither did he hearken unto them; as the Lord had said.

23 ፈርዖንም ተመልሶ ወደ ቤቱ ገባ፥ ይህንም ደግሞ በልቡ አላኖረውም።

23 And Pharaoh turned and went into his house, neither did he set his heart to this also.

24 ግብፃውያንም ሁሉ የወንዙን ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉምና በወንዙ አጠገብ ውኃ ሊጠጡ ቆፈሩ።

24 And all the Egyptians digged round about the river for water to drink; for they could not drink of the water of the river.

25 እግዚአብሔርም ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈጸመ።

25 And seven days were fulfilled, after that the Lord had smitten the river.